የሕወሃት ም/ሊቀመንበር ነፍሰ ገዳዩ ሕወሃትን ‘አመራር’ በእጃቸው ለማስገባት የሚያደርጉት ዝግጅት፡ከወዲሁ መጥፎና ክፉውን ገጽታቸውን በክህደት እያበሱ ያሉ አስመስሏቸዋል!

29 Oct

በከፍያለው ገብረመድኅን The Ethiopia Observatory (TEO)
 
የቀረቡላቸው ጥያቄዎች በደብረጽዮን ተቀርጸው ለጽናት ራዲዮ የተሠጡ እንደሆኑ፡ የጥያቄዎቹ ይዘትና በአሁኑ ሰዓት ለምን እንደተነሱ ማንም ሰው ከይዘታቸው በመነሳት ለደብረጽዮን ለምን እንዳስፈለጉ መገመት የሳተርን መንኮራኮር ካሲኒን የሠሩትን የጠፈር ሊቃውንት ጭንቅላት አይጠይቅም!

የሚኒስትሩን ንግግር ሶስት ጊዜ ካዳመጥኩ በኋላ፡ ከዚህ በታች የራሴን ግንዛቤና ትዕዝብት እንደሚከተለው አሥፍሬያለሁ፡-

“የሃገራችንን ወቅታዊ ጉዳይ አስመልክቶም ሆነ ከዚያ በፊት በነበሩት አንዳንድ ችግሮች ሁሉ ሕወሃትን ተጠያቂ የማድረግና የመውቀስ ሁኔታዎች ይሰተዋላሉ። ይህ በተለይም በዲያስፖራው የጽንፍ ፖለቲካ ውስጥ ሠፋ ብሎ ይታያል። ለምን ይሆን? መነሻው ምንድነው?”


በዚህ ላይ የእርሶ አስተያየት የሚለው ጥይቄ በቀዳሚነት ለሕወሃት ምክትል ሊቀመንበር የሕወሃት ምክትል ሊቀመንበርና የኮሚኒኬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል ቀረበላቸው።

የሥርዓቱ ዋነኛው ጠላት “ኪራይ ሰብሳቢነት ነው” በማለት መንደርደሪያ ከሠጡ በኋላ፣ ሃገራችንን በዲጂታል ቴክኖሎጂ ዕድገት የሃገሮች ጭራ ያስደረጓት፣ ለዘመናት የኢትዮጵያ በመስኩ ሚኒስትር ሆነው የኖሩት፤ ከዚህ ሥራቸው ይልቅ ኢትዮጵያውያንን በመከፋፈል የተጠመዱት እኒሁ ሰው — በቅርቡ በሶማልያ ክልል ባለው የልዩ ፖሊስ ኢትዮጵያውያን ኦሮሞች እንዲፈናቀሉ አቀነባባሪ መሆናቸው የሚነገርላቸው — ማንነታቸውን በሚገባ ያንጸባረቀውን አፍነው፡ እሠረው፡ በለውና ግጨው አሳፋሪ መልሳቸውን ሠጥተዋል — ክዚህ በታች ካለው ቃለ መጠይቅ አድምጣችሁ ፍርዱን የናንተ አድርጉት!


 

ደብረጽዮን ገ/ሚካኤልም በሰጡት መልስ እንደ ተቀጣሪያቸው የጽናት ራዲዮ አዘጋጅ ሰሎሞን ተካልኝ ጠያቂያቸው ሁሉ፡ ሕወሃት በኃላፊነት ብቻውን — ከአራቱ ድርጅቶች ውጭ — ከትግራይ ክልል ባሻገር ሃገር ያስተዳደረበት ጊዜና ሁኔታ ስለሌለ፣ በተለይ በኢትዮጵያ ላለው ሁኔታ የተለየ ኃላፊነት የለውም በማለት አጣጥለውታል።

ሰለሆነም ጠያቂያቸው በሠጣቸው መሰላል ላይ ወጥተው፡ቁጢጥ ካሉ በኋላ ኃላፊነት ባልተሠጠበት ተጠያቂነት አይኖርም በማለት፡ ቀጠሉ።

ሕወሃት እንዲህ ዐይነት ኃላፊነት በኢትዮጵያ ውስጥ የለውም ብለው በጊዜው አስገዳጅነት ምክንያት ሌሎች ቅጥረኞቻቸውን በሚያስደነግጥ ሁኔታ እነእርሱን በንግባር ቀድምነት ኃላፊነት እንዳለባቸው ዛሬ በማውራት ለማምለጥ የሚደረገው ዝግጅት ለሌሎቹ ሥልጣኑ “የሕልም እንጀራ” ነው ብለው ማንም እንዳይነጥቃቸው ሲውተረተሩ ቢደመጡም፡ ሕወሃት የገባበት አጣብቂኝ እሳቸውንም እንዳሳሰባቸው የሚያሳይ ሆኖ ተሰምቶኛል — የቅጣት ማቅለያቸውን ያዘጋጁ መስለው ታይተውኛል!

ታዲያ የቀረው ቢቀር ለምን ይሆን፣ የስኳር ገንዘባችንን እንክት አድርጎ የበላውና ውሽሞቹን ያዝናናበት ዘራፊው ዐባይ ፀሐዬ ከዛሬ ሁለት ዓመት በፊት — የአዲስ አበባ ዙርያን የሕዝብ መሬት ለመሠልቀጥ ቋምጦ ማስተር ፕላን “ይተገበራል! ይፈጸማል!” “ማንም ይሁን ማን ልክ እናስገባለን!” ብሎ በመደንፋትና በማን አለብኝነት አልነበር እንዴ በራሱ ማቅራራት ተሳክሮ ሕዝቡን በዚያ የቁጣ ማዕበል ያስነሳው?

እንዴት ይሆን በብሄራዊ ደረጃ በፊደራል መዋቅራዊ አመራር፣ በክልሎች ደግሞ በፖለቲካ ግንባሮቹ አደረጃጀትና ድርጅታዊ ሥራ ሕወሃት የያዛቸውን ሥልጣኖች በብቸኝነት ይዞ የማይስማማውን ከመሃል እስከድንበር እየበወዘ፣ ሥልጣኑን ሥራ ላይ ማዋል የቻለው? ያንንም መከታ አድርጎ አይደል እንዴ በማስፈራራትና ዜጎችን በማሸበር — ሕዝቡ ታጋሽ ቢሆንም — ‘ነጻ አውጭዎቹ’ በማፍያነት እስካሁን ሃገሪቷን እያሸበሩና እያስገበሩ ያሉት?

በተለይ የሃገሪቱን የደኅንነት፣ የፍትህና የጦር የአመራሮቹን ሥፍራዎች በተናጠል ይዞ ባለበት ሁኔታ በየውቅቱና በየሥፍራው ነጻነታቸውንና መብቶቻቸውን መከበር የጠየቁትን ኢትዮጵያውያን በራሱ በአጋዚ ጦር ሲረሽናቸውና ሲያስረሽናቸው የኖረው በብቸኝነት ሕወሃት አይደል እንዴ?

Foto Aigaforum

ደብረጽዮን ዶክትሬት አላቸው ቢባልም — ትክክል ከሆነ — በእርሳቸው ትንሿ ጭንቅላታችው ላይ ዘውድ ካልተደፋላቸው በስተቀር፣ ሕወሃት ሃገር ረግጦ በጉልበት እየገዛ መሆኑን አያምኑም! የኢትዮጵያ ሕዝብስ ከ1997 ምርጫ ጀምሮ ሕወሃት የሚባል ዘረኛና ሽብር ፈጣሪ ድርጅት እንዳልፈለገና እንዳልተቀበለም በልባቸው ልብ ውስጥስ ያምኑ ይሆን?

ያልተገንዘቡት ሌላው ጉዳይ የኢትዮጵያ ሕዝብ ቅጥፈትን መብቱ ያደረገን ባለሥልጣን ይንቃል። አክራሪንና ዋሾነት መሪዎቹ ላይ ቀርቶ ጎረቤቶቹም ላይ የሚጠላ ሕዝብ መሆኑን ደብረጽዮን መገንዘብ ሕዝቡን ንቀውታልና የቻሉ አይመስልም!

በአጠቃላይ፡ ይህም ሆኖ የሕወሃት ሰዎች — እገሌ ከእገሌ ሳይባል — ውሽትና ክህደት የጋራ ባህርያቸው ነው።

ያን ጊዜ ዐባይ ፀሐዬም “እኔ እንደዚያ አላልኩም ካፌም አልወጣም፤ ሊወጣም አይችልም” ብሎ ዳንኤል ብርሃኔ በስለላ ድርጅቱ ገንዘብ በሚያስተዳደራቸው ሚዲያዎች አማካይነት ጭልጥ አድርጎ ካደ። ዛሬም በዘረኝነታቸውና በዜጎች ጨፍጫፊነታቸው እጅግ የታወቁት ደብረዮንም የሕወሃት ችግሮችን በመሸፋፈን፡ ትላንት ስለድርጅቱ የተወራው፣ ዛሬም የሚባለው ሁሉ የጽንፈኛው ዲያስፖራ ለሕወሃት ያለው ጠላትነት
ነው ብለው ነገሩን ሸፋፍነው ለማለፍ ሞክረዋል።

ቀና አመራር እኮ ስህተት አይፈጽምም ማለት አይደለም። ቀላማጅነትና አጭበርባሪነት ግን የጥሩ አመራር ባህሪ አይደለም። ከዚህ በፊት የኢትዮጵያን ሕዝብ ሲያስገርመው የከረመው ለሁሉም ብልሽታቸው የእነርሱ ዘራፊነት እንኳ ሳይቀር ለግብጽና ለኤርትራ ማስተላለፋቸው ነው።

የኢትዮጵያን ሕዝብ ጠላቶች አበራክተው፣ እነርሱ በጎ ሠሪዎች ለመምሰል፡ ኪራይ ሰብሳቢዎች፡ ጠባቦች፡ ትምክህተኞች፡ የባዕዳን ተቀጣሪዎችና ያለፈውን ሥርዓት ናፋቂዎች ወዘተ ሃገሪቱ በልማት፡ በዲሞክራሲና በዕድገት ጎዳና እንዳትመላለስ ዕንቅፋት እንደሆኑ፣ ንጹሃኑ ሕወሃቶች ሁሉንም ወነጀሉ ከራሳቸው በስተቀር! ይህንንም መወንጀላቸውን በየቀኑ እንደቀጠሉ ናቸው — በዚህ ቃለ መጠይቅ ውስጥም! ይህ ግን የኢትዮጵያን ሕዝብ አልደለለውም!

[click to magnify] ሌላው ዜጎችን ሳናስታውስ የማናልፈው ጉዳይ፣ ደብረጽዮን ከሁለት ዓመታት በፊት ፌስቡክ እንዳነበራቸውና “እንኳን 30 ሚልዮን ሰዎችን (አማሮችን ማለታቸው ነው) መላው አፍሪካን መደምሰስ ችሎታ አለን ያሉት ሲታወስ፣ ለውጥ ተቃርቧልና ለግድያዎቹ ሁሉ ግንባር ቀደም ተጥያቂ እደረጋለሁ በመፍራት ይመስላል፣ “እኔፊስ ቡክ ኖሮኝም አያውቁም ያሉት ሽምጠጣ።

ያ ሁሉ በማስተር ፕላን ዙርያ የነበረው የዐባይ ፀሐዬ ድንፋታ እንደጉም ተኖ “ይህቺን ቃል አላውቃትም” ካሉት ጋር አንድ ደምና ሥጋ ናቸው!

ኤርትራን በተመለከተ፣ በዚህ ቃለ መጠይቅ እንደተሰማው ከሆነ — ዲፕሎማቶች እንደሚሉት — ሕወሃት ቀደም ብሎ ለላከው Feeler — ወይንም አንዳንድ መንግሥታት ከምርጫ በፊት እንደሚያደርጉት — trial balloon በመልቀቅ የኤርትራን መንግሥት ምላሽ ሙሉ ለሙሉ እንዳልጣለው ተጨማሪ ምልክቶች እንደሚጠብቁ ደበቅበቅ ባለቋንቋ ነግረውናል። ኢርትራንም ለማስደሰት ግን የቀድሞው ስድቦች ቀርተው አንድ ሕዝብ ነን በትግሉም አብረን ነበርን የሚለው ደጀ ጥናት በዚህ ቃለ መጠይቅ ድንብርብሩ ከሚወጣው ጠቅላይ ሚኒስትር ይልቅ በሕወሃት ምክትል ሊቀመንበር በኩል መላኩን ቃለ መጠይቁም ከዚያ ጋር የተያያዘ የሲግናል ልውውጥ መስሏል!

ለዚህም እንደጠያቂው ሁሉ፡ ምክትል ሊቀመንበሩም ጽንፈኛው ዲያስፖራ በፈረሰው ሥርዓት ተጠቃሚ የነበረ በመሆኑ አሁን የሕወሃትን ስም ለሁሉም ነገር ኃላፊነቱን በድርጅቱ ላይ በመጫን ይላሉ። ለዚህም ምደምደሚያ ምክንያታቸው፣ በቂም በቀል ነው ብለው ከማጣጣላቸውም በላይ፡ አዲስም መጤም ከሆነ የሥልጣን ጉጉቱን በማርካት ሃገሪቱን ለመዝረፍ የሚደረገው ጥረት አካል ነው ብለው አስተሳሰባቸውን በሚያንጸባርቅ መንገድ፡ ሰንካላ ምክንያታቸውን አሰምተዋል።

ደግሞ የደብረጽዮን አስተሳሰብ አላሳቢነት የሚታየው እኮ፣ “በዘር ላይ የተመሠረተውን የብሂረስብ ፖሊሲያችን” በማለት ሲቀናጡ መደመጣችው፣ ከቁጣ ይልቅ እጅግ የሚከበረው ስለጥንታዊው አክሱም ታላቅነት የሚያወሳው የአክሱም ሃውልት የሚተርኩ መምሰላቸው ነው! ሃቁ ግን የማይሠራ ነገር አይሠራም!

እስካሁን ኢትዮጵያን ያህል ሃገር ለማፍረስ የተጠቀሙበት ነገር እኮ ባዶ ፊያሽኮ፣ እነርሱም ኤርትራን ለኢርትራዎኖቹ አስረክበው፣ ኦሮሞቹና ሶማሌዎችን በአንቀጽ 39 አማለው፥ ኢትዮጵያን የመሰለች ሃገር በቀጥታ የፖለቲካ ችግሮቿን የመፍታት ዕድል ነፍገው፣ ወደኋላ እንድትንሸራተት አድርገዋታል!

ልማትና ዕድገት በከተማ ሕንጻ ላይ ሕንጻ መከመር ና አስፋልት ማስፋፋት ሳይሆን፡ ዜጎች በሃገራቸው ሰላምና ደህንነት የሚሰማቸው፡ ጤናቸው ከዕለት ዕለት እየተሟላ የሚሂድበት፡ ልጆቻቸው የተሻለ ትምህርት ቤቶች የሚኖሯቸው ሁኔታ መሟላትና ዜጎች በእኩልነት የሚተዳደሩባት እንጂ ዘውገ ሕወሃቶች የባላይነት የምትሆኑባት እንድትሆን አልነበረም!

የሚገርመው ይሉኝታ የሚባለው ነገር የሕወሃት ሰዎች ውስጥ ስላልተፈጠረ ወይንም በሙሉ ስለተደረመሰ፡ መለኪያችሁ የጦርነቱ የደርግ ዘመን – እናንተ የሃገሪቱን ሕልውና አደጋ ላይ የጣላችሁበት ጋር ማወዳደር ነው! ባጭሩ ልማት ለምን የሕዝብ ልማትና ሕይወት ወደ ተሻለ ደረጃ መሸጋገር ማለት ነው! ለምን ዛሬ ከሩዋንዳ ጋር አትሉም ሌላው እንኳ ቢቀር! ካጋሜም እንዳያንዳቹ አወናባጅ ቢሆንም፣ የሃገሪቷን ገንዘብ ዘርፎ ራሱንና ዙሪያው ያሉትን ብቻ አልቀለበም!

ለማንኛውም፣ የሕወሃት ካምፕ ሽብር ላይ፣ ካቡ እየተናደ መሆኑን ከከዶር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል ይበልጥ ገሃድ ያደረገ ሰው፣ አናሊስት ወይንም ጋዜጠኛ የለም!
 

%d bloggers like this: