‘ኢትዮጵያ’: ቴዲ ያበረከተልን የፋሲካ ገጸ በረከታችን

17 Apr

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)
 
ይህንን ፎቶ ሰኞ ጥዋት 3ሺ800 ሰዎች እንደሚወዱት ፈስ ቡኬ ላይ መስከረዋል!
 
ኢትዮጵያ ውስጥ ተከብሮና ተከባብሮ በሰላም መኖር የሚሻ ሁሉ፡ ሕዝቡ ከሚያከብረውና ከሚወደው ነገር ጋር ሁሉ መላተምን ማስወገድ ዋነኛው የሕይወት መመሪያ መሆን አለበት።

ለምሣሌም ያህል፡ ኢትዮጵያውያን ግንባራቸውንና ልባቸውን ከሚያኮሳትሩበት ዘረኝነቱ በተጨማሪ፡ በሥልጣንና በተዘረፈ የሃገርና የዜጎች ሃብት ጥጋብ ውጥጥር ያለው ሕዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ (ሕወሃት)፡ ቴዲ አፍሮን እንደአዝማሪ ማነኪኑ አድርጎ ለማሸከርከር ሲዳዳው ነው፡ ገና ከማለዳው ቴዲ መመሪያው ኢትዮጵያዊነት እንጂ ገንዘብ ወይንም ባለሥልጣን ላይ መንጠላጠል አለመሆኑን ለነመለስ ዜናዊ አሰረግጦ እንዲህ ሲል “በያሰተስርያል” ያስታወቀው፡-

‘በ17 መርፌ በጠቆመው ቁምጣ
ለለውጥ ያጎፈረው ዙፋን ላይ ሲወጣ
አዲስ ንጉሥ እንጂ ለውጥ መች መጣ’

ከዚሀ በሁላ፡ –እንደምናውቀው– ለአረመኔው ሕወሃት ክፋትና የጥፋት በትር ቢጋለጥም፡ ቴዲ ግንባሩን ሳያጥፍ መኖር ብቻ ሳይሆን፡ ክምን ጊዜውም በላይ ይህ ወጣት የሙዚቃ ሰው ከጦር ሰው ባላነሰ ኢትዮጵያን ካዓመት ዓመት ከፍ ከፍ እያደረገ እየተንከባከባት ይገኛል!

ከሶስት ዓመታት በፊት ቴዲ መኖሪያዬ ሂልሲንኪ መጥቶ ሲጫወት፣ አዳራሹ ባዶ እንዲሆንበት ከየአቅጣጫው በትዊተር ጭምር በሃሰት ‘ኮንሰርቱ ተሠርዟል’ የሚለውን መረጃ ጸረ-ኢትዮጵያዊ ሕወሃቶችና ቅጥረኞቻቸው ሲለቁ፡ እርሱ ለጥቂት አድናቂዎቹ አዳራሹ ውስጥ ሲጫወት፡ እኔም ቲወተሬ ላይ ያ መልዕክት ደርሶኝ ሃሰታቸውን ለመቁቋም (ብዙ ካሳሳቱ በኋላ) መልሶች በአማርኛና እንግሊዝኛ መሥጠቴ ትዝ ይለኛል።

“ኢትዮጵያን” እንደሰማሁ፡ በተለይም ቃላቱን ቅዳሜ ማታ በደንብ ካወራረድሁ በሁላ፡ በማግሥቱ በፌስ ቡክ ገጼ ላይ ለቴዲና አምለሰት ምሥል ከበሬታየን ገልጫለሁ። እንደ አምለሰት ዐይነት ጠንካራ ባለቤት ከባልዋ ጀርባ ካልቆመች፡ ‘አባ ወራው’ ብቻውን ሙሉ ጥንካሬውን ሊያወጣው አይችልም! በመሆኑም፡ ቴዲ ለኢትዮጵያ ተቆርቋሪ ብቻ ሣይሆን፡ በአርትና ሙዚቃው ለኢትዮጵያ ደኅንነትና መከበር ታላቅ አሰተዋጽዖ ያደረገ አዝማች፡ ገና የሚያደርግ ዜጋ ጭምር ነው!

ሊያና ተፈሪ ከእንግሊዝ ሃገር በትዊተር ገጿ የሚከተለውን ስትለቅ፡ እኔ እንዴት ልብ አላልኩትም በማለት ተመልሼ እንደገና ሙዚቃውን ማጫወቴን አስታውሳለሁ!

እመኑኝ፤ ራሳችንን ካላከበርን ማንም አያከበረንም! ራሳችንን የምናከብረው ደግሞ በባዶነት ሳይሆን ባለን አኩሪ ታሪክ፣ ዕድሉን መጠቀም የሚችል፡ ኤትዮጵያዊነትን የተላበሰ፡ ይህን ጨዋ ብርቱ ሠራተኛ ሕዝብ አክብሮ ወደ ተሻለ ዘመናዊ አመራርና አስተዳደር ሊያሸጋግር የሚችል እኩልነትና ነጻነትን መርሁ ያደረገ መንግሥት ሲመሠረት ነው!

በሃይማኖትና በዘር ዜጎችን መከፋፈል የሕወሃቶችና ቅጥረኞቻቸው እምነትና ‘መንግሥታዊ’ መመሪያ በኖነባት ሃገር፣ ቴዲ፡

‘ተዋዶ ያለበት እስላም ክርስቲያኑ
ተዘነጋሽ እንዴ ኢትዮጵያ መሆኑ
አንቺም በሃይማኖትሽ እኔም በሃይማኖቴ
መኖር እንችላለን አይጠበንም ቤቴ!

ሸገር አዲስ አበባ አንቺ ያለሽበት
ራጒኤል አይደል ወይ የአኗር ጎረቤት
ቅዳሴንና ዛኑን አጥር ቢለያቸው
ፈጣሪ ከሰማይ በአንድነት ሰማቸው!’

ከእምነትና ፍቅር የበለጠ ምንም ኃይል እንደሌለ ነው ሸመን ደ ፈር (Chemin de fer) ላይ የተመሠረተ ሙዚቃው የሚያሳየን! የሃገራችን የወደፊት ጉዞዋ ገና ብዙ ፍቅር የሚያስፈልገው ነው – ፖሊሲና አይዲኦሎጂ ብቻ ሳይሆን!

‘…ዛሬ አዲስ አይደለም የነካሽ ሲቃጠል…’! ለሚለው ቴዲ ጭንቅላት ውስጥ ያልው ትርጉም ከታሪከ ጋር የተያያዘ ሊሆን ይችላል። አላውቅም! በእኔ አተረጓጎም ግን ሕዝቡን የሚጨፈጭፍ ገዥ ለኔ መንግሥት አይደለም። ሕወሃት ትውልድ እያጠፋ ነው። አያሌ ወጣቶች እሥራቱንና ግድያውን ተቋቁመው የነጻነት ትግላቸውጽን ሲያፋፍሙ አይደል እንዴ፡ ሕወሃት በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ወደ ወንጀልና የትምህርት ውድቀት የኤኮኖም ማዘቀጥ የዞረው!

ስለሆነም በሁለቱ ወገኖች በኩል በሚደረገው ትግል ምክንያት፥ ሕወሃት በክራይሲስ በመቃጠል ላይ ነው ብዩ ተርጉሜዋለሁ!

ለአንዴም ሆነ ለመጨረሻ ጊዜ የኢትዮጵያ ነጻነት ሊረጋገጥ የሚችለው፡ የሕዝባችን ሥቃይ የሚያበቃው፡ ዘረኛ፡ ዋሾና ወንበዴውን የሕወሃት አስተዳደር ማንኮታኮቱ ሲጠናቀቅ ነው! የታሪክ ሂደት ነውና ደግሞ ይሆናል!
 

%d bloggers like this: