ገብሩ ዐሥራት፡                              “የኦሮሞ ብሔረተኝነት ፖለቲካ ከሌለ የትግራይ ሕዝብ አደጋ ላይ ይወድቃል”

29 Jun

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)
 
የዕለቱ ሃተታ ገብሩ ዐሥራትና ሌንጮ ለታ አሉ የተባለውን ጠቅሶ በቬሮኒካ መላኩ በቀረበው ጽሁፍ ላይ ያተኮረ ቅብጥል ያለ ምልከታ ነው።

አሁን በደረስንበት፣ እርስ በእርሳችን የመጠባብቅ ሳይሆን፡ ሕወሃት ባስገደደው ባህሪ መሠረት እያንድንዱ ለሥጋው ከራሚ ሆኖአል። በቀዳሚነት በሚያሳዛንና በሚያሳርፍ ሁኔታ ይህ ትግራይ ውስጥ ለረዥም ጊዜ ገሃድ ታይቷል፤ እይታየም ነው — ኢትዮጵያውያን በየወቅቱ ሲፈናቀሉና ሲጨፈጨፉ ማለት ነው!

ይህ በእንዲህ እንዳለ — ከራስ በላይ ንፋስ በማለት — በተለይም በአማራ ብኄረሰብ አካባቢ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ወደ ውስጣቸው በመመለስ —— በመደራጀቱም ሆነ በትግሉ ምሣሌ መሆን የሚገባውን ብኄረሰብ —— አንዳንድ ተማርን የተሚሉ የአማራ ብኄረሰብ አባሎች በአማራ ላይ ደረሰ የሚሉትን ጥቃት ሌላው የኢትዮጵያ ሕዝብ የራሱ ጥቃት ለማድረግ ፍላጎት የሌለው ይመስል፣ እየወሰዱ ያሉት አቅጥጫ፣ ከአማራ ተቆርቋሪነታቸው ይልቅ የራሳቸውን የሥልጣን ርሃብ ያረገዘ ሆኖ መታየት ከጀመረ ሰንበት ብሏል።

ይህም ሃገራችንን ወደ ፊት ወደ ከፋ አዘቅጥት ከሚጥሏት ሁኔታዎች አንዱ ይሆናል የሚል ሥጋት አለ። ተከራክረንበታል፤ ሰሚ ባይገኝም! ወይንም አሳማኝ ምክንያት ባይሰጥም!

ሌላው ቀርቶ፣ የገብሩ ዐሥራት መቆርቆር ለማን ነው? ለኢትዮጵያ ወይንስ ለትግራይ? ከግለሰብነታችን ባሻገር፣ ለሃገርና ለወገን ልናስብ ይገባል!

ይህንን እያዩ በዕድሜም ሆነ በልምድ ያልዳበሩትን፣ ወይንም በትምህርት ያልገፉትን አንደበተ ርቱዕዎች የሚያበራቷቸውም በብርቱ ከሃገሪቱ ነጻነት፡ የዜጎች እኩልነትና ደኅንነትና ከጋራ ጥቅምና አንፃር በቅጡ ሊያስቡበት ይገባል!
 

%d bloggers like this: