ሕወሃት የአብዲ ኦመር ኮሙኒኬሽን ቢሮ ግጭትን የሚያባብሱ መረጃዎችን ከመልቀቅ እንዲቆጠብ ጠየቀ!

9 Oct

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)
 
አዲስ አበባ ፣ መስከረም 28 ፣ 2010 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ግጭትን የሚያባብሱ መረጃዎችን ከመልቀቅ እንዲቆጠብ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት አሳሰበ።

ጽህፈት ቤቱ ትናንት ባወጣው መግለጫ ባለፈው ማክሰኞ በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል የኮሙዩኒኬሽን ማህበራዊ ትስስር ገጽ ላይ የተሰራጨው መረጃ መንግስት ያስቀመጠውን አቅጣጫ የሚቃረን ነው ብሏል።

መልዕክቱ ከኢትዮጵያ ሶማሌ ሰላም ወዳድ ህዝብ እና መንግሥት፥ እንዲሁም የፌደራል ዴሞክራሲያዊ ሥርዓቱን ከሚያራምድ ማንኛውም አመራር የማይጠበቅ እንደሆነም ነው የገለጸው።

በክልሉ ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ የወጣውን መግለጫ፥ ለኦሮሚያና ኢትዮጵያ ሶማሌ ወንድማማች ህዝቦች እንዲሁም ለሃገሪቱ ዘላቂ ሰላምና ልማት የማይጠቅም ነው ብሎታል።

ጉዳዩን በተመለከተም የሚመለከተው የመንግሥት አካል ጉዳዩን መርምሮ በቀጣይ ውሳኔ እንደሚሰጥበት ገልጿል።

ጽህፈት ቤቱ የፌደራል መንግስት የጸጥታ አካላት በወሰዱት የማረጋጋት እርምጃ ግጭቱ በቁጥጥር ስር የዋለ መሆኑንም ነው ያመለከተው።

ግጭቱን በዘላቂነት ለመፍታት፣ የተፈናቀሉ ወገኖቻችንን ለመደገፍና ለማቋቋም የተጀመረው እንቅስቃሴ ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑንም ጽህፈት ቤቱ ገልጿል።
 

ተዛማጅ:

 

%d bloggers like this: