የ113 ሰዎች ሕይወት በቆሼ ጥፍቷል! ሕወሃት ነዋሪዎች ላይ የፈጸመውን ወንጀል ለማምለጥ ከሃገር ውስጥ በመለመላቸውና ቴክሳስ ዩኒቨርሲቲ ወዳጆቹ መንስዔው እንዲጣራ የኮሚቴ አባሎች መለመለ

15 Mar

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)
 
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 6፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአዲሰ አበባ ከተማ ቆሼ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ቅዳሜ እለት በደረሰው አደጋ የሟቾች ቁጥር 113 መድረሱ ተገለጸ።

የአዲስ አበባ ከንቲባ ድሪባ ኩማ ማምሻውን በሰጡት መግለጫ፥ ፍለጋው ወደ መጠናቀቅ ደርሷል፤ በፍለጋው የአካባቢው ህብረተስብ ከፍተኛ ርብርብ አድርጓል ብለዋል።

በተለይም የአካባቢው ወጣቶች በፍለጋው ወቅት ያደረጉት ድጋፍ ከፍተኛ ነው ያሉት ከንቲባው፤ የአካባቢው ህብረተሰብ እና ለወጣቶች ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ከንቲባው አያይዘውም፥ የአደጋው መንስኤ ከሀገር ውስጥ እና በውጭ ሀገራት ባለሙያዎች እንደሚጣራ አስታውቃል።

መንስኤውን ለማጥናትም ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና ከአሜሪካው ቴክሳስ ዩኒቨርሲቲ የተወጣጡ ባለሙያዎች በተቀናጀ አኳኋን እንዲሰሩ የማድረግ ዝግጅት እየተደረገ ነው ብለዋል።

አስከሬናቸው የተገኘ ሟቾች ስርዓተ ቀብር በዛሬው እለትም መፈፀሙን ገልፀዋል።

ከ113 ሟቾች መካከል 75ቱ ሴቶች ሲሆኑ 38ቱ ወንዶች ናቸው።

ከንቲባ ድሪባ ኩማ በቆሻሻ ክምር መደርመስ ጉዳት የደረሰባቸውንና በአደጋ ስጋት ከቤታቸው የተፈናቀሉ ዜጎችን በዛሬው እለት ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።

ከንቲባው ቤተሰቦቻቸውን በአደጋው በሞት አጥተው በድንኳን ውስጥ ሀዘን የተቀመጡ ሰዎችን እና ለተጎጂዎቹ ቤተሰቦች ምን አይነት ድጋፍ እየተደረገ እንዳለ ተመልክተዋል።

በአደጋው ምክንያት ቤተሰቦቻቸውን በሞት የተነጠቁ ሰዎች ከከንቲባ ድሪባ እጅ ከከተማ አስተዳደሩ ወጪ የተደረገ ለቀብር ማስፈፀሚያ የሚሆን የገንዘብ ድጋፍ ተቀብለዋል።

የተደረገው የገንዘብ ድጋፍም በአንድ ህይወቱ ባለፈ ሰው ለቀብር ማስፈፀሚያ ተብሎ የ10 ሺህ ብር የተሰጠ ሲሆን፥ በዛሬው እለትም ለ11 ሰዎች የገንዘብ ድጋፉ ተሰጥቷል።

የሚደረገው የቀብር ማስፈፀሚያ የገንዘብ ድጋፍ በቀጣይ የሟቾች ቤተሰቦችን በማጣራት እንደሚሰጥም ከንቲባ ድሪባ ኩማ ተናግረዋል።

ከዚህ በተጨማሪም በቀጣይ ተመሳሳይ የቆሻሻ መደርመስ አደጋ ሊደርስባቸው ይችላል በሚል ስጋት ከቤታቸው ተፈናቅለው በኮልፌ ቀራኒዮ ወረዳ 1 ወጣት ማእከል ለገቡ ዜጎችም ድጋፍ እየተደረገ ይገኛል።

ከተማ አስተዳደሩ ከሚያደርገው ድጋፍ ባለፈም በግለሰቦች፣ በማህበራት እና በአካባቢው ነዋሪዎች ጭምር ድጋፍ እየተደረገ ነው።

ከቤታቸው የተፈናቀሉ ሰዎችም ከተማ አስተዳደሩ በዘላቂነት የምንቋቋምበት መንገድ ሊያዘጋጅልን ይገባል ሲሉ ጠይቀዋል።

ከንቲባ ድሪባ ኩማም፥ መጠለያ በማዘጋጀት እና ሌሎች ድጋፎችን ለማድረግ የከተማ አስተዳደሩ እንደሚሰራ ተናግረዋል።

በዘላቂነት የማቋቋም ስራው አደጋ የደረሰባቸውን ብቻ ሳይሆን ለአደጋም ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችንም ይጨምራል ያሉት ከንቲባው፥ ሁሉንም በአጭር ጊዜ ውስጥ መልሶ የማቋቋም ስራ ይሰራል ብለዋል።

ከዚህ ባሻገር የነዋሪዎቹን የመጠለያ እና በዘላቂነት ኑሯቸውን ለማሻሻል የሚያስፈልገውን ሁሉ ለመስራት የሚያስችል በከንቲባው የሚመራ ኮሚቴ ተቋቁሙ ስራዎችን እያከናወነ መሆኑን ገልጸዋል።

በተያያዘ በዛሬው እለትም በፍርስራሹ ስር የቀሩ አስክሬኖችን የማፈላለግ እና የማውጣት ስራም እንደቀጠለ ነው።

በርካታ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎችም በአደጋው የተጎዱ ሰዎችን ስፍራው ድረስ በመሄድ የተለያዩ ድጋፎችን በማድረግ እና በማጽናናት ላይ ይገኛሉ።
 

ተዛማጅ፡

በአዲስ አበባ የሚገኙ ኤምባሲዎችና ዓለምአቀፍ ተቋማት የሃዘን መልዕክት እያስተላለፉ ነው

የቆሼ አደጋ የሕወሃትን አፓርታይዳዊ ሥርዓትን ከምድረ ኢትዮጵያ መገርሰስን አስፈላጊነትን ገሃድ አድርጎታል!
 

%d bloggers like this: