የሕወሃት አስተዳደርን የሕዝቡ ቁጣ በአነስተኛ ንግድ ላይ የተጫነውን አዲስ ግብር እንዲሠርዝ በማስገደድ ነጋዴዎች ራሳቸው ያመኑበትን እንዲከፍሉ ተወሰነ!

23 Jul

የአዘጋጁ አስተያየት:

    ይህ ለጊዜው ሕወሃት የንጹሃንን ደም እንዳያፈስ ስላደረገው መልካም እርምጃ ነው!

    ለወደፊቱ ግን በገንዘብ ስግግብግብነቱ የሚታወቀው ሕወሃት ከሕዝብ ጋር ምክክር ማለት የፕሮፓጋንዳ ፍጆታ ወይንም የማሸነፍ ፉክክር ሳይሆን፡ እንደምክክር መውሰድን መጀመሪያ መማር ይኖርበታል — ለወደፊቱ የሚባል ነገር ካለ!

    ከበደ ጫኔ ስለዜግነት ግዴታና ኃላፊነት በሕወሃት ስም መናገሩ አሳፋሪ ነው! ነፍሰ ገዳዩ ሕወሃት ነው የዜግነት ግዴታን ለሕዛብችን የሚያስተምረው? እባካችሁ! የምትወረውሯቸውን ተሳዳቢ፡ ተመጻዳቂና ጸያፍ ቃላት ሕዝባችን ላይ ከመወርወራችሁ በፊት እራሳችሁን እወቁ!

    አሁን በደረሰበት ደረጃ፣ ለሕወሃት ዘራፊና ዘረኛ አስተዳደር ት ዕግሥቱ ተሟጧል!

 

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)
በሪፖርተር
 
ከሰኔ ወር መጨረሻ 2009 ዓ.ም. ጀምሮ በኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ሠራተኞች ተግባራዊ የተደረገው የቀን ገቢ ግምት፣ በተለይ በአነስተኛ ንግድ ሥራ ላይ የተሰማሩ ነጋዴዎች ከፍተኛ ቅሬታ በማቅረባቸው ሳቢያ ራሳቸው ያመኑትን እንዲከፍሉ ውሳኔ ላይ መደረሱ ተገለጸ፡፡

ሪፖርተር ያነጋገራቸው በሚኒስትር ማዕረግ የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ከበደ ጫኔ እንደተናገሩት፣ እነዚህ የኅብረተሰብ ክፍሎች ራሳቸውን ችለውና በልተው ካደሩ፣ ለመንግሥት ሸክም ማቃለል ነው፡፡ ምክንያቱ ደግሞ መንግሥት ዜጎች በልተው፣ ጠጥተውና ራሳቸውን ችለው እንዲኖሩ የማድረግ ግዴታ ስላለበት ነው ብለዋል፡፡

በዝቅተኛና አነስተኛ የንግድ ሥራ ላይ በተሰማሩ የንግዱ ማኅበረሰብ አባላት ላይ የተወሰነ ግምት ከፍተኛ ቁጣ ማስነሳቱን፣ “ራሳቸው በልተው ካደሩ በቂ ነው፣ ለምንድነው በእነሱ ላይ ይህንን ያህል ግምት የተጫነው፤” የሚሉ ተደጋጋሚ ስሞታዎችን ከኅብረተሰቡ መቅረቡን አቶ ከበደ አስረድተዋል፡፡

በመሆኑም በጀበና ቡና፣ በጉልት ንግድ፣ በፀጉር ሥራ፣ በልብስ ስፌት፣ ፑል በማጫወትና በሌሎች ጥቃቅንና አነስተኛ ሥራዎች ላይ ተሰማርተው የሚገኙ ኅብረተሰብ ክፍሎች እነሱ ያመኑበትን እንዲከፍሉ ውሳኔ ላይ መደረሱን አቶ ከበደ አረጋግጠዋል፡፡ ያላግባብ ግምት የተጣለባቸው ካሉ እንዲነሳላቸውም ቅሬታቸው እየታየ መሆኑንም አክለዋል፡፡

ነገር ግን ትንሽም ቢሆን ከሚያገኙት ገቢ በራሳቸው እምነት በመክፈል ወደ ታክስ ሥርዓቱ በመግባት፣ የዜግነታቸውን ድርሻቸውን መወጣት እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡
 

%d bloggers like this: