በመብራትና ኃይል ሥርጭት ሕወሃት ኢትዮጵያ ውስጥ የሚፈጽመው ዘረኝነት፡ደባና ጠላትነት ሃገራችንን ጎድቷል!

20 Jul


 

ከአዘጋጁ፡

ዳንኤል ብርሃነ ትክክል ነው!

ይህንን ከአማራ ቴሌቪዥን የተገኝውን ዜና አማራው ብአዴን (ትግራዊ ያልሆነው ማለቱ ነው) ያጋለጠውን “…ኢሳት ግንባር ቀደም ዜናው አድርጎ ይዘግበዋል (የማሸማቀቅ ስትራቴጂው አካል ስለሆነ” ብሎ ነበር። ያለው ሆኖ ይኸው ኢሣትም እንደተባለው ከዚህ በታች በሠፈረው ውይይት ዳታ ላይ ጭምር ተመሥርቶ እውነታውን አጣጥሞ አቅርቦታል።

ምሥጢር አይደለም፡ ከቤተሰቤ ጋር ገጠር ዕረፍት ላይ ሆነን፣ እኔ የመኝታ ክፍሉን በር ዘግቼ የልውውጣቸው ተቋዳሽ በመሆኔ በጣም ተደስቻለሁ። ለዚህም ኤርምያስንና ምናላቸውን እጅግ አመስግናለሁ።
========000========

ታዲያ ርሃብና ድህነት በተንሰራፋባት ኢትዮጵያ፣ ሕውሃት በየዓመቱ በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠር የታክስ ከፋዩን ገንዘብ ኢሣትን ለማፍረስ ቢረባረብ ምን ያስገርማል?

ከሁሉ የሚያስገርሙኝና የሚያሳዝኑኝ ግን፡ ከኢትዮጵያውያኖች ጠላት ከሆነው ሕወሃት ላይ ትግልና ፍልሚያቸውን ከማተኮር ይልቅ፡ በየአካባቢያችን ጸረ-ሕወሃት በሆኑት ላይ ያዞሩት፣ ከሕይወት ልምድና ትምህርት የቀሰሙት ዕርባና ያልሆናቸው በአማራ ስም ራሳቸውን ለአማራ ቆመናል የሚሉ ግን የአማራን የወደፊት ዕድል ብቻ ሣይሆን ያለፈውን ታሪኩና በታሪክ ያለውን ሥፍራ የሚያበላሹት አማሮች መሆናቸው ሊታወቅ ይገባል።!

እነዚህን ግለሰቦች ነው Joseph-Marie de Maistre (1753-1821) የተባለው የፈረንሣይ ፈላስፋ፣ የሕግ ምሁር፣ ጸሃፊና ዲፕሎማት ስለእነዚህ ዐይነት ግለሰቦች “Every nation gets the government it deserves” የሚለውን የምወደውን አባባሉን እንደገና አንዳስብበት አድርጎኛል። እንደነዚህ ዐይነት ግለሰቦች ናቸው ለሕወሃት ‘መንግሥትነት’ መሠረት የሆኑት እንጂ የኢትዮጵያ ሕዝብ በሙሉ አይደለም!
=======000==========

የሕወሃቱ ዳንኤል ብርሃነ ሐምሌ 9 ቀን 2009 (July 16/2017) ለዚህ በአማራ ቴሌቪዥን የቀረበው የኤሌክትሪክ ልማት አልተሰራልንም ኃይል ቅሬታ ያቀረበው አሣፋሪ መልስ:

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)
 

“ደርግ ማረኝ፣ ኢሠፓ ማረኝ፤ የወያነ ነገር ምንም አላማረኝ።”

“ይቺ በ1983/4 የተለመደች ቀልድ/ጨዋታ ነበረች።

ትላንትና የአማራ ክልል ቲቪ ከደርግ ወዲህ የኤሌክትሪክ ልማት አልተሰራልንም የሚል ወሬ ሲያሰማ ትዝ አለችኝ።

መንግስቱ እኮ በህይወት አለ። አንደኛቸውን ለምን አይጋብዙትም?

የአማራ ክልል መገናኛ ብዙሓን ቅዳሜ ባቀረበው ዘገባ መሰረት፤ ክልሉ በኤሌክትሪክ ኃይል ዘርፍ ተበድሏል።

በዘመነ-ኢሕአዴግ በአማራ ክልል የኃይል ማስራጫ ጣቢያ እምብዛም ተገንብቶ አያውቅም ሲል የክልሉን ሹመኞች ጠቅሶ ዘግቧል። የክልሉ ሹመኞችም፡- ይህንን በደል ሕዝብ ይወቅልን ሲሉ በቴሌቪዥን ጣቢያው አውጀዋል።

እናም – እንደክልሉ ባለስልጣኖች አገላለጽ – ዓመቱን ሙሉ ሲወራለት የከረመው ኢንዱስትሪ ሪቮሉሽን(revolution) ማሳካት ያልተቻለው በዚህ ምክንያት ነው።

ግሩም!

እስኪ ዝርዝር መረጃ አፈላልገን የተባለው እውነት መሆን አለመሆኑን እናጣራለን።

በተለይ የቀድሞም ሆነ የአሁኑ የኤሌክትሪክ ኃይል መስሪያ ቤት ኃይል ዋና ዋና አመራሮች ብአዴን ከመሆናቸው አንጻር፤ እንዲህ ዓይነት ማዳላት እንዴት እንደተፈጸመ (ተፈጽሞ ከሆነ) ማጣራት ያስፈልገዋል።
ያ እንደተጠበቀ ሆኖ:-

አንድ ትግራዋይ የዚህ ዓይነት ስሞታ ቢያቀርብ ምላሹ ምን ይሆን ነበር?

  –> የኤሌክትሪክ ኃይል ድርጅት ዋነኛ አመራሮች ብአዴን ስለሆኑ ብቻ “የግለሰቡ ስሞታ ኢላማ ብአዴን ነው” ይባላል
  –> በዘርፉ ከአራቱ የኢሕአዴግ ድርጅቶች የተጠሩ ሰዎች ይሰበሰቡና ስሞታው ይቀርባል
  –> የህወሓት ተወካይ ተብለው በዚያ ስብሰባ የሚቀርቡ ሰዎች “እኛ የምናውቀው ነገር የለም፣ እንዲያውም ኤሌክትሪክ ሀይል የለም ብሎ አመጽ ሊያስነሳብን ነበር” ብለው ይወሸክታሉ
  –> ጉዳዩ ኤሌክትሪክ መሆኑ ቀርቶ አንድን ግለሰብ እንዴት ማጥቃት እንደሚቻል ወደ መዶለት ይወርዳል።
  –> ያንንም ኢሳት ግንባር ቀደም ዜናው አድርጎ ይዘግበዋል።(የማሸማቀቅ ስትራቴጂው አካል ስለሆነ)

This is today’s Ethiopia!”
 

ዳንኤል ትክክል ነው! ይህቺ ዛሬ ሕወሃት እየረጋገጣት የእነርሱ ሰዎች ብቻ እንደ ዳንኤል ዐይነቶቹ ተጠቃሚ የሆኑባት፡ ከሌሎች ዜጎች የበለጠ ነጻነትና ምቾት የተሠጣቸው ኢትዮጵያ መሆኗ የሚካድ አይደለም።

በሌላ አባባል ዳንኤል ሕወሃታዊ ትግሬዎች ብቻ ነጻና ተጠቃሚ የሆኑባት ኢትዮጵያ ናት ማለቱ ከሆነ ትክክል ነው! በዚህ አባባሉ — ሕወሃትን ከውስጥ በማጋለጥ — ትልቅ ውለታ ውሎልናል ማለት ነው።

ይህ ከሆነ ዘንዳ የኛ የሁላችን ያልሆነች የጋራ እኩልነትና ነጻነት የማታካፍል ኢትዮጵያን የእነርሱ ብቻ ስላዳደረጓት በዚህ እንዳትቀጥል ማሰናከሉ በሰብዓዊነት፡ በሃይማኖት፡ በባህልና በፖለቲካም ተቀባይነት ያለው እርምጃ መሆኑን አምንበታለሁ!

ኢትዮጵያውያን ነን የሚሉ ሁሉ በዚህ እንዲያምኑና ሕውሃትን ለማፈራረስ የሚደረገውን ትግል አጽንተው እንዲቀላቀሉና እንዲታገሉ አጥብቄ እመከራለሁ!

ይህ እንደዘመናችን የአድዋ ጦርነት ተደርጎ ቢወሰድ፡ ቀደምት አያቶቻችንን የነጻነት አፍቃሪነት ታሪክና ባህል በክብር የሚደግም ተደርጎ ሊታይ ይገባዋል!

በወቅቱ እንደሌሎች ኢትዮጵያውያን ሁሉ፡ የሕወሃቱ ካድሬ ዳንኤል ብርሃነ አጻጻፍ እንደ ኢትዮጵያዊነቴ ስላልተስማማኝ የሚከተለውን መልስ በገጹ ላይ ስጥቸዋለሁ። ነገር ግን
ዳንኤል ብርሃነ የጻፍኩትን ስለሠወረው፡ አንባብያን ከዚህ ሥር ሊያነቡት ይችላሉ:

  “አማሮች አሁን ይህን ማውራት ከጀመራችሁ፣ ትንሽ ቆይታችሁ ትግራይ ውስጥ ከሚደረገው የለውጥና የልማት እንቅስቃሴ ጋር ራሳቸውን ያወዳድሩና ችግሩ ይከራል የሚል ሥጋት ያደረበት ይመስላል ዳንኤል ብርሃነ!

  የሚገርመኝ ግን አንተን ሳይመችህ ሲቀር ሕወሃት ድርጅትህን ለመውቀስ የምትሞክር ለመስል አንዳንድ ማዘናጊይ ትጥላለህ!

  እኔ እንደሚታየኝ ከሆነ፡ ከእኔ በስተቀር ሌላው [ኢትዮጵያዊ] ምንም ማለት አይችልም ብለህ፡ ሲያሰኝህ በምትሠነዝራቸው ሃገርና ሕዝብ ከፋፋይ አንዳንዲም አዋራጅ መልሶችህና ማሾፍህ የብዙ ዜጎችን ልብ እንዳቃጠልክ አልታየህ እንደሆነ ይታይህ! — In this Ethiopia of unequal nations, nationalities and individuals, the TPLF has created!

  በአንድ በኩል በደኅንነት ውስጥ፣ በሌላ በኩል ደግሞ በመንግሥት አመራር ቁንጮ ውስጥ ወጭ ገቢ ሆነህ፣ ዛሬ አንተ ሌላው የኢትዮጵያ ሕዝብ የምትንበሸበሽበትን ነጻነት እንደሌለው አንተም አይጠፋህም!

  ይህንንም አንተ በጥበብህ፡ ሃገሪቷ ካረረባት የውጭ ምንዛሪ እጅግ ውድ በሆነ መንገድ ይበልጥ ዋጋ ሠጥተህ ዙሪያህ ባሰባሰብካቸው አንዳንድ ኢትዮጵያውያንና የውጭ ዜጎች ለጥቅምህ ስታሽከረክር (ባለህ የሥልጣን ቅርርብ ምክንያት) ሰው አልገባውም ብለህ ከሆነ እንደልብህ ሁሉንም የምትዘልፈው እጅግ ተሳስተሃል!

 

ተዛማጅ፡

ትግረኛ ተናጋሪው የሕወሃት ክንፍ ብአዴን ላለፉት 26 ዓመታት የአማራ ሕዝብ ሲናገር የነበረውን መራራ ሐቅ አወጣ!
 

%d bloggers like this: