ትግረኛ ተናጋሪው የሕወሃት ክንፍ ብአዴን ላለፉት 26 ዓመታት የአማራ ሕዝብ ሲናገር የነበረውን መራራ ሐቅ አወጣ!

17 Jul

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)
by Veronica Melaku, welkaiyt.com
 
ዛሬ ብአዴን የተባለው ድርጅት አስገራሚና ለመዋጥ እጅግ የሚከብድ መራራ ሀቅ ይዞ ወጥቷል። ብአዴን የተናገረው እንደወረደ ሲቀርብ “በአማራ ክልል ውስጥ በደርግ ጊዜ ከተተከሉ የኤሌክትሪክ ማሰራጫዎች ውጭ ምንም አይነት አዲስ የኤሌክትሪክ ማሰራጫ ባለፉት 25 አመታት አልተሰራም” ይላል።

ይሄን አይነት የኢኮኖሚ አፓርታይድና “ባንቱስታይዜሽን “በኢትዮጵያ ውስጥ መኖሩን ሁሉም ህዝብ አውቆ ለአመታት ሲፅፍና ሲናገር የኖረ ቢሆንም ይሄ መራራ ሀቅ ከብአዴን ሲነገር ያስገርማል።

ብአዴን ዛሬ ሃቁን ቢተነፍሰውም ይሄን ጉዳይ የአማራ አርሶ አደር ከ20 ዓመታት በፊት ተናግሮ ነበር።

ገና ከጅምሩ አማራ ክልል ከሚገኘው የሀይል ማሰራጫ ተነስቶ የአማራ ክልል ከተሞችን በድቅድቅ ጨለማ ውጦ እያለፈ ሄዶ ለትግራይ ሃያ አራት ሰአት ኤሌክትሪክ ሲሰጥ የታዘበው የአማራ አርሶ አደር በራሱ ቀበሌ የሚያልፈውን የኤሌክትሪክ ግንድ እየቆረጠ ማረሻ ሰራበት ። በዚህ የተበሳጩት ወያኔዎች የመብራ ፖሉ በሚያልፍበት እያንድንዱ የአማራ ገበሬ ደጃፍ ላይ ተፈጻሚ የሚሆን ህግ ተግባራዊ ማድረግ ጀመረ። ይኸውም ከዚያን ግዜ ጀምሮ አንድ የመብራት ፖል ቢወድቅ በአቅራቢያው ያለው ገበሬ ቤትና በሬ ተሸጦ ለመብራት ሃግል ገቢ ይሆናል የሚል ነበር ።ከዚያን ግዜ ጀምሮ የጎጃምና የጎንደር ገበሬ ክረምት ከበጋ በተራ በተራ እየወጣ ግንዱን ሲጠብቅ ያድራል።

ታዲያ በደረቀ ሌሊት ተገትሮ ያዩት ሰዎች “ጨለማ ውስጥ ምን ታደርጋለህ ?” ብልው ሲጠይቁት” መቀሌን እራት እያበላሁ ነው!” ብሎ በሚያምር ቅኔ ይሄን ገደብ የለሽ አፓርታይድ ገልፆታል።

ዛሬ ትግራይ በመሠረተ ልማት፣ በጤና፣ በትምህርት፣ በኢንዱስትሪ እና በቢዝነስ ከኢትዮጵያ ግንባር ቀደም መሆኗን በመስማት ሳይሆን አይቶ ማረጋገጥ ይቻላል። ትግራይ ውስጥ ያልተገነባ ፋብሪካ የለም። ወጣቱ ትግራይን ለመገንባት የሚያስችለውን ገንዘብ እንዲያመጣ በመላው ኢትዮጵያ ተሰማርቷል። ትግራይ ውስጥ ያሉ አዛውንት እና መከላከያ ሠራዊት ብቻ ናቸው። ኤፈርት የተባለው የህወሀት የኢኮኖሚ ድርጅት ሀብት በአፍሪካ ተወዳዳሪ እንደሌለው አቦይ ስብሀት በአሜሪካ ድምጽ ቀርበው መስክረዋል። አሁን ያለማጋነን በኢትዮጵያ የትግራይ ሀብት ድርሻ ከ50 ፐርሰንት በላይ ነው። በእርግጥ የኤፍርት ሀብት ምንጭ ኢትዮጵያ ናት ትግራይ አይደለችም።

ዋናው ጉዳይ ችግሩን ማውራት ብቻ ሳይሆን ዋናው መመለስ ያለበት ጥያቄ ” ይሄ እጅግ አስከፊ የአንድ ጎሳ ባንቱስታይዜሽን እንደት ሊስተካከል ይችላል?” የሚለው ነው።

እኔ የማምንበት መፍትሄ

አለማችንን የአንድ ሺህ አመታት ታሪክ ያጠኑት የስታምፎርድ ዩኒቨርሲቲው ፕሮፌሰር ዋልተር ሺዴል ያቀረበው የተዛባና አድሎአዊ የኢኮኖሚ ፍትህና፣ ፖለቲካዊ ቀያሪ መዘውሮች ናቸው።

ፕሮፌሰሩ እንዳረጋገጠው እንደዚህ ያለ ስር የሰደደ አድሏዊ ስርአት የሚያስተካክሉት:-

1~ ጦርነት
2~ አብዮትና ፖለቲካዊ ለውጥ፣
3~ የመንግስት መፍረስ
4 ~ ወረርሽኝና በሽታ ናቸው ይላል ( 4ኛውን እኔ አላምንበትም)

እነዚህ ነገሮች ነባራዊውን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ስርአት በመቀየር በአለም ማህበረሰብ እኩልነት ያሰፍናሉ ብሏል።

ኢትዮጵያም ውስጥ እንደ ወያኔ ያለውን ይሉኝታ ቢስ ለአንድ ጎሳ የቆመ ስርአት የምትገላገለው በጥገናዊ ለውጥ ሳይሆን ከላይ ፕሮፌሰሩ ባስቀመጡት የስር ነቀል ለውጥ መሳሪያዎች ብቻ ነው።
 
============000===========

ከላይ ሁኔታው ይኽ ቢሆንም፡ በተሳከረ ክህደት ነገሩን በዳንኤል ብርሃኔና ጓደኞቹ አማካይነት በፌስ ቡክ ዘመቻ ለማጣጣል እየሞከሩ ነው!
 

“ደርግ ማረኝ፣ ኢሠፓ ማረኝ፤
የወያነ ነገር ምንም አላማረኝ።”

ይቺ በ1983/4 የተለመደች ቀልድ/ጨዋታ ነበረች።

ትላንትና የአማራ ክልል ቲቪ ከደርግ ወዲህ የኤሌክትሪክ ልማት አልተሰራልንም የሚል ወሬ ሲያሰማ ትዝ አለችኝ። መንግስቱ እኮ በህይወት አለ። አንደኛቸውን ለምን አይጋብዙትም?
 

የአማራ ክልል መገናኛ ብዙሓን ቅዳሜ ባቀረበው ዘገባ መሰረት፤ ክልሉ በኤሌክትሪክ ኃይል ዘርፍ ተበድሏል።

በዘመነ-ኢሕአዴግ በአማራ ክልል የኃይል ማስራጫ ጣቢያ እምብዛም ተገንብቶ አያውቅም ሲል የክልሉን ሹመኞች ጠቅሶ ዘግቧል። የክልሉ ሹመኞችም፡- ይህንን በደል ሕዝብ ይወቅልን ሲሉ በቴሌቪዥን ጣቢያው አውጀዋል።
እናም – እንደክልሉ ባለስልጣኖች አገላለጽ – ዓመቱን ሙሉ ሲወራለት የከረመው ኢንዱስትሪ ሪቮሉሽን(revolution) ማሳካት ያልተቻለው በዚህ ምክንያት ነው። ግሩም!
እስኪ ዝርዝር መረጃ አፈላልገን የተባለው እውነት መሆን አለመሆኑን እናጣራለን።

በተለይ የቀድሞም ሆነ የአሁኑ የኤሌክትሪክ ኃይል መስሪያ ቤት ኃይል ዋና ዋና አመራሮች ብአዴን ከመሆናቸው አንጻር፤ እንዲህ ዓይነት ማዳላት እንዴት እንደተፈጸመ (ተፈጽሞ ከሆነ) ማጣራት ያስፈልገዋል።
ያ እንደተጠበቀ ሆኖ:-

አንድ ትግራዋይ የዚህ ዓይነት ስሞታ ቢያቀርብ ምላሹ ምን ይሆን ነበር?

–> የኤሌክትሪክ ኃይል ድርጅት ዋነኛ አመራሮች ብአዴን ስለሆኑ ብቻ “የግለሰቡ ስሞታ ኢላማ ብአዴን ነው” ይባላል
–> በዘርፉ ከአራቱ የኢሕአዴግ ድርጅቶች የተጠሩ ሰዎች ይሰበሰቡና ስሞታው ይቀርባል
–> የህወሓት ተወካይ ተብለው በዚያ ስብሰባ የሚቀርቡ ሰዎች “እኛ የምናውቀው ነገር የለም፣ እንዲያውም ኤሌክትሪክ ሀይል የለም ብሎ አመጽ ሊያስነሳብን ነበር” ብለው ይወሸክታሉ
–> ጉዳዩ ኤሌክትሪክ መሆኑ ቀርቶ አንድን ግለሰብ እንዴት ማጥቃት እንደሚቻል ወደ መዶለት ይወርዳል።
–> ያንንም ኢሳት ግንባር ቀደም ዜናው አድርጎ ይዘግበዋል።(የማሸማቀቅ ስትራቴጂው አካል ስለሆነ)

This is today’s Ethiopia.
 

Comments; More comments; Further comments
 

አያሌ ግለሰቦች አስተያየቶቻቸውን መሠጥታቸውን የገጹ አዘጋጆች አሳውቀዋል። ምላሾቹም በትግራዊና በሌሎች ኢትዮጵያውያን የተከፈለ መሆኑን በግልጽ መምልከት ይቻላል።

በወቅቱ ኢትዮጵያ ውስጥ በመንግሥት ስም መልስ የሚሠጠው ዳንኤል የመሆኑ አሳፋሪነት እንደተጠበቀ ሆኖ፡ ብ፡ልግናና ስድቡ ግን ኢትዮጳይ የትግራይ ቅኝ ግዛት መሆኗን የሚያናገር በመሆኑ፡ እኔም የሚከተለውን አስተያየቴን እንደሚከተለው ለመሰጠት ተገዳጃለሁ፦

“አማሮች አሁን ይህን ማውራት ከጀመራችሁ፣ ትንሽ ቆይታችሁ ትግራይ ውስጥ ከሚደረገው የለውጥና የልማት እንቅስቃሴ ጋር ራሳቸውን ያወዳድሩና ችግሩ ይከራል የሚል ሥጋት ያደረበት ይመስላል ዳንኤል ብርሃነ!

የሚገርመኝ ግን አንተን ሳይመችህ ሲቀር ሕወሃት ድርጅትህን ለመውቀስ የምትሞክር ለመስል አንዳንድ ማዘናጊይ ትጥላለህ!

እኔ እንደሚታየኝ ከሆነ፡ ከእኔ በስተቀር ሌላው ምንም ማለት አይችልም ብለህ፡ ሲያሰኝህ በምትሠነዝራቸው ሃገርና ሕዝብ ከፋፋይ አንዳንዲም አዋራጅ መልሶችህና ማሾፍህ የብዙ ዜጎችን ልብ እንዳቃጠልክ አልታየህ እንደሆነ ይታይህ! — In this Ethiopia of unequal nations, nationalities and individuals, the TPLF has created!

በአንድ በኩል በደኅንነት ውስጥ፣ በሌላ በኩል ደግሞ በመንግሥት አመራር ቁንጮ ውስጥ ወጭ ገቢ ሆነህ፣ ዛሬ አንተ ሌላው የኢትዮጵያ ሕዝብ የምትንበሸበሽበትን ነጻነት እንደሌለው አንተም አይጠፋህም!

ይህንንም አንተ በጥበብህ፡ ሃገሪቷ ካረረባት የውጭ ምንዛሪ እጅግ ውድ በሆነ መንገድ ይበልጥ ዋጋ ሠጥተህ ዙሪያህ ባሰባሰብካቸው አንዳንድ ኢትዮጵያውያንና የውጭ ዜጎች ለጥቅምህ ስታሽከረክር (ባለህ የሥልጣን ቅርርብ ምክንያት) ሰው አልገባውም ብለህ ከሆነ እንደልብህ ሁሉንም የምትዘልፈው እጅግ ተሳስተሃል!
 

%d bloggers like this: