የሃገሪቱ ዕዳ ከ$40 ቢሊዮን በላይ በሆነበት ወቅት የሕወሃት ፓርላማ ተጨማሪ ቢሊዮን ያህል የአሜሪካን ዶላር ብድሮችን አጸደቀ

23 Jun

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 15፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሁለተኛ ዓመት የስራ ዘመን በ42ኛ መደበኛ ጉባኤው ከቀረቡለት 15 የተለያዩ ረቂቅ አዋጆች በብድር ስምምነት ላይ ያተኮሩ ስድስት አዋጆችን በሙሉ ድምጽ አፅድቋል።

ለሁለተኛው የከተሞች የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን 236 ሚሊየን 400 ሺህ ኤስ ዲ አር እና 125 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር የብድር ስምምነት አዋጅ ጸድቋል።

ኤስ ዲ አር ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም ለአባል ሀገራት እንደ አማራጭ መገበያያ የፈጠረው የገንዘብ መለኪያ ሲሆን፥ የአንድ ኤስ ዲ አር ዋጋ ምንዛሬ 1 ነጥብ 4 የአሜሪካ ዶላር አካባቢ ነው።

ለንግድና ሎጂስቲክስ 110 ሚሊየን 400 ሺህ ኤስ.ዲ.አር፣ ለጥራት ማረጋገጫ መሰረተ ልማት ማሻሻያ 37 ሚሊየን 200 ሺህ ኤስ.ዲ.አር፣ ለጤና መሰረተ ልማት ፕሮግራም ማስፈጸሚያ 110 ሚሊየን 600 ሺህ ኤስ.ዲ.አር ከአለም አቀፉ የልማት ማህበር ጋር የተደረጉ ስምምነቶች ፀድቀዋል።

በዛሬው ጉባኤ ከጃፓን ዓለም አቀፍ የትብብር ድርጅት ጋር ለሴቶች ንግድ ስራ ፈጠራ ብቃት ማሻሻያ ማሳደጊያ ፕሮጀክት ማስፈጸሚያ የሚሆን፥ 5 ነጥብ 5 ቢሊየን የጃፓን የን የብድር ስምምነት አዋጅ ፀድቋል።

ለህብረተሰቡ ተደራሽ የሆኑ የጤና ተቋማት ማጠናከሪያ ፕሮግራም ማስፈጸሚያ የጸደቀው የ5 ሚሊየን ዩሮ የብድር ስምምነት አዋጅ በኢትዮጵያና በጣልያን መንግስት መካከል የተደረገ ነው።

የበጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወይዘሮ ገነት ታደሰ እንዳሉት፥ የብድር ስምምነት አዋጆቹ ሀገሪቱ የጀመረችውን ልማት ለማስቀጠል የሚያግዙ ናቸው።

ከስምምነቱ የሚገኘው ገንዘብ የብድር ጫናው ያልበዛና ከአገሪቱ የብድር ስትራቴጂ ጋር የተጣጣመ መሆኑንም ጠቁመዋል።

ምክር ቤቱ በተጨማሪም የባቡር ትራንስፖርት አስተዳደር ረቂቅ አዋጅን መርምሮ ለትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ መርቷል።
 

ተዛማጅ

    ትልቁ የኢትዮጵያ ‘ፌደራል’ በጀት ድክመቱ፣ገጽታዎቹና ውስብስብ ችግሮቹ

    Ethiopia: TPLF’s economic argument and its opportunity cost

 

%d bloggers like this: