በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በመንገድና ስኳር ፕሮጀክቶች ኤች አይ ቪ በከፍተኛ ሁኔታ እየተሰራጨ ነው ተባለ!

3 Sep

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)
 
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 27፣ 2009 (ኤፍ ቢ ሲ) ኤች አይ ቪ/ኤድስ በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት፣ በመንገድና ስኳር ፕሮጀክቶች በስፋት እየተሰራጨ መሆኑን የፌደራል ኤች አይ ቪ/ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ ጽህፈት ቤት አስታወቀ።

የጽህፈት ቤቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ አብርሃም ገብረመድህን እንደገለጹት፥ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አካባቢ ለቫይረሱ የሚያጋልጡ ሁኔታዎች እየተበራከቱ ነው።

ሴተኛ አዳሪዎችና ወጣቶች በሚበዙባቸው የመንገድና ስኳር ፕሮጀክቶች የቫይረሱ ስርጭት ከፍ ባለ ደረጃ የሚገኝባቸው መሆኑን ተናግረው፥ በገጠርም ባልተለመደ ሁኔታ እየተስፋፋ ነው ብለዋል።

አቶ አብርሃም ቫይረሱን በመከላከልና በመቆጣጠር ላይ የሚሰሩ በተለይም ገንዘብ ሲገኝ የሚሰሩ ሲጠፋ ደግሞ የሚያቆሙ በአጠቃላይ ሥራውን የዘነጉ አስፈፃሚ ተቋማት፥ በመኖራቸው በየደረጃው ያሉት የህዝብ ተወካይ ምክር ቤቶች ሊከታተሏቸው ይገባል ብለዋል።

ቫይረሱ እያደረሰ ያለው ጉዳት ዘርፈ ብዙ በመሆኑ ምላሹም ዘርፈ ብዙ እንዲሆን ተቋማት በቅንጅት እንዲሰሩ ነው የጠየቁት
የመንግስት አስፈጻሚ አካላትና ተቋማት ኤች አይ ቪ/ኤድስን የሥራቸው አካል ሳይሆን፥ ከሥራቸው ዋና ዋና ተግባራት አንዱ እንዲያደርጉትም አሳስበዋል።
 

Related:

 

%d bloggers like this: