በጋምቤላ የሕወሃቶች ዘረፋ ምክንያት የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ከሥሮ አዲስ ካፒታል ቢሰጠውም፣ የብሔራዊ ባንኩ ገዥ አሁም ባንኩ አደጋ ላይ ነው ይላሉ!

4 May

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)
 
አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 26፣ 2009 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ከሰጠው ብድር መመለሱ የሚያጠራጥረው ገንዘብ ከተቀመጠው ገደብ በላይ መሆኑ ተነገረ።

በዓለም አቀፍ አሰራር መሰረት ንግድ ባንኮች ካበደሩት ገንዘብ ውስጥ መመለሱ አጠራጣሪ የሚሆነው፥ ከአምስት በመቶ በላይ እንዳይሆን ሲፈለግ የልማት ባንኮች ደግሞ ከ15 በመቶ እንዳይበልጥ ነው የሚፈለገው።

ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉት ንግድ ባንኮች በዚህ መለኪያ መሰረት፥ ጤናማ የሚባል ደረጃ ላይ መሆናቸውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መረጃ ያሳያል።

እንደ ብሔራዊ ባንክ መረጃ ንግድ ባንኮች ካበደሩት ገንዘብ ውስጥ መመለሱ አጠራጣሪ የሆነው፥ 2 ነጥብ 9 በመቶ ነው።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ አቶ ተክለወልድ አጥናፉ እንደሚሉት፥ የልማት ባንኮች የሚሰጡት ብድር በዓለም አቀፍ ደረጃም ቢሆን ከንግድ ባንኮች በተቃራኒ አብዛኛው የመካከለኛ እና ረጅም ጊዜ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በተለያዩ መንገዶች የሚያበድረውን ገንዘብ የሚሰጠው የኢትዮጵያ ልማት ባንክ፥ መመለሱ አጠራጣሪ የሆነው ከተቀመጠው ገደብ በላይ መሆኑን የብሔራዊ ባንኩ መረጃ ያሳያል።

የልማት ባንኩ ተመላሽነቱ ጥርጣሬ ውስጥ የገባው ብድር ከተቀመጠው የ15 በመቶ ገደብ አልፎ አሁን 16 ነጥብ 1 በመቶ የደረሰ ሲሆን፥ በዚህ የሚቀጥል ከሆነ ወደ ከፍተኛ አደጋ ሊያመራ ይችላል ይላሉ አቶ ተክለወልድ።

የባንኩ አጠራጣሪ ብድር እዚህ ደረጃ ሊደርስ የቻለው፥ በሀገሪቱ ውስጥ ያለው የተበዳሪዎችን ማንነት የሚገልጽ መረጃ ላይ በሚከሰት ችግር ምክንያት መሆኑንም ይጠቅሳሉ።

የብሔራዊ ባንኩ ገዥ ከተበዳሪዎች መረጃ ችግር በተጨማሪ አሁን ላይ በሀገሪቱ ውስጥ እንደሌሎች ሀገራት ክሬዲት ሬቲንግ የሚሰሩ ተቋማት አለመኖራችው፥ ለብድሩ ተመላሽነት አጠራጣሪነት ሌላው ምክንያት በመሆኑ ሀገሪቱ ገለልተኛ መረጃም ሊኖራት እንደሚገባም አንስተዋል።

በሌላ በኩል የልማት ባንኩ አጠራጣሪ ብድር ከፍተኛ የሆነው ከባንኩ ብድር የወሰዱ ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው ጊዜ ወደ ምርት ባለመግባታቸው መመለስ ስላልቻሉ ሲሆን፥ ይህ ደግሞ በብድርም ብቻ ሳይሆን በውጭ ምንዛሪ ግኝቱ እየተስተዋለ መሆኑንም ያነሳሉ።

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የኮርፖሬት ማስተዋወቅና ግንኙነት ተጠባባቂ ዳይሬክተር አቶ ሀይሉ ምስጋናው በበኩላቸው፥ ልማት ባንኩ በአሁኑ ወቅት መመለሱ አጠራጣሪ የሆነው ብድር ችግር ለመፍታት፥ ከፍተኛ ማኔጅመንቱን ጨምሮ መዋቅራዊ ለውጥ እያደረገ ነው ብለዋል።

በዚህ መሰረት ልማት ባንኩ ከሰሞኑ አራት ምክትል ፕሬዚዳንቶቹን አንስቶ በምትካቸው በብሔራዊ ባንክ እስከሚጸድቅለት ድረስ ምክትል እጩ ፕሬዚዳንቶችን ሾሟል ።

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ላለፉት ዓመታት በተለይም ለሰፋፊ እርሻዎች በቢሊየን የሚቆጠር ብርን ሰጥቷል፤ ሆኖም ይህን ብድር ከወሰዱት ባለሃብቶች መካከል ጥቂት የማይባሉት ተበዳሪዎች ንንዘቡን አግባብ በሆነ መልኩ እንዳልተጠቀሙበት መዘገቡ ይታወሳል።

ባንኩ ለተደራረቡ መሬቶች ሁለት ብድር መስጠቱ፣ ባለሃብቶች እስከ ብድራቸው መጥፋታቸው እና የአምራች ኢንዱስትሪው በወሰደው ብድር ልክ ምላሹ የሚጠበቀውን ያህል አለመሆኑ፥ ብድር አመላለሱ ላይ ጫና መፍጠሩም ተጠቅሷል።

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ብድሩን ጤናማ ለማድረግ አዲስ መመሪያ በሰፋፊ እርሻ ላይ መተግበሩ ይታወቃል።
 

One Response to “በጋምቤላ የሕወሃቶች ዘረፋ ምክንያት የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ከሥሮ አዲስ ካፒታል ቢሰጠውም፣ የብሔራዊ ባንኩ ገዥ አሁም ባንኩ አደጋ ላይ ነው ይላሉ!”

Trackbacks/Pingbacks

  1. Disturbing is Dr.Tedros Adhanom’s horse trading on human rights, | - May 12, 2017

    […] በጋምቤላ የሕወሃቶች ዘረፋ ምክንያት የኢትዮጵያ ልማት ባንክ … […]

    Like

Comments are closed.

%d bloggers like this: