የአገዛዙን ዕድሜ ለማርዘም፥የሕወሃት አፈና አዋጅ ለተጨማሪ አራት ወራት ተራዘመ

30 Mar

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

የሕወሃት ፕሮፓጋንዳ ምንጭ የሆነው ፋና በዛሬው ዕለት እንደዘገበው ከሆነ፡ የሕወሃት የአፈና መሣሪያ የሆነው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለቀጣዮቹ አራት ወራት ተራዝሟል።

ለነገሩማ የሰብዓዊ መብቶችን የሚረግጡት የአዋጁ አካሎች ተነስተዋል ቢባልም፡ ነባሩና አፋኙ አዋጅ እንዳለ ነው የጸደቀው። ይህም ሕወሃት የፈለገውን እየመረጠ እንዲያጠቃ የሕግ ድጋፍ (Discretionary powers exercised by administrative and legal authorities) ይሠጠዋል! በነገራችን ላይ፣ ይህንኑ አስመልክቶ የፋና ጋዜጠኛ ኃይለየሱስ ሥዩም እንደታዘበው፣

“ምንም እንኩዋን አዋጁ ባስገኛቸው ጥቅሞች የተወሰኑ ማሻሻያዎች ተደርገው ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ መያዝና ፍተሻ እንዲሁም በሚዲያ ላይ ተጥለው የነበሩ ክልከላዎች በከፊልና በሙሉ ቢነሱም፣ አብዛኞቹ ክልከላዎች ግን አሁንም በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ውስጥ እንደተካተቱ ነው። በዚህም የአስቸኩዋይ ጊዜ አዋጁን ለማስፈጸም ወጥተው በስራ ላይ ያሉ ደንቦችና መመሪያዎች ተፈጻሚነታቸው የሚቀጥል ይሆናል።”

እስካሁን የኢትዮጵያ ሕዝብ ስለአዋጁ ምንነት ጉዳቱንና ወራሪው የገዥው አባሎች – ዩኒፎርም የለበሱትም ሆነ በሲቪሊያን ልብስ የሚዘዋወሩት – ሲዘርፉ፡ ሲያስሩና ሲገድሉ እንጂ፥ አንዳችም ለሃገር የሚፈይድ ነገር ሲሠሩ እንዳልነበር ዜጎች ምሥክርነቶቻቸውን ሲያሰሙ ቆይተዋል።

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ኮማንድ ፖስት ሴክሬታሪያትና የመከላከያ ሚኒስትሩ ሲራጅ ፈጌሳ – በዋሾነታቸው የኃይለማርያም ደሣለኝ ታናሽ ወንድም መሆናቸው የሚታይላቸው – ለምክር ቤቱ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዲራዘም ያስፈለገበትን ምክንያት ሲያቀርቡ ከተጠቀሱት መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፦

    (ሀ) በሀገሪቱ ተጋርጦ የነበረውን የጸጥታ ችግር በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መቆጣጠር መቻሉን

    (ለ) ክልሎች በሚዋሰኑባቸው አካባቢዎች የሚነሱ ችግሮችን ለመጠቀም የሚፈልጉ ፀረ ሰላም ኃይሎች እየተንቀሳቀሱ መሆናቸውን

    (ሐ) በሁከትና ብጥብጡ ቀንደኛ መሪዎች ከነበሩት ውስጥ አብዛኛዎቹ ቢያዙም ቀሪ በመኖራቸውና በወረቀት ፅሁፎችን በመበተን አሁንም ሰላምና መረጋጋትን ለማደፍረስ የሚጥሩ ወገኖች አልፎ አልፎ በመታየታቸው

    (መ) በአንፃራዊነት ሰላምና መረጋጋቱ የተሻለ ደረጃ ላይ ቢገኝም፣ ወደማይቀለበስበት ደረጃ ላይ ለማድረስ ተጨማሪ ጊዜ ማስፈለጉን

    (ሠ) የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መርማሪ ቦርድም በመላ ሀገሪቱ ያደረገውን ቅኝት መሠረት አድርጎ አዋጁ ቢራዘም የሚል አስተያየት ለምክር ቤቱ በመቅረቡ

በተለይም ልጆቹን መልሶ መዋጥ የማይችል ወላጅ ነፍሶች ገብሮ፡ ሚስቶችና ልጆች ባሎቻቸውንና አባቶቻቸውን ገብረው፡ በእሥር ላይ በቶርች አጓጉል ሆነውባቸው እያዩ፣ ይህ አዋጅ ይራዘምልን ብለው ጠየቁ ምናልባት መጠይቁ የተሠራጨው ለወያኔ አባሎች ብቻ ከሆነ፣ ያ ሌላ ታሪክ ነው። ኢትዮጵያ ውስጥ ሃገር እየተገነባች ያለችው ዜጎችን በማሰቃየትና በሃሰት ነው! ለዚህ ነው ሕወሃትም ብዙ ቀባጥሮ ብዙ ሳይሆንለትም የቀረው!

በኢራቅ የአሜሪካ ጦር አዛዥ ጋዜጠኞች ከ140 በላይ ሲቪሎች በአሜሪካ ጦር ተገድለዋል ሲባል ወደ ክህደትና ምክንያታዊነት አልሄዱም! ሳናጠፋ አለቀረንም ነው ያሉት። ይህም ወታደሮቻቸውን ታማኞች ማድረግ ብቻ ሳይሆን፡ ሃገራቸውም በጦሯ እንድትኮራ የሚያደርግ ነው!

ሕወሃት ግን የሚፈልገውን ‘ውጤት’ ወይንም ዓላማ ለማሳካት፡ ይዋሻል፡ ይሠርቃል፡ ያሥራል፡ ይገድላል፤ ይዘርፋል፤ ይሠርቃል፤ ይገድላል፤ ሌላውን ሕዝብ ግን አትሥረቅ፤ አትግደል፤ ጉቦ አትብላ ብሎ በሕጉ ሊቀጣ ይሞክራል፤ ምንም ውጤት ላያገኝበት!

ይህ እኮ ነው ሕዝቡ የወንበዴ አስተዳደር ላይ አመኔታ እንዳይኖረው የሚያደርገው። ወያኔ ታርሞ፣ ተምሮና ተሻሽሎ ደህና አስተዳዳዳሪ ይወጣዋል ብሎ የሚያስብ ካለ 26 ዓመት ረዥም ነው ያ ሊሆን አልቻለም! አይችልም!

ይህም አዋጅ በየሚዲያውና በየሃገሩ የሕወሃትን ማንነትና ምንነት – ሰብዓዊ መብቶች ጣሽነትና ወንበዴነት – ግልጥ አድርጎ አሳይቷል! ምነው ሩዋንዳና ኢትዮጵያ ታዋቂዎቹ በኮማንድ ፖስት ሃገርና ሕዝብ አፋኞች መሆናቸው በዓለም ዙርያ የታወቀ እንደሆነ ገምተው ያውቃሉ?

ለኢትዮጵያውያን ይህ አዋጅ ተነሳ፡ ተራዘመ ምንም ለውጥ አይኖርም! አዋጁም ቢነሳ ሕወሃት ሃገራችንን ከመቸብቸብ ዜጎቿን ከማዋረድ አይቆጠብም!

በእኔ እይታ፣ ስለአዋጁ ከሕግ አንጻር ትክክለኛውን ትንተና የሠጠው የሁማን ራይትስ ዎች ጥናት ነው!
 

Related:

Breaking News: Ethiopia falls under six-month state of emergency
 

%d bloggers like this: