ሙጋቤ ሹመቱን ሀገራቸው ትምባሆ አምራች ስለሆነች አይቀበሉም ነበር!

25 Oct

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)
BBC አማርኛ
 
የዚምባብዌ ፕሬዚዳንት ሮበርት ሙጋቤ የዓለም ጤና ድርጅት የበጎ ፈቃድ አምባሳደር ሹመትን አገራቸው የትምባሆ አምራች ከሚባሉ አንዷ በመሆኗ ሹመቱን ለመውሰድ በጭራሽ ፈቃደኛ እንደማይሆኑ መንግስታዊው ጋዜጣ ሄራልድ የመንግስት ቃል አቀባይ የሆኑትን ጆርጅ ቻራምባን በመጥቀስ ዘግቧል።

ሙጋቤ የሹመቱን ዜና የሰሙት በመገናኛ ብዙኃን ሲሆን በኦፊሴያላዊ ደረጃ ምንም ጥያቄ ያልቀረበ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ “ጉዳዩን አሳፋሪ ነው ” ሲሉ ጆርጅ ቻራምባ ተናግረዋል።

ዶክተር ቴድሮስ አድኃኖም የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር በመሆን ሲሾሙ የመጀመሪያው አፍሪካዊ ናቸው።

የዓለም ጤና ድርጅት ትምባሆ ላይ ግልፅ አቋም ያለው ሲሆን ሙጋቤም ከአገሪቷ ብሔራዊ ፍላጎት ጋር የማይጣጣም ዘመቻን በመከተል ዋነኛ የገንዘብ ምንጭ የሆነውን ትምባሆን ከማብቀል፣ ከመሸጥ እንደማትቆጠብ ተናግረዋል።

ዚምባብዌ የትምባሆ ምርቷን ታቁም የሚለውን ሙጋቤ አይስማሙም “ምክንያቱም የሲጋራ አጫሾች ማጨስ ይፈልጋሉ፤ ከሲጋራ በላይ መጥፎና ገዳይ የሆኑ መጠጦች እንደነ ዊስኪና ቢራ በዓለም ይመረታሉ፤ ይሸጣሉም” በማለት ጆርጅ ቻምባራ ተናግረዋል።

አጭር የምስል መግለጫ

በአለም ዓቀፍ ደረጃ ከፍተኛ የትምባሆ አምራች ከሚባሉ አገራት ዚምባብዌ አንዷ ናት

ዶክተር ቴድሮስ የሙጋቤን ሹመት ባለፈው ሳምንት ያስተላለፉት የማይተላለፉ በሽታዎችን ለመከላከል በአቻዎቻቸው ላይ ተፅእኖ ማሳደር ይችላሉ በሚል ነበር።

የእንግሊዝና የካናዳ መንግስታትን ጨምሮ ከፍተኛ ዓለም አቀፍ ውግዘት ስለደረሰባቸውም ሹመቱን ቀልብሰውታል።

አራት አስርት ዓመታት ሊደፍን ትንሽ በቀራቸው አመራር የመጀመሪያዎቹ 20 ዓመታት ሙጋቤ የተሻለ የጤና ስርዓትን መዘርጋት ችለው ነበር።

ከዚምባብዌ የኢኮኖሚ ማሽቆልቆል ጋር ተያይዞ የጤና ስርዓቱም ከፍተኛ ተፅእኖ ደርሶበታል።

የህክምና ባለሙያዎች ያለደሞዝ በሚሰሩበት፤ መድኃኒቶች በከፍተኛ ሁኔታ በሚያጥሩበት ሁኔታ በተቃራኒው ሙጋቤ ህክምናን ለመሻት ወደውጭ ይጓዛሉ።
 

Related:

አቤት ቅሌት!

Statement from WHO Director-General Dr Tedros Adhanom Ghebreyesus rescinding the appointment of Goodwill Ambassador for NCDs in Africa

WHO blunder exposes UN: President never told of appointment …

Lacking good judgement & moral compass, corrupt Tedros Adhanom designates fellow traveller Mugabe WHO Goodwill Ambassador — Wait for more TPLF decadence to infest hitherto best run UN body — Poor WHO!

Tedros Adhanom embarrasses WHO, its staff & United Nations system: First with his poor judgement, now bungling it with disgraceful retreat of first order! Not even an apology!

 

%d bloggers like this: