የአሜሪካ መጤ ተምች በሰባት ክልሎች በ135 ሺሕ ሔክታር መሬት ላይ የተዘራ በቆሎ ማጥቃቱ ተገለጸ

25 Jun
    የአዘጋጁ አስተያየት፡

    በሽታው ኢትዮጵያ ውስጥ መግባቱ ለዓመታት ቀደም ብሎ ታውቋል፡ በተለይም በኦሮሚያ ከጥር 2015 ጀምሮ ክትትል ሲደረግበት ነበር።

    ታዲያ መከላከያው ለምን እንዲህ ራቀ – ይህ የተጠያቂነትን አለመኖር አመላካች አይደለምን? የሃሰት የምርት ክምችት ማውራታችሁን ትታችሁ ይህ በደል የተፈጸመብት ሕዝብ ምንደነው የሚደረግለት — ‘መንግሥት’ ሥራውን መሥራት ሳይችል ሲቀር?

 

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)
በሪፖርተር
 

የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ሚኒስቴር የእርሻ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ተስፋዬ መንግሥቴ፣ በመኸር እርሻ እንቅስቃሴና በወቅታዊው የአሜሪካ ተምች ላይ ዓርብ ሰኔ 16 ቀን 2009 ዓ.ም. በሰጡት መግለጫ፣ ለኢትዮጵያም ሆነ ለአገሪቱ ባለሙያዎች አዲስ የሆነው የአሜሪካ ተምች ለግብርናው ዘርፍ ከባድ ፈተና መሆኑንና በበቆሎ ከተሸፈነው እርሻ በ135 ሺሕ ሔክታር መሬት ላይ መታየቱን አስረድተዋል፡፡

ተምቹ በኢትዮጵያ ከመከሰቱ አስቀድሞ ናይጄሪያ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ታንዛኒያና ኬንያ ሲገባ ወደ ኢትዮጵያ ሊገባ ይችላል ተብሎ ለአገሪቱና ለባለሙያዎቿ እንግዳ በመሆኑ መረጃ ለማቀናጀት፣ በምርምር ተቋማትና በሚመለከታቸው አካላት ግብረ ኃይል ተቋቁሞ ነበር፡፡ ሆኖም መረጃ ተሰብስቦ ለአርሶ አደሩና ለባለሙያዎች ሥልጠና ለመስጠት እየተዘጋጁ ባሉበት ወቅት፣ በደቡብ ክልል በቤንች ማጂ ዞን ተምቹ ቀድሞ መታየቱን ሚኒስትር ዴኤታው አስረድተዋል፡፡

አንድ ሔክታር መሬት በመስመር የተዘራ 58 ሺሕ ያህል የበቆሎ እግር ሲይዝ፣ ከዘር ጀምሮ እስከ ማንሳት ድረስም አርሶ አደሩን እስከ 15 ሺሕ ብር ያስወጣዋል፡፡ ከአንድ ሔክታር መሬት በአማካይ ከ40 እስከ 50 ኩንታል በቆሎ ሲገኝ፣ ሞዴሎች ደግሞ ከዚህ በላይ ያገኛሉ ይባላል፡፡ አነስተኛ አርሶ አደሮች ደግሞ በሔክታር ከ20 እስከ 30 ኩንታል እንደሚያገኙ፣ የጉራጌ ዞን የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ቢሮ ባለሙያዎች ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡
 

%d bloggers like this: