ለ3.3 ሚሊ ወጣቶች ሥራ ለመፍጠር በ10ቢሊ በጀት የተደገፈ ዕቅድ ቢተገበርም፣ 28.3% ብቻ መሳካቱ ታወቀ! ባላዋቂነት/ያላግባብ የሚባከነው የሃገሪቱ ገንዘብ ነው የሚያሳዝነው!

11 Apr

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)
 
አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 3፣ 2009 (ኤፍ ቢ ሲ) በበጀት አመቱ ባለፉት 8 ወራት ከ900 ሺህ በላይ ለሆኑ ወጣቶች የስራ እድል ቢፈጠርም ተግባሩ የሚፈለገውን ያክል አለመሆኑን የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አስታወቀ፡፡

ምክር ቤቱ በዛሬው ውሎው የኢፌዴሪ የወጣቶችና ስፖርት ሚኒስቴርን የስምንት ወራት እቅድ አፈጻጸም አድምጧል፡፡

የኢፌዴሪ ወጣቶችና ስፖርት ሚኒስቴር ባለፉት ስምንት ወራት ከ935 ሺህ በላይ ለሆኑ ወጣቶች በከተማና በገጠር የስራ እድል መፍጠሩን ገልጿል።

በከተማ በአምስቱ እድገት ተኮር የስራ ዘርፎች፥ የማምረቻ፣ ግንባታ፣ የከተማ ግብርና፣ አገልግሎትና ንግድ ዘርፍ ለ580 ሺህ 590 ወጣቶች የስራ እድል ተፈጥሯል ነው ያለው።

በገጠርም በግብርና ለ248 ሺህ 524 እንዲሁም ከግብርና ውጭ ባሉ የስራ መስኮች ደግሞ 107 ሺህ 576 ወጣቶች የስራ እድል መፍጠሩን ገልጿል።

ይሁን እንጅ በበጀት አመቱ በስራ አጥነት ለተለዩ ከ3 ነጥብ 3 ሚሊየን በላይ ወጣቶች ለመፍጠር ከታቀደው የስራ እድል አንጻር ቁጥሩ አነስተኛ መሆኑ ተገልጿል።

ሚኒስቴሩም ስራ አጥ ወጣቶችን የመለየትና የማሰልጠን ስራ ረጅም ጊዜ በመውሰዱ እቅዱ በሚፈለገው ልክ ላለመከናወኑ በምክንያትነት አንስቷል፡፡

ከተዘዋዋሪ የወጣቶች ፈንድ አተገባበር ጋር ተያይዞም፥ ብድር የሚያቀርቡ ተቋማትን አቅም የማጠናከር እና የአመራሩን ግንዛቤ የማሳደግ ስራ እየተሰራ በመቆየቱ ወደተግባር አለመገባቱን አንስቷል።

አሁን ላይም ለብድር ስርጭቱ የሚውል የመጀመሪያ ዙር ገንዘብ ክልሎች ባላቸው የወጣት ቁጥር ልክ በመላኩ በቀሪ የበጀት አመቱ ወራት ወደ ስራ ይገባል ብሏል።

ለወጣቶች አገልግሎት የሚሰጡ የወጣት ማዕከላት ወጥ የሆነ አገልግሎት ይሰጡ ዘንድም ደረጃ ወጥቶላቸው እንዲሰሩ ይደረጋል ነው የተባለው።

ሚኒስቴሩ በሪፖርቱ ልዩ ፍላጎት ያላቸውን በተለይም አካል ጉዳተኛ ወጣቶችን ተጠቃሚ ለማድረግ አቅም ማጎልበቻ ስልጠና እየተሰጠ መሆኑን ጠቅሶ፥ ችግሮቻቸውን መፍታት የሚችሉባቸው መድረኮች መዘጋጀታቸውን ጠቁሟል።

ከዚህ ባለፈም ህገ ወጥ የሰዎች ዝወውርን ከመግታት አንጻር ያከናወናቸው ስራዎችን አቅርቦም ውይይት ተደርጎባቸዋል።
 

ተዛማጅ:

  It’s a mindset/political culture in Ethiopia today things should be done at someone’s expense – the TPLF has institutionalized – Part I

  ወጣቱ ቢጠቀም እንዴት በተደሰትን!‘ኬኛ ቤቬሬጅስ አክሲዮን ማኅበር’ ግን ለሕወሃቶችና ግብረ አበሮቻቸው በፖለቲካውና ኤኮኖሚውም መጠቀሚያ ነው! የኢትዮጵያ ወጣቶች ወደ ፊት የሚያቀኑት በሕወሃት መቃብር ላይ ብቻ ነው!

  TPLF’s new employment plan more politics than jobs & means for stealing more resources

  Why does TPLF consider foresight a crime, seeing Ethiopia being in danger zone?

  Human rights & plurality sink to the lowest in 2016 in Ethiopia

  ኢትዮጵያ ወደአደገኛ አግጣጫ እያመራች ነው

 

%d bloggers like this: