የኢሬቻ በዓል ተቃውሞ ቢሰማበትም በሰላም ተጠናቀቀ

1 Oct

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)
ቢቢሲ አማርኛ
 
የዘንድሮው ኢሬቻ በዓል ላይ መንግሥትን የሚያወግዙ ሙዚቃዎችና መፈክሮች በብዛት ቢሰሙም በዓሉ በሰላም ተጠናቋል።

ዛሬ ጠዋት በቢሾፍቱ ከተማ የጣለው ከባድ ዝናብ የበዓሉን ታዳሚ በቦታው ከመሰባሰብ አላገደውም።

አባገድዎች ከአንድ ስዓት ተኩል የእግር ጉዞ በኋላ ሆራ አርሰዴ ደርሰው ወደ መጡበት ተመልሰዋል።

በተዘጋጀውን መድረክ ላይ ከጠዋት ጀምሮ በመንግሥት በሚቃወሙ የሚያሰሙ ወጣቶች ታይተዋል ቁጥጥር ሥር ውሎ ነበር።

አባገዳዎችም ሆኑ የመንግሥት አካል በሥነ-ሥርዓቱ ላይ ንግግር አላደረጉም።

በዘንድሮው የኢሬቻ በዓል ላይ መንግሥት ምንም አይነት ድርሻ አይኖረውም መባሉ ይታወሳል።ት ምንም አይነት ድርሻ አይኖረውም መባሉ ይታወሳል።

የዘንድሮው በዓል ተቃውሞን አስተናግዷል (ከቢቢሲ አማርኛ)

በኢሬቻ በዓል ላይ የትኛውም የመንግሥት አካል ድርሻ አይኖረውም ተባለ

የበዓሉን ዝግጅት ሲያስተባብሩ የነበሩት የኦሮሚያ አባ ገዳዎች ምክር ቤት አባላትም ንግግር ሳያደርጉ ወደ መጡበት ተመልሰዋል።

የኦሮሚያ ፖሊስ በዓሉ ከሚከበርበት ሥፍራ በግምት ሁለት ኪ.ሜ ርቀት ላይ የነበረ ሲሆን፤ የቢቢሲ ዘጋቢ እናዳለው ፖሊስ የጦር መሳሪያ ሳይታጠቅ የፀጥታ ማስከበር ሥራ ሲያከናውን ነበር።

ነገር ግን በቢሾፍቱ ከተማ ውስጥ የጦር መሳሪያ የታጠቁ ፖሊሶች ታይተዋል።

በበዓሉ ላይ ለመሳተፍ ከሰበታ ከተማ የመጣው ወጣት አለሙ አረጋ “የዘንድሮ በዓል እጅግ አስደሳች ነው” ስል ለሪፖርተራችን ተናግሯል።

“የዘንድሮ በዓል ከባለፈው ዓመት በተለየ መልኩ አስደሳች እና ሰላማዊ ነው” ያለቸው ደግሞ ከሻሸመኔ የመጣችው ወጣት ሃምዚያ በሪሶ ናት።

በዘንድሮ በዓል ላይ እሰከ እኩለ ቀን ድረስ በተሳታፊዎች ላይ የደረሰ ጉዳት እንዳልታዘብ እና በአካቢቢ ላይ የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር አስቸኳይ እርዳታ ለማድረግ በተጠንቀቀ ተሰማርተው ነበረ።
 

%d bloggers like this: