የአማራን መሬቶች የትግራይ ለማድረግ ቂሎ በሆነ መንገድ ልማደኛው የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የአማራና ቅማንት ማኅበረሰብ ተቀላቅለው በሚኖሩባቸው 12 ቀበሌዎች ሕዝበ ውሳኔ ለማካሄድ እየተዘጋጀ ነው

17 Aug

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)
 
አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 11፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአማራና ቅማንት ማህበረሰብ ተወላጆች ተቀላቅለው በሚኖሩባቸው 12 ቀበሌዎች ህዝበ ውሳኔ ላማካሄድ ዝግጅት እያደረገ መሆኑን የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ገለፀ፡፡

ህዝበ ውሳኔው የሚካሄደው የፌድሬሽን ምክር ቤት ጉዳዩን ተመልክቶ ባሳለፈው ውሳኔ መሰረት መሆኑን ቦርዱ አስታውቋል።

የአማራ ክልል ካቢኔ ሰሞኑን የቅማንት ማህበረሰብ የራሱ አስተዳደር እንዲኖረው ስምምነት ላይ መድረሱ ይታወሳል።

ይህንን ተከትሎም የአስተዳደር ወሰን ለማካለል የአማራና ቅማንት ብሄረሰብ ተወላጆች እንደ ምርጫቸው፥ በፈለጉት አስተዳደር ስር እንዲሆኑ ህዝበ ውሳኔ መዘጋጀቱም ተነግሯል።

ህዝበ ውሳኔውን የማስፈፀም ሃላፊነት የተሰጠው ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ወደ ቀበሌዎቹ የቴክኒክ ቡድን መላኩን፥ የቦርዱ ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ተስፋ ዓለም አባይ ተናግረዋል።

የህዝበ ውሳኔው ማካሄጃ ጊዚያዊ መርሃ ግብር የተዘጋጀ ሲሆን፥ በቦርዱ እና በክልሉ መንግስት ተመክሮበታል።

መርሃ ግብሩን በቅርቡ አፅድቆ ይፋ እንደሚያደረግ ያሳወቀው ምርጫ ቦርድ፥ በህዝበ ውሳኔው እስከ 25 ሺህ ዜጎች ይሳተፋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅም አመላክቷል፡፡
 

ተዛማጅ:

    ተነስ ጎበዝ! ተነሽ ጓዴ ለሃገራችን እንዋደቅ! ወንበዴው ሕወሃት ሃገራችንን አደጋ ላይ ጥሏል!

    “የወያኔን የውስጥ ሽኩቻ አትመኑ”! ወልቃይቴዋ ታጋይ እርስቴ የወያኔን ማንነት በአዜብ ጎላና ወዘተ ከንቱነት ታጋልጣለች!

    በኢትዮጵያ ያለው የህዝብ በደልና የፍትህ እጦት በሽምግልና የሚፈታ አይደልም

 

%d bloggers like this: