የሕወሃት ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ በፖሊስ ረዳት ኮሚሽነር ሐጎስ መራ ትኩዕ ላይ የመሠረተውን ክስ ለምን አነሳ?

14 Aug

የአዘጋጁ አስተያየት:
 

  ግልጽ ለመሆን፡ ከላይ በአርዕስቱ ለተነሳው ጥያቄ በመረጃ ተደግፎ ያገኘነው መልስ የለም። ነገር ግን ላለመሆን የሚችልበትን ምክንያትም ማየት አልቻልንም!

  እስከዛሬ በሃገራችን ውስጥ ሕወሃት ሲያደረግ ያየነው በዘርና በዘወግ የራሱን ሰዎች ደግፎ የመጠቃቀሙን አስጸያፊ የፖለቲካና የኤኮኖሚ አሠራር ባህሉ ስላደረገው፡ ኮምሽነር ሃጎሥ ከተመሠረተባቸው ክስ — ለብሄረሰባቸው ኢትዮጵያ ውስጥ ሕወሃት ‘በደነገገለት’ የበላይነት ምክንያት — ክሱ ቢነሳላቸው — መደረግ የሌለበት ቢሆንም — አዲስና ሕወሃት የማያደርገው ነገር መሆኑን የሜጠቁም ነገርም አልታየንም!

  ትምህርት ኖራቸው አልኖራቸው፣ ከማዘዝ ውጭ (ለዚያውም ማዘዝ የሚያውቁ ሆነው) ሌሎች ሠራተኞችን የማስተባበርና የመምራት ችሎታ አላቸው ሳይባል አይደል እንዴ ላይ እስካሉት ጭምር፡ ሃገሪቱን እንዲመሩ፡ሕወሃቶች ለእያንዳንዱ የመንግሥት መ/ቤት ከላይ እስከታች ኃላፊዎች ሊሆኑ የበቁት?

  የዚያን ምርት አየነው፤ ግራ የገባው አመራር ሃገራችንን ግራ አጋብቶ፣ የደነዘዘ ኅሊናቸው መፍትሂ አስመስሎ እንዲቀበሉት ያደረጋቸው ዋናው ነገር — ወገኖቻችንን እየሰበሰቡ ማሠር፣ መግደል፣ ቶርች ማድረግ አይደል እንዴ የሕወሃቶች ሙያ?

  ታዲያ የትኛው የሕወሃት ኅሊና ነው፣ ትግራዊው የሕወሃቱን አባል ትግራዊው ጠቃላይ አቃቤ ሕግ የፖሊስ ረዳት ኮሚሽነር ሐጎስ መራ ትኩዕ ላይ የተመሠረተውን ክስ ትክክል ነው ብሎ የሚቀበለው?

  ሕጉን የሚለውን ወደ ጎን እንተወው! እስካሁን ሕጉ ብዙ ነገር እያለም ሕዝባችን ተገፍቷል፡ ተረግጧል፡ ተግዟል፡ ከመሬት ንብረቱ ተገፍቷል፣ ተገድሏል፣ ተሰዷል፣ በባሕሮች በተደጋጋሚ ተበልቷል፣ ሰብዓዊነቱን ተነጥቋል።

  ይህ ሁሉ ሲሆን እያዩ እኮ ነው፣ ቄሱም፣ ሼኩም፣ መጽሕፍቱም፣ መናፍስቱም የእነርሱው ሆነውበት፣ ሕጉ ግራ ተጋብቶ ወረቀት ላይ የሠፈረ በድን ምሥል ሆኖ የቀረው!

  ታዲያ አሁን፣ ወቅቱ ደርሶ የወያኔ ቁስል በመላ ሃገሪቱ ክፉኛ ማመርቅዝ ላይ ነው መሰለኝ፡ ዛሬ ባሕር ዳር ፍርድ ቤት የአማራ ባለሃብቶችን — ኢሣት ሁለት መቶ ያህል አለ ለበል — ሰብስቦ አሥሮ ከከረመ በኋላ፣ የሕግ ምንነትን ጠንቅቀው የሚያውቁ ሴት ዳኛ፣ ፖሊስ በታክስ ስም አድማ አካሂደዋል ብሎ “ወንጀለኞቹን” ሲያቀርብላቸው፣ የንግድ በራቸውን መዝጋት ሕጉ የሚፈቅድላቸው ስለሆነ፣ ይልቁንስ ወንጀላቸውን ለምን አትነግረኝም ብለው በሕወሃቶችና አጫፋሪዎቻቸው ላይ ሰማይ ምድሩን እንደ ደባላለቁባቸው የተነገረው!

=====================
 

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)
በሪፖርተር
 
የቀረበላቸውን ሐሰተኛ የፍርድ ቤት መያዣን ትክክለኛ መሆን አለመሆኑን ሳያረጋግጡ ትዕዛዝ በመስጠት አንድ ግለሰብ እንዲታሰር አድርገዋል የተባሉት፣ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ባልደረባ ረዳት ኮሚሽነር ሐጎስ መራ ትኩዕ ላይ የተመሠረተው የሙስና ክስ ተነሳ፡፡

የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ በረዳት ኮሚሽነር ሐጎስ ላይ ያቀረበው ክስ የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምርያ ኃላፊ ሆነው ሲሠሩ፣ ከየካቲት 15 እስከ 28 ቀን 2008 ዓ.ም. ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ በሐሰተኛ የፍርድ ቤት ሰነድ የቀረበን ግለሰብ እንዲታሰር ትዕዛዝ ሰጥተዋል በማለት ነው፡፡

ዓቃቤ ሕግ ባደረገው ተጨማሪ ምርመራ ረዳት ኮሚሽነሩ በድርጊቱ ያላቸው ተሳትፎ ተጨባጭ ባለመሆኑ ክሱን ማንሳቱ ታውቋል፡፡ ነገር ግን ከረዳት ኮሚሽነር ሐጎስ በታች ያሉ የጣቢያው ኃላፊ ኮማንደር ግርማ ሰንበቶና ሌሎች በክሱ ከተካተቱ ግለሰቦች ጋር ድርጊቱን ፈጽመዋል በማለት ዓቃቢ ሕግ ክሱን ቀጥሏል፡፡

ዓቃቤ ሕግ የረዳት ኮሚሽነር ሐጎስን ክስ ማቋረጡን ሐምሌ 21 ቀን 2009 ዓ.ም. በተጻፈ ደብዳቤ መግለጹን ፍርድ ቤቱ ገልጾ ክሳቸውን አቋርጧል፡፡ ረዳት ኮሚሽነር ሐጎስ ከእስር ተለቀው መደበኛ ሥራቸውን መጀመራቸው ታውቋል፡፡ ረዳት ኮሚሽነር ሐጎስ በአሁኑ ጊዜ የየካ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምርያ ኃላፊ ሆነው እየሠሩ ናቸው፡፡
 

%d bloggers like this: