የሕወሃት አባል የሆነ የወጋገን ባንክ የጥበቃ ሠራተኛ ሁለት የሕወሃት አባሎችን በመግደል ራሱን አጠፋ

4 Oct

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)
 
(ኢሳት ዜና–መስከረም 24/2010) በአዲስ አበባ ከተማ የወጋገን ባንክ የጥበቃ ሠራተኛ ሁለት ሰዎችን በመግደል ራሱን ማጥፋቱ ታወቀ።

ከዐይን ምስክሮችና ከሀገር ቤት ጋዜጦች ማረጋገጥ እንደተቻለው ድርጊቱ የተፈጸመው ዛሬ ከሰአት በኋላ ሲሆን ግለሰቡ ግድያውን ለምን እንደፈጸመና በመጨረሻም ራሱን ያጠፋበት ምክንያት አልታወቀም።

ቦሌ ኦሎምፒያ አካባቢ በሚገኘው ደምበል ሕንጻ 10ኛ ፎቅ ላይ የተፈጸመውን ግድያ በተመለከተ ዝርዝር መረጃዎችን ለግዜው ማግኘት አልተቻለም።

አንዳንድ ምንጮች እንደገለጹት ግድያውን የፈጸመው የወጋገን ባንክ የጥበቃ ሠራተኛ የሕወሃት ታጋይና በጡረታ ላይ የሚገኝ የሠራዊት አባል ሲሆን ሟቾቹም የሕወሃት ታጋዮች መሆናቸው ታውቋል።

ግለሰቡ ግድያውን የፈጸመው በግል ጸብ ይሁን በፖለቲካ ምክንያት የታወቀ ነገር የለም።

በሕወሃት ውስጥ በተፈጠረው ክፍፍል የሕወሃት ደጋፊዎች ጎራ ለይተው በመወነጃጀል ላይ መሆናቸው ይታወቃል።

ወጋገን ባንክም የሕዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ ንብረት የሆነው የኢፈርት ባንክ ንብረት መሆኑን ጸሃይ የሞቀው እውነታ ነው።
 

%d bloggers like this: