ወጣቱ ቢጠቀም እንዴት በተደሰትን!         ‘ኬኛ ቤቬሬጅስ አክሲዮን ማኅበር’ ግን ለሕወሃቶችና ግብረ አበሮቻቸው በፖለቲካውና ኤኮኖሚውም መጠቀሚያ ነው! የኢትዮጵያ ወጣቶች ወደ ፊት የሚያቀኑት በሕወሃት መቃብር ላይ ብቻ ነው!

1 Apr

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

የአዘጋጁ አስተያየት

  ሕወሃት ወደ መቃብሩ ሲያቀና በድንገት ለኢትዮጵያ ወጣቶች ተቆርቋሪ ለመምሰል የማይሠራው ቲአትር የለም! አዛኝነት እንዴት በድንገት ይከሰታል፣ በተለይም እንደ ሕወሃት ከመሰለ ጨካኝ፣ ቂመኛና አረመኔያዊ ከሆነ እጁ በደም የተጨማለቀ ድርጅት?

  በ2015/2016 የመንግሥት በጀት ውስጥ በተመሳሳይ ለመጀመሪያ ጊዜ 10 ቢሊ ብር ለሥራ አጥ ወጣቶች ተይዞ፡ በሶስት ወራት ደብዛው መጥፋቱን ስናስታውስ፡ እንዲሁም ሕወሃት ርኅራሄ የጎደለው፣ በእነዚህ ሁለት ዓመታት በተለይ ወጣቱ ላይ የፈጸማቸው ጭፍጨፋዎች ግንዛቤ ውስጥ ሲገቡና የአሁኑ ቅጡ የጠፋበት የፖለቲካ ማምታት ግራ የመጋባቱ ምልክት መሆኑን በመንገነዘብ ወጣቱ – በተለይም የማኮላሸት ትኩረት ያረፈበት የኦሮሞ ወጣት – ከአራጆቹ ስለት እንዲጠነቀቅ ምልክቶቹን በሚገባ ማየት ይኖርበታል።

  ይኸው ሕወሃት ወጣቱ እንደገና እንዳይነሳ በመፍራቱና የድንጋጤው ብዛት አይደል እንዴ ኦሮሚያ ውስጥ ባለሃብቶች ያፈሩትን ንብረት በመውረስ፣ ለዘለቄታው ግን የክልሉን የወደፊት የኢኮኖሚ ተስፋ በፍጥነት ለማጨለም በሚያስችል ሁኔታ ያንን ከጊዜው አስተሳሰብ ውጭ የሆነ የፖሊሲ እርምጃ በቅርቡ የወሰደው?

  የውጭዎቹ እነዳንጎቴ፡ አላሙዲና ሌላውም የሲሚንቶ ቱጃሮች በቀላሉ የማይገፉ በመሆናቸው ዳንጎቴ በናይጀሪያው ጋዜጣ ላይ እንዳስቀመጠው፣ እርምጃችሁ አንድ ሣንቲም ወጭ ቢጨምርብኝ አልቀበልም ሲል እግሩን የቆመበት ላይ እንደተከለ ቀረ! ዜጋ የሆኑ በ60 ሺ ዶላር ድርጅታቸውን ያቋቋሙት ግለሰብ ግን ‘ትን እንዳይልህ ውሃ ጠጣ‘ ነው የተባሉት!

  አሁንም በዚህች የመጨረሻው ደቂቃ እንኳ፡ ኬኛ ቤቬሬጅስ አክሲዮን ማበር የተሰኘ ድርጅት በመንግሥትና የግል ባለሃብቶች ባለቤትነት የ5.7 ቢሊ ብር ካፒታል ግብ ዒላማ ያደረገ የንግድ ድርጅት ማቁቋማቸውን ሕወሃት አውጇል። ዚህ ውስጥ የመንግስት የልማት ድርጅቶች 15 በመቶ ብቻ ድርሻ እንደሚኖራቸው ተገልጿል።

  መንግሥት ይህን ድርሻ የሚይዘው በዋናነት ከዚህ ትርፍ ለማግኘት ሳይሆን የክልሉ ባለሀብቶች ከወጣቶችና አርሶ አደሮች ጋር ተቀናጅተው መሥራት እንዲችሉ ለማነሳሳት ነው ይላል ሕወሃት።

  ዓላማውም ሆነ አሠራሩ በቅድሚያ ወጣቱን ለመያዝ በመሆኑ፣ እንደሌሎቹ የሕወሃት አሠራሮች ሁሉ ግልጽነት የጎደለው መሆኑን ማንም ሊገነዘበው ይችላል።

  የአክስዮን ድርጅቱ ሲቋቋም እንደገና ስጦታ ያሸበረቀበት ምልክቱ ኦሮሞነቱን ጎላ ማድረጉ ሲሆን፡ ይሀ ለተነሱት የመብት ጥያቄዎች መከበር መልስ መሆናቸው ታስቦት ይመስላል፦

   (ሀ) የድርጅቱ አክስዮን የሚሸጠው በኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ፣ በአዋሽ ኢንተርናሽናል ባንክና በኦሮሚያ የኅብረት ስራ ባንክ ሁሉም ቅርንጫፎች እየተከናወነ ይገኛል ተብሏል

   (ለ) የአክሲዮን ማህበር የፋብሪካዎች ማዕከልም የአዋሽ ምንጭ የሆነችውና በምዕራብ ሸዋ ዞን የኦሮሞት ተቃውሞ የተቀሰቀስባት ጊንጪ ከተማ እንደሆነም ተገልጿል

  ሕወሃት የአማራ የልማት ሕወሃትና ድርጅቶችን አቋቁመው አሁን ካፒታሉ ከሕወሃት በለጠ ብለው በቅርቡ የጻፉትን በቅርቡ አይጋና ትግራይ ኦን ላይ ካነበብን በኋላ፡ ድርጅቱ ነፍሰ ገዳይ መሆኑ ብቻ ሳይሆን፣ ከራሱ የበላይነት አባዜ ውጭ ለሌሎች ብኄረስቦችና በአጠቃላይም ለኢትዮጵያም አንደ ሃገር አንዳች ደንታ የሌላቸው አረመኔዎች ጥርቅምና ዳር ድንበሯን ለሱዳን የቸረቸረ በመሆኑ፣ ከእንግዲህ ይህንን እያወቀ በማጅራቱ መታረድ የሚፈልግ ልፈፋውን አቁሙ ሄዶ መታረድ ይችላል!

  ማስታወስ ቢያሰፈልግ ፣ የሕወሃት ሊቀመንበር ባለቤት ትርፉ ኪዳነ ማርያምና የጌታቸው አሰፋ ወንድም ዳንኤል አሰፋ 100 ያህል ትግሬዎችን በዋሽንግቶን ኢትዮጵያ ኤምባሲ ውስጥ ከ2015 ምርጫ በኋላ ነሐሴ ወር ውስጥ አምባሳደሩን ጭምር ከኤምባሲው አስወጥተው ያደረጉት ስብሰባ ላይ ተማርን የሚሉት ትግሬዎች ካነሱላቸው ጥይቄዎች መካከል የሚከተለው ይገኙበታል፦

  “እናንተ (የሕውሃት አመራሮች) ለትግራይ ህዝብ ምንም አልሰራችሁም፤አማራጭ አጥተን እናንተን እየደገፍን ለመቀጠል ተገደናል፣ ከእናነተ ውጭ ያለው አማራጭ ጉድጓድ ስለሆነና፣ የትናንቶቹ ተመልሰው እንዳይመጡ እነቸግራችሁ ከእናንተ ጋር ቆመናል”

  በአዲስ አበባ ደረጃ ልማቱ ለምን በትግራይ አይካሄድም የሚል ጥያቄ የተነሳ ሲሆን፣ ለኢትዮጵያ አመታዊ ስፖርት ውድድር ባህር ዳር ከመሄድ ይልቅ መቀሌ ውስጥ ለምን ትልቅ ስታዲየም አልተሰራም የሚል ጥያቄ ከተሰብሳቢዎች ተነስቷል።

  ሕወሃትና ሃገራዊነት ይህ ነው!

  ሲጠቃለልም፡ ከዚህ ሁሉ የፖለቲካ ትርጉመ ቢስ ድብብቆሽ፣ ዛሬ ሃገራችን ለገጠማት የአልገዛምነት የፖለቲካ ቀውስ መልሱ ሕወሃት ረግጦ በአፈና ከሕዝቡ የገፈፈውን የመገር፡ የመሰብሰብና የመደራጀት ነጻነት መልቀቅ ነው፤ ከተወሰነ የመደራጀት ሂደት በኋላም ጊዜያዊ መንግሥት እንዲቋቋም በሩ መከፈት ይኖርበታል። ከዚያ በኋላ ሕወሃት እንደ ድርጅትና አባሎቹም በግልና በጋራ በሃገራችንና ሕዝባችን ላይ ለፈጸሙት የአፈና፡ ያላግባብ እሥራት፡ ዘረፋና ግድያ በኃጢያታቸው መጠን ፍርዳቸውን መቀበል ይኖርባቸዋል!

===============
 

የአክስዮን ድርጅቱን መቋቋም ዜና ከፋና ክዚህ በታች ይመልከቱ፡፟

ኬኛ ቤቬሬጅስ አክሲዮን ማህበር ተመሰረተ

Keenga Beverages S.C. (Fana)

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 23፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ኬኛ ቤቬሬጅስ የተሰኘ ግዙፍ አክሲዮን ማህበር በግል ባለሀብቶች፣ በህዝብና በመንግስት ጥምረት ዛሬ በይፋ ተመስርቷል።

ይህ ኩባንያ ከአልኮል ነጻ የሆኑ የማልት መጠጦች፣ ለስላሳ መጠጦች፣ ጭማቂዎች፣ የማዕድን ዉሃ፣ የብርጭቆና የጠርሙስ ፋብሪካዎችን እና የስፖርት እና መዝናኛ ዘርፍን ያካተተ ሲሆን ኬኛ ቢራንም ያመርታል።

የኦሮሚያ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ እንዳስታወቀው ለኩባንያው እውን መሆን 5 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር ካፒታል እንደሚያስፈልግ በጥናት ተረጋግጧል።

ከዚህ ውስጥ የመንግስት የልማት ድርጅቶች 15 በመቶ ብቻ ድርሻ እንደሚኖራቸው ተገልጿል።

መንግስት ይህን ድርሻ የሚይዘው በዋናነት ከዚህ ቢዝነስ ትርፍ ለማግኘት ሳይሆን የክልሉ ባለሀብቶች ከወጣቶችና አርሶ አደሮች ጋር ተቀናጅተው መስራት እንዲችሉ ለማነሳሳት ነው ብለዋል የቢሮው ሀላፊ አቶ አዲሱ አረጋ።

ቀሪው የአክሲዮን ድርሻ በግል ባለሀብቶች፣ በወጣቶች እና በአርሶ አደሮች የሚሸፈን ይሆናል።

በዛሬው ዕለት በኦሮሞ ባህል ማዕከል አዳራሽ ብቻ በተደረገ የምስረታ ስነ ስርዓት የ1 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር አክሲዮን ተሽጧል።

ዛሬ ከተሸጠው አክሲዮን የመንግስት የልማት ድርጅቶች የ500 ሚሊየን ብር፣ በመላው ኦሮሚያ በጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት የተደራጁ ወጣቶች የ300 ሚሊየን ብር አክሲዮኖች የገዙ ሲሆን፥ የቀረውን አክሲዮን የግል ባለሀብቶች እና ሌሎች ግለሰቦች ገዝተዋል።

ከዚህ በተጨማሪ የአክሲዮን ሽያጩ በኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ፣ በአዋሽ ኢንተርናሽናል ባንክ እና በኦሮሚያ የህብረት ስራ ባንክ ሁሉም ቅርንጫፎች እየተከናወነ እንደሚገኝ ተጠቁሟል።

የኬኛ ቤቬሬጅስ አክሲዮን ማህበር የፋብሪካዎች ማዕከል የአዋሽ ምንጭ የሆነችውና በምዕራብ ሸዋ ዞን የምትገኘው ጊንጪ ከተማ መሆኗም ነው የተገለፀው።

ለመሆኑ ሃገራችን ውስጥ በከተማዎች ብቻ 22 ከመቶ ሕዝባችን ሥራ አጥ ሲሆን (በሕወሃት መረጃ)፣ ከዚህም ውስጥ በዕድሜ ከ19-29 ያለው ብቻ ሜዳ ላይ የተጣለ ነው – ወይ የረባ ትምህርት ያልተሠጠው ነው! ታዲያ ለምንድነው ይህ ትኩረት የኦሮሚያ ሥራ አጥ ላይ ብቻ ያተኮረው?
 

ተዛማጅ፡

It’s a mindset/political culture in Ethiopia today things should be done at someone’s expense – the TPLF has institutionalized – Part I
 

%d bloggers like this: