ገሃዱ ማን አለብኝነት በዜጎች ገንዘብ:         የ40/60 ባለ አንድ መኝታ ቤት ተመዝጋቢዎች ሕገ መንግሥቱን የጣሰ ድርጊት ተፈጽሞብናል አሉ

10 Jul

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)
by The Reporter
 

ከአዘጋጁ፦ ከራሱ ጥቅሞች ውጭ ለሕዝቡ ችግሮች ደንታ የሌለው የሕወሃት አስተዳደርን ቀጣፊነትና ዘራፊነት የሚያጋልጥ ጽሁፍ!

ለፖለቲካው ብልሹነትና መግማማት ግንዛቤ መንበብ ያለበት!

 

“ከ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤት ተመዝጋቢዎች ጋር ባንኩ ውል መፈጸሙን የገለጹት አቶ በቃሉ ውል የፈጸሙት ከባለ አንድ፣ ባለ ሁለትና ባለ ሦስት መኝታ ቤት ተመዝጋቢዎች ጋር ብቻ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ነገር ግን 324 ባለ አራት መኝታ ቤቶች የተገነቡ ቢሆንም፣ እነሱን በሚመለከት ውል የፈጸመ አካል ባለመኖሩ ሁለት አማራጮችን ማስቀመጣቸውን ጠቁመዋል፡፡ ለባለ ሦስት መኝታ ቤት የተመዘገቡ ለባለ አራት መኝታ ቤትም ላይ እንዲወዳደሩ፣ ነገር ግን አቅም የለንም የሚሉ ከሆነ ቤቶቹን ለአስተዳደሩ እንደሚያስረክቡ አክለዋል፡፡ የባለ አንድ መኝታ ቤቶች ተመዝጋቢዎች ዕጣ ፈንታ ምን እንደሆነ ጥያቄ የተቀረበላቸው አቶ በቃሉ፣ ለሙከራ በተሠሩት የክራውንና የሰንጋ ተራ ሳይቶች ባለ አንድ መኝታ ቤት አለመገንባቱን ተናግረው በቀጣይ በ2010 ዓ.ም. ዕጣ በሚወጣባቸው 20 ሺሕ ቤቶች ውስጥ እንደሚካተቱ አስረድተዋል፡፡ ሙሉ ክፍያ በተገለጸው ወቅት ከከፈሉ 11,088 ተመዝጋቢዎች ውስጥ ሦስት በመቶ ዳያስፖራዎች እንደሚሳተፉ፣ 20 በመቶ የመንግሥት ሠራተኞችም እንደሚካተቱ አቶ በቃሉ አክለዋል፡፡ በመንግሥት ሥራ ላይ ሆነው የተመዘገቡ፣ ነገር ግን በአሁኑ ጊዜ ከመንግሥት ሥራ የለቀቁ ከሆኑ ዕጣ ቢወጣላቸውም ቤቱ እንደማይሰጣቸው አስረድተዋል፡፡ በሁለቱ ሳይቶች ከተገነቡ የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ውስጥ የተወሰኑት ለመንግሥት ተቋማት በሽያጭ ስለመተላለፋቸው የተጠየቁት ኃላፊዎቹ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ አባተ ስጦታው አንድም ቤት ለማንም አካል እንዳልተሰጠ ገልጸዋል፡፡ በሁለቱ ሳይቶች የተገነቡት ቤቶች 972 መሆናቸውንና 320 ሱቆችም እንዳሉ ጠቁመው፣ ሁሉም በዕጣና በጨረታ የሚቀርቡ መሆናቸውን በማስረዳት ቤቶቹ አለመሸጣቸውን በተደጋጋሚ አስረድተዋል፡፡

የአቶ አባተን ምላሽ በማጠናከር፣ ‹‹ይኼ ጥያቄ በተደጋጋሚ እየተነሳ ምላሽ ሰጥተንበታል፤›› ያሉት ደግሞ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳዳር ቤቶች ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ይድነቃቸው ዋለልኝ ናቸው፡፡ በሁለቱም ሳይቶች በድምሩ 19 ሕንፃዎች ተገንብተዋል፡፡ ሕንፃዎቹ መጀመርያ ጊዜ ሊገነቡ የነበረው ባለ አንድ መኝታ ቤት 55 ካሬ ሜትር፣ ባለ ሁለት መኝታ ቤት 75 ካሬ ሜትርና ባለ ሦስት መኝታ ቤት 100 ካሬ ሜትር የነበረ ቢሆንም፣ በተደረገው የዲዛይን ለውጥ ካሬ ሜትሮቹ ተቀይረው፣ ባለ ሁለት መኝታ ቤት 124.97 ካሬ ሜትር፣ ባለ ሦስት መኝታ ቤት 150.09 ካሬ ሜትርና ባለ አራት መኝታ ቤት 168.6 ካሬ ሜትር ስፋት ያላቸው እንዲሆኑ መደረጉን አስረድተዋል፡፡ ቤቶቹ ለማንም አልተሸጠም ብለዋል፡፡”

መንግሥት በ2005 ዓ.ም. በዳግም ምዝገባ ይፋ ካደረጋቸው የጋራ መኖሪያ ቤቶች ፕሮግራሞች በ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤት ፕሮግራም የባለ አንድ መኝታ ቤት ተመዝጋቢዎች፣ ሐምሌ 1 ቀን 2009 ዓ.ም. በዕጣ ከተተላለፉ ቤቶች ውስጥ ‹‹ባለ አንድ መኝታ ቤት የለም›› መባሉ፣ ሕገ መንግሥቱን የጣሰ ድርጊት ነው ሲሉ ተቃውሞአቸውን እያሰሙ ነው፡፡

በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 25 ላይ ‹‹ሁሉም ዜጎች በሕግ ፊት እኩል መሆናቸውንና በመካከላቸው ማንኛውም ዓይነት ልዩነት ሳይደረግ በሕግ ጥበቃ ይደረግላቸዋል›› የሚለው ድንጋጌ ታልፎ፣ እንደ ማንኛውም የከተማዋ ነዋሪ በአቅማቸው ማግኘት የሚችሉትን የቤት መጠን በመመዝገብ የቆጠቡና እየቆጠቡ ቢሆንም፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እነሱን የሚያካትት ሕንፃ አለመገንባቱንና ከዕጣ ውጪ እንደሆኑ መግለጹ፣ ትልቅ የመብት ጥሰት መሆኑን ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡

ከ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ባለ አንድ መኝታ ቤት መመዝገባቸውንና እስካሁን ያለማቋረጥ እየቆጠቡ መሆናቸውን የገለጹት ወ/ሮ አፀደ አሰፋ፣ አቶ ፍጹም ገብረ ኪዳንና አቶ ደመና ቶሌራ ለሪፖርተር እንደተናገሩት፣ በ2005 ዓ.ም. ለመመዝገብ ሲሄዱ የቤቶቹ ስፋት ባለ 55፣ 75 እና 100 ካሬ ሜትር መሆኑ ተገልጾላቸው፣ አቅማቸው የሚፈቅደውን ባለ አንድ መኝታ ቤት የሆነውን 55 ካሬ ሜትር ስፋት ላለው ቤት ተመዝግበዋል፡፡ ላለፉት አራት ዓመታትም ያለማቋረጥ በመቆጠብ ላይ ናቸው፡፡ ግንባታቸው በተጠናቀቀው የክራውንና የሰንጋ ተራ ሳይቶች ባለ አንድ መኝታ ቤት እንዳልተገነቡ በወሬ ደረጃ የሰሙ ቢሆንም፣ መንግሥት እንዲህ እንደማያደርግና ወሬውን ችላ እንዳሉት ይናገራሉ፡፡

ነገር ግን ዘግይቶም ቢሆንም የተጠናቀቁት ቤቶች ለዕጣ ሲዘጋጁ በወሬ ደረጃ ቀደም ብለው የሰሙት እውነት ሆኖ በማግኘታቸው፣ በጣም ማዘናቸውንና በዜጎች መካከል እኩልነት ሳይሆን የበላይነት እንዳለ ያረጋገጡበት መሆኑንም አክለዋል፡፡ ከመንግሥት በላይ ማንን ማመን እንደሚቻል ግራ መጋባታቸውን የሚናገሩት አቶ ፍጹም፣ ከልጆቻቸው ጉሮሮ እየቀነሱ የቆጠቡት ከኪራይ ቤት ስቃይ ለመገላገልና ቀሪ ሕይወታቸውን ‹‹የራሴ›› በሚሉት ቤት ለማሳለፍ ቢሆንም፣ ከውድድር ውጪ መሆናቸው እንዳሳዘናቸው አስረድተዋል፡፡ አቅም ስለሌላቸውና የትም መድረስ እንደማይችሉ ስለሚታወቅ፣ ቢያንስ ሕገ መንግሥቱ ያረጋገጠላቸውን የእኩልነት መብት መንግሥት ሊያከብርላቸው ስለሚገባ፣ ለቤት ችግራቸውን መንግሥት ትኩረት ሰጥቶ ተግባራዊ እንዲያደርግላቸው ጠይቀዋል፡፡

ባለ አንድ መኝታ ቤት ተመዝጋቢዎቹ ቅሬታቸውን የገለጹት ሐምሌ 1 ቀን 2009 ዓ.ም. ለባለ ዕድለኞች በዕጣ የተላለፉትን ባለ ሁለት፣ ባለ ሦስትና ባለ አራት የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶችን አስመልክቶ የከተማ አስተዳደሩ፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክና የከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስቴር በጋራ ሐሙስ ሰኔ 29 ቀን 2009 ዓ.ም. በሒልተን አዲስ የሰጡትን ጋዜጣዊ መግለጫ ተከትሎ ነው፡፡

በ40/60 ቤቶች ፕሮግራም በ15 ቀናት ውስጥ ከ160 ሺሕ በላይ ነዋሪዎች የተመዘገቡ ቢሆንም፣ 140 ሺሕ የሚሆኑ ሰዎች በየወሩ እየቆጠቡ እንደሚገኙ የገለጹት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ በቃሉ ዘለቀ ናቸው፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዲዛይናቸው ተጠብቆ በጥራት የተገነቡ (በሰንጋ ተራና በክራውን) 972 ቤቶችን መረከባቸውን የተናገሩት ፕሬዚዳንቱ፣ ያለምንም ማቋረጥ በ18 ወራት ውስጥ የቆጠቡና መቶ በመቶ የቆጠቡ በዕጣው ውስጥ እንደሚካተቱ አስረድተዋል፡፡ በ18 ወራት ውስጥ 11,088 ሰዎች ሙሉ በሙሉ የቆጠቡ በመሆናቸው፣ በዕጣው ውስጥ መካተታቸውን አክለዋል፡፡ የንግድ ቤቶቹ በግልጽ ጨረታ እንደሚሸጡና ለጊዜው መነሻ ዋጋቸው በካሬ ሜትር 17 ሺሕ ብር መደረጉን አክለዋል፡፡

ከ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤት ተመዝጋቢዎች ጋር ባንኩ ውል መፈጸሙን የገለጹት አቶ በቃሉ ውል የፈጸሙት ከባለ አንድ፣ ባለ ሁለትና ባለ ሦስት መኝታ ቤት ተመዝጋቢዎች ጋር ብቻ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ነገር ግን 324 ባለ አራት መኝታ ቤቶች የተገነቡ ቢሆንም፣ እነሱን በሚመለከት ውል የፈጸመ አካል ባለመኖሩ ሁለት አማራጮችን ማስቀመጣቸውን ጠቁመዋል፡፡ ለባለ ሦስት መኝታ ቤት የተመዘገቡ ለባለ አራት መኝታ ቤትም ላይ እንዲወዳደሩ፣ ነገር ግን አቅም የለንም የሚሉ ከሆነ ቤቶቹን ለአስተዳደሩ እንደሚያስረክቡ አክለዋል፡፡ የባለ አንድ መኝታ ቤቶች ተመዝጋቢዎች ዕጣ ፈንታ ምን እንደሆነ ጥያቄ የተቀረበላቸው አቶ በቃሉ፣ ለሙከራ በተሠሩት የክራውንና የሰንጋ ተራ ሳይቶች ባለ አንድ መኝታ ቤት አለመገንባቱን ተናግረው በቀጣይ በ2010 ዓ.ም. ዕጣ በሚወጣባቸው 20 ሺሕ ቤቶች ውስጥ እንደሚካተቱ አስረድተዋል፡፡ ሙሉ ክፍያ በተገለጸው ወቅት ከከፈሉ 11,088 ተመዝጋቢዎች ውስጥ ሦስት በመቶ ዳያስፖራዎች እንደሚሳተፉ፣ 20 በመቶ የመንግሥት ሠራተኞችም እንደሚካተቱ አቶ በቃሉ አክለዋል፡፡ በመንግሥት ሥራ ላይ ሆነው የተመዘገቡ፣ ነገር ግን በአሁኑ ጊዜ ከመንግሥት ሥራ የለቀቁ ከሆኑ ዕጣ ቢወጣላቸውም ቤቱ እንደማይሰጣቸው አስረድተዋል፡፡ በሁለቱ ሳይቶች ከተገነቡ የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ውስጥ የተወሰኑት ለመንግሥት ተቋማት በሽያጭ ስለመተላለፋቸው የተጠየቁት ኃላፊዎቹ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ አባተ ስጦታው አንድም ቤት ለማንም አካል እንዳልተሰጠ ገልጸዋል፡፡ በሁለቱ ሳይቶች የተገነቡት ቤቶች 972 መሆናቸውንና 320 ሱቆችም እንዳሉ ጠቁመው፣ ሁሉም በዕጣና በጨረታ የሚቀርቡ መሆናቸውን በማስረዳት ቤቶቹ አለመሸጣቸውን በተደጋጋሚ አስረድተዋል፡፡

የአቶ አባተን ምላሽ በማጠናከር፣ ‹‹ይኼ ጥያቄ በተደጋጋሚ እየተነሳ ምላሽ ሰጥተንበታል፤›› ያሉት ደግሞ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳዳር ቤቶች ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ይድነቃቸው ዋለልኝ ናቸው፡፡ በሁለቱም ሳይቶች በድምሩ 19 ሕንፃዎች ተገንብተዋል፡፡ ሕንፃዎቹ መጀመርያ ጊዜ ሊገነቡ የነበረው ባለ አንድ መኝታ ቤት 55 ካሬ ሜትር፣ ባለ ሁለት መኝታ ቤት 75 ካሬ ሜትርና ባለ ሦስት መኝታ ቤት 100 ካሬ ሜትር የነበረ ቢሆንም፣ በተደረገው የዲዛይን ለውጥ ካሬ ሜትሮቹ ተቀይረው፣ ባለ ሁለት መኝታ ቤት 124.97 ካሬ ሜትር፣ ባለ ሦስት መኝታ ቤት 150.09 ካሬ ሜትርና ባለ አራት መኝታ ቤት 168.6 ካሬ ሜትር ስፋት ያላቸው እንዲሆኑ መደረጉን አስረድተዋል፡፡ ቤቶቹ ለማንም አልተሸጠም ብለዋል፡፡ ለየትኛውም የመንግሥት አካል አለመተላለፋቸውንና እንደማይተላለፉም በመግለጽ ምላሻቸውን አጠናክረዋል፡፡ ነገር ግን ሪፖርተር በመስከረም ወር በደረሰው መረጃ መሠረት፣ የመንግሥት ቤቶች ኤጀንሲ (አሁን የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ተብሏል) 300 ባለ አራት መኝታ ቤቶች ከ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች እንዲሸጥለት ባቀረበው ጥያቄ መሠረት እንደተፈቀደለት ታውቋል፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽሕፈት ቤት ሐምሌ 13 ቀን 2008 ዓ.ም. በቁጥር አ.አ/ከጽ/01/16.5/114 ለቤቶች ልማት አስተዳደር ቢሮ የጻፈው ደብዳቤ ይኼንኑ ያስረዳል፡፡ በወቅቱ ከሪፖርተር ጥያቄ የቀረበላቸው የቢሮ ኃላፊው አቶ ይድነቃቸው ዋለልኝም ጥያቄ የቀረበ ቢሆንም፣ የተፈቀደ ነገር እንደሌለ መግለጻቸውን መዘገባችን ይታወሳል፡፡

መንግሥት ለ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ ከፍተኛ ድጎማ ማድረጉን የገለጹት ምክትል ከንቲባ አቶ አባተ፣ በካሬ ሜትር 5,680 ብር መሸጥ የነበረበትን፣ በካሬ ሜትር 4,918 ብር እንዲተላለፉ መደረጉን ጠቁመዋል፡፡ በዚህም ከ720 ሚሊዮን ብር በላይ አስተዳደሩ ድጎማ ማድረጉን አክለዋል፡፡

ቤቶቹ በ18 ወራት ውስጥ ተገንብተው እንደሚተላለፉ የተገለጸ ቢሆንም፣ የዲዛይንና የስትራክቸር ለውጦች፣ በማኔጅመንት የተለዩ ችግሮች፣ ከአቅም ጋር በተያያዘና በተለያዩ ምክንያቶች ግንባታው መዘግየቱን የገለጹት የቁጠባ ቤቶች ኢንተርፕራይዝ ዋና ዳይሬክተር አቶ ኃይሉ ቀንዓ ናቸው፡፡ የቤቶቹ መስኮቶች ከፒቪሲ ወደ አልሙኒየም፣ ጣሪያቸው ከኤጋ ሺት ቆርቆሮ ወደ ኮንክሪት መቀየሩን፣ የግድግዳ ማዋቀሪያ ስፋት በመጨመሩ፣ ተሸካሚ ቋሚ ብረቶች ከባለ ስድስት ወደ ባለ ስምንት በመቀየራቸውና ሌሎችም ሥራዎች ለውጥ ስተለደረገባቸው የግንባታ ጊዜውን ሊያዘገየው እንደቻለ አስረድተዋል፡፡ የሚተላለፉት 972 ቤቶች መሠረተ ልማቶች የተሟሉላቸው መሆኑንም አክለዋል፡፡

ከቤቶቹ ግንባታ ፍጥነትና ብዛት አንፃር ተስፋ አስቆራጭ ስለመሆናቸው የተጠየቁት አቶ አባተ እንደገለጹት፣ በእሳቸው ግምት ተስፋ ሰጪ እንጂ ተስፋ አስቆራጭ አይደለም፡፡ በ2010 ዓ.ም. የሚተላለፉ 20 ሺሕ ቤቶች ግንባታቸው 68 በመቶ ደርሷል፡፡ የ17 ሺሕ ቤቶች ደግሞ 36 በመቶ ደርሷል፡፡ መንግሥት ለቤቶች ግንባታ ልዩ ትኩረት በመስጠት በየበጀት ዓመቱ 15 እና 16 ቢሊዮን ብር በጀት እየመደበ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡ በመሆኑም ተስፋ ሰጪ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ ቤት ፈላጊዎችን ባለቤት ለማድረግ ሌሎች አቅጣጫዎችም እየታዩ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ በመግለጫው ላይ የከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ጌታቸው ኃይለ ማርያም የተገኙ ሲሆን፣ የቤት ችግር ለዘመናት ሲከማች የኖረ በመሆኑ እሱን ለማቃለል መንግሥት የሚያደርገውን ርብርብ ኅብረተሰቡ ከግምት ውስጥ ማስገባት እንዳለበት አሳስበዋል፡፡
 

%d bloggers like this: