“የፍትህ ያለህ!” ያስባሉ የፓርላማ ኦዲት ሪፖርቶች በባለሙያዎች እይታ

26 Jul
    “ተሻሻለ ሲባል በግብርና ታክስ ክፍያ ላይ እንደሚታየው የአስተዳደሩ ገቢ ማዝቀጥ — ሕዝቡ ባመቸው መንገድ ሕወሃትን ገቢ ለመንፈግ የተቻለውን እንደሚሞክር ያሳያል።”
     
    ሰኔ 21/2017 ትልቁ የኢትዮጵያ ‘ፌደራል’ በጀት ድክመቱ፣ገጽታዎቹና ውስብስብ ችግሮቹ

 
Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)
VOA (Amharic)
 

“በዚህ በኩል ግብር እየሰበሰቡ በሌላ በኩል ጎደለ ማለት በሀገሪቱ ተጠያቂነት ያለበት አሠራር አለመኖሩን ማሳያ ነው” ብለዋል።


 
የፌዴራል ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤትና የክልል ጠቅላይ ኦዲተር መሥሪያ ቤቶች የመንግሥት በጀት አጠቃቀምን በተመለከተ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሚያቀርቡት ዓመታዊ ሪፖርት፤ በቢሊዮን የሚቆጠር የገንዘብ ጉድለት፣ ያልተወራረደ የሒሳብ ሰነድ መኖርና ገንዘቡ ለታቀደለት ሥራ ያለመዋሉን የሚያሳዩ ተደጋጋሚ ሪፖርቶችን ያቀርባል።

በቅርቡም የወጡት ሪፖርቶች የሚያሳዩት ይህንኑ ነው። ጉድለቱን ይፋ በሚያደርግበት ጊዜም ዐቃቤ ሕግ ወይም ፀረ ሙስና ኮሚሽን በጉዳዩ ገብቶ እንዲያጣራም ምክረ ሐሳብ ይለግሳል።

በዚሁ ጉዳይ ላይ ያነጋገርናቸው ሁለት ምሑራን ግን የመሥሪያ ቤቱ የጉድለት ሪፖርት ከዓመት ዓመት እየጨመረ ከመምጣት ውጪ በጉድለቱ የተጠየቀ አካል አላየንም ይላሉ። “በዚህ በኩል ግብር እየሰበሰቡ በሌላ በኩል ጎደለ ማለት በሀገሪቱ ተጠያቂነት ያለበት አሠራር አለመኖሩን ማሳያ ነው” ብለዋል።
 

ተዛማጅ፡

    ትልቁ የኢትዮጵያ ‘ፌደራል’ በጀት ድክመቱ፣ገጽታዎቹና ውስብስብ ችግሮቹ

    ድንገተኛ የገንዘብ ሚኒስትሩ ትውስታ? የግብር ገቢ አሰባሰብና የወጪ ንግድ አፈጻጸም ዝቅተኛነት የ2010 በጀትን ለማሳካት እንደሚያዳግት የገንዘብ ሚ/ሩ ዶክተር አብርሃም ተከስተ አመኑ!

 

%d bloggers like this: