በጋምቤላ መሬት የተቀራመቱ የቀን ጅቦች ሕጉ ተፈጻሚ እንዳይሆንባቸው ለደጋፊዎቻቸው ዋይታቸውን እያሰሙ ነው! ምነው ዋና ዘራፊዎቹ እዚህ አልተጠቀሱ?

27 Apr

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)
 

አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 19 ፣ 2009 (ኤፍ ቢ ሲ) የእፎይታ ጊዜያችን ሳያልቅ እንዲሁም በመሬት መደራረብ ምክንያት ስራ አቁሙ በተባልንበት ሁኔታ ውላችን እንዲሰረዝ ተደርጎብናል ሲሉ በጋምቤላ ክልል በግብርና ኢንቨስትመንት ላይ የተሰማሩ ባለሀብቶች ቅሬታቸውን ያሰማሉ።

በ2008 ዓ.ም በሰፋፊ እርሻ ኢንቨስትመንት ላይ ያጋጠመው ችግር ከአቅም በላይ ሆኗል በሚል መንግስት ለበርካታ ወራት የዘለቀ ጥናት በጋምቤላ ክልል በዘርፉ ላይ እንዲካሄድ ማድረጉ ይታወሳል።

ጥናቱ ዘርፉ ላይ በርካታ ችግሮች እንዳሉ ከለየ በኋላ በጋምቤላ ክልል ያሉ የዘርፉ ባለሀብቶችን በተለያየ ደረጃ በመመደብ ፥ መልካም አፈጻጸም ላመጡት የኤ ደረጃን በጣም ዝቅተኛ ውጤት አምጥተዋል ላላቸው 269 የዘርፉ ተዋናዮች ደግሞ ኤፍ በመስጠት ውላቸው እንዲቋረጥ ምክረ ሀሳብ አቅርቧል።

የክልሉ መንግስትም ይህን ምክረ ሀሳብ ተቀብሎ በቅርቡ የ269ኙን ውል ሰርዟል፤ ይሁን እንጅ ይህ እርምጃ ያልተገባ፣ ውልና ህግንም ያላከበረ መሆኑን 300 አባላት ያሉት የጋምቤላ ባለሃብቶች ማህበር ቅሬታ አቅርቧል።

የማህበሩ ሊቀ መንበር አቶ የማነ ሰይፉ፥ ውላቸው እንዲሰረዝ የተደረጉት የማህበሩ አባላት በመሬት መደራረብ ምክንያት መንግስት ጉዳዩን እስከማጣራ ስራ አቁሙ ባላቸው ሁኔታ መሆኑ ተገቢ አይደለም ይላሉ።

ቢ ኤች ኦ የተሰኘ የህንድ ኩባንያ በዚህ ክልል ኢታንግ 27 ሺህ ሄክታር ተቀብሎ ስራ ከጀመረ በኋላ ብድሩን ሳይመልስ መሰወሩ ይታወሳል፤ በኩባንያው መሬት ላይ 22 ባለሀብቶች ተደርቦ ተሰጥቷችው ችግሩ ከታወቀ በኋላ ነገሩ እስከሚስተካከል ስራ እንዲያቆሙ ተደርገው ነበር።

አቶ ሳምሶን ወልደማርያም ኩባንያቸው በዚሁ የቢ ኤች ኦ መሬት ላይ ተደርቦ በተሰጠው 1 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ ማልማት ከጀመረ በኋላ፥ መሬቱ ተደርቧልና ካርታ ይስተካከል በሚል ለሁለት አመታት ስራ እንዲያቆሙ መደረጋቸውንና በዚያው ውሉ መሰረዙንም ይናገራሉ።

አቶ ሳምሶን እንደሚሉት ኩባንያቸው ከተረከበው መሬት ተደረበ የተባለውን ትቶ በ200 ሄክታሩ ላይ ምርት እያመረተ መሆኑንም ነው የተናገሩት።

በሌላ በኩል ግን ብድር ለማግኘት የእርሳቸውን ድርሻ አምስት ሚሊየን ብር ለባንክ አስይዘው እየጠበቁ ባሉበት ሁኔታ፥ ለዘርፉ ብድርና መሬት ይቁም በተባለበት ጊዜ ገንዘባቸው እስካሁን በባንክ ተይዞ ባለበትም ሁኔታ ውላቸው መሰረዙ ተገቢ አለመሆኑን ያነሳሉ።

ውላቸው ከተሰረዙ 269 መሬት ወሳጆች መካከል ከ100 በላይ የሚሆኑት ገና የውላቸው ጊዜ አለመጠናቀቁን የሚናገሩት ደግሞ የማህበሩ ሊቀ መንበር አቶ የማነ ሰይፉ ናቸው።

እስከ 450 ሄክታር መሬት ያለማ እና የብድር ድርሻውን 10 ሚሊየን ብር ያስያዘ አባላችንም ባልተገባ ሁኔታ ውሉ ተሰርዟል ብለዋል።

ድርሻቸውን በሚሊየን ብር ለባንክ አስይዘው ብድር የሚጠብቁ 25 አባላቶችም ውላቸው መሰረዙ ተገቢ አይደለምም ነው ያሉት፤ ከእርምጃው በፊት የባለሀብቶች ድምጽ ሊሰማ ይገባ እንደነበር በመጥቀስ።

የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጋት ሉዋክ ቱት በበኩላቸው፥ ክልሉ በፌደራል መንግስት እጅ የነበረውን መሬት እንዲያስተዳድር ከተወሰነ በኋላ ከዚህ ቀደም በተሰራው ጥናት ላይ ተመስርቶ የወሰደውን እርምጃ ተከተሎ ቅሬታ ቀርቦለት እየተመለከተ መሆኑን ተናግረዋል።

የእፎይታ ጊዜያችን ሳያልቅ ውላችን ተሰርዟል በሚል ለቀረበው አቤቱታ ግን፥ በዚህ ላይ የደረሳቸው ጥያቄ እንደሌለ ጠቅሰው ወደፊት ከቀረበ እንደሚታይ ገልጸዋል።

ከእርምጃው በኋላም ባለሀብቶቹ በጥናቱ የታየንበት መንገድ በድጋሚ ይታይልን በሚል ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ቅሬታ አቅርበው፥ ጽህፈት ቤቱ የባለሀብቶች ጉዳይ በድጋሚ እንዲታይ መወሰኑን ሰምተናል።
 

ተዛማጅ:

    Gambella’s failed commercial agriculture & Tigrean investors; TPLF nepotism, lawlessness & corruption; Sebhat Nega rooting for Tigrean land grabbers: Unequal Ethiopianity is the challenge in 2017 (Part I)

    The issue in Gambella commercial farms is ethnicity. Why are some Ethiopians more privileged than others, in Gambella the army killing tens of thousands to keep them ‘safe’! There’s crime to unveil!

    Gambella land grab breeds TPLF lawlessness & corruption; DBE & its ponzi scheme at the centre of it!

%d bloggers like this: