TPLF Ethnicities: ሕወሃት ለምን ይሆን ገና ከንጋቱ የእያንዳንዱ ዜጋ ዘር በመታወቂያ ካርዱ/ዷ ላይ እንዲጻፍ በሕግ ያስገደደው? ከሶማሌ ክልል ጋር ሕወሃት ያለው ግንኙነት መሠረቱ ምንም ምሥጢር ስላልሆነ ከሕወሃት ካድሬዎችና መኮንኖች ተገንዘቡ!

16 Sep

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)
 

 


 

የአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ መምህር አንማው አንተነህን ያዳምጡ!

ይህ የአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ መምህር አንማው አንተነህ ይባላል ። መምህር አንማው ከምርጫ 97 ከመካሄዱ 3 ዓመት በፊት ፣ ሟች መለሰ ዜናዊ ከአዲስ አበባ ዪንቨርስቲ መምህሮች ጋር ባደረጉት ውይይት ላይ በመገኘት ይህን አስገራሚ ንግግር አድርጎ ነበር ። መምህር አንማው የተናገረው በአቶ መለስ ዜናዊና በአበሮቻቸው በቀኝ ጆሮ ገብቶ በግራ ባይፈስ ኖሮ ዛሬ ላይ ባልደረስን ነበር ።

አቶ መለስ እና አበሮቻቸው ጫካ ሲገቡ ዓላማቸው ትግራይን ነፃ ለማውጣት ነበር ። የትግራይ ነፃ አውጪ ብለው ሲንቀሳቀሱ ከቆዩ በኋላ በመጨረሻም ተሳክቶላቸው ትግራይን አይደለም ኢትዮጵያን ሊቆጣጠሩ በቅተዋል። ይሁንና ቅንነት ስለሌለ፣ ጫካ አቅደው የመጡትን በተግባር በማዋል ኢትዮጵያን እና ኢትዮጵያውያንን ማጥፋታቸውን ተያይዘውታል።

ብዙ የተማሩ ልጆች ያሏት ሀገር በመሀይም እየተገዛች ገደል አፋፍ ደርሳለች ። መምህር አንማው የተናገረው ቃል በቃል በተግባር ተፈጽሞ እያየን ነው ።
 
ኢሳት (ሰኔ 23 ፥ 2008) በቅርቡ በሶማሊያ ክልል በሚገኘው የጃማ ዱባብ የገጠር መንደር አካባቢ ተቀስቅሶ ለ21 ሰዎች ሞት ምክንያት የሆነው ግጭት ዳግም ተቀሰቀሰ። አካባቢውን ከሶማሌላንድ ጋር በሚያዋስናት የድንበር አካባቢ ከሁለት ሳምንት በፊት የተቀሰቀሰው ይኸው ግጭት ጎርጎር፣ አሊ ቡራሌ እና ቦዴ ድሂር በሚባሉ ሶስት የገጠር መንደሮች መዛመቱን የሶማሊላንድ ፕሬስ ሃሙስ ነዋሪዎችን ዋቢ በማድረግ ዘግበዋል።

ከሁለት ቀን በፊት በሶማሊ ክልል ልዩ ሃይሎች እየተወሰደ ነው በተባለው በዚሁ ጥቃት ቁጥራቸው በአግባቡ ሊታወቅ ያልቻለ የአካባቢው ነዋሪዎች መሞታቸውንና ለእስር መዳረጋቸውን እማኞች ገልጸዋል።

በአካባቢው ማንነታቸው ያልታወቀ ታጣቂዎች በጸጥታ ሃይሎች ላይ የሚፈጽሙትን ጥቃት ተከትሎ በስፍራው ግጭት መቀስቀስ መጀመሩን የተናገሩት ነዋሪዎች በትንሹ ወደ 60 የሚጠጉ ሰዎች ለእስር መዳረጋቸውን አክለው አስታውቀዋል።

ኢትዮጵያ ራሷን እንደነጻ አገር አድርጋ ካወጀችው ሶማሊላንድ ጋር ጠንካራ የድንበር ንግድ ልውውጥ ያላት አገር ሲሆን፣ በአካባቢው ያለው የጸጥታ ሁኔታ በንግድ እንቅስቃሴው ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ያሳድራል ተብሎ ተሰግቷል።

ኢትዮጵያ ከሶማሊላንድ ጋር በምትዋሰንበት የድንበር አካባቢ በተደጋጋሚ የሚቀሰቀሰውን ግጭት የሶማሊላንድ ባለስልጣናት በቅርቡ ወደ አዲስ አበባ በመጓዝ በጸጥታ ጉዳዮች ዙሪያ ምክክር ማካሄዳቸው ይታወሳል። ይሁንና ጉዳዩ ዕልባት አለማግኘቱን ያስታወቁት የአካባቢው ነዋሪዎች ግጭቱ እየተባባሰ በመሄድ ላይ መሆኑን ለሶማሊላንድ መገናኛ ብዙሃን አስረድተዋል።

ከሁለት ሳምንት በፊት በዚሁ የድንበር አካባቢ ተቀስቅሶ በነበረው ግጭት በትንሹ 21 ሰዎች መሞታቸውን የተለያዩ መገናኛ ብዙሃን መዘገባቸው ይታወሳል። ከቀናት በፊት በድንበሩ አካባቢ የተቀሰቀሰን ይህንኑ አዲስ ግጭት ተከትሎ ሃውድ ተብሎ በሚጠራ የሶማሊላንድ አካባቢ የሚኖሩ በርካታ ነዋሪዎች የመኖሪያ ቀያቸውን ለቀው መሰደዳቸን ሶማሊላንድ ፕሬስ ጋዜጣ በዘገባው አስፍሯል።

በግጭቱ ዙሪያ ከኢትዮጵያ በኩል እስካሁን ድረስ የተሰጠ ምላሽ የለም።
 

ለነ ታምራት ላይኔ አ.አ ስታዲየም ታማኝ እንዲህ አለ!

  በሶማሊያ ችግር አብረን ስንጨነቅ
  በይጎዝላቢያ ቆመን ስንሳለቅ
  በእንጀራ አባታችን በሩሲያ ስንስቅ
  ከነሱ ሳንማር ካለፍነው በዋዛ
  አርባ መንግስት ሆነን ክልል ስናበዛ
  እዳንጠያየቅ ፓስፖርትና ቪዛ፡

==================
 

ተዛማጅ፡

  Prevent Genocide International:

  Group Classification on National ID Cards as a Factor in Genocide and Ethnic Cleansing

  Uneasy peace and simmering conflict: the Ethiopian town where three flags fly

  History repeating itself in the Horn of Africa: Is the crime in Darfur being replicated in Eastern, South & Southern Oromia Regional State of Ethiopia? A MUST-READ!

  Ethiopia’s Somali Region: Political Marketplace for Tigray Military Commanders

 

WHAT IS THE MOTIVE BEHIND THE TPLF CAMPAIGNS BELOW?

  Tigray Online March 8, 2017:

  The Somali State Special Police Forces (Liyuu Police) Are Gallant

  Aigaforum & Tigrai Online, March 11 & 12, 2017:


  Shedding light on the recent violence in the border areas between Somali and Oromia regions of Ethiopia

  Tigray Online January 5, 2016

  Tigrai Online chose Abdi Mohamud Omar as person of the year 2016

  Awrambatimes, August 15, 2016:

  Ethiopian Somali Region “Liyu” Police: The Savior of Its People and Beyond

*Updated
 

%d bloggers like this: