ኢትዮጵያ የውጪ ጉዳይና የደኅንነት ፖሊሲዋን ልትቀይር ነው ይባላል! ኢትዮጵያውያን ሕወሃትን — “በቃ! ከእንግዲህ ሞኝህን ፈልግ” ሊሉት ይገባል!

4 Nov

የአዘጋጁ አስተያየት

  ተሃድሶ ምንድነው እንደ ኢትዮጵያ ላለች ብዙ ግፎች ለተፈራረቁባት ሃገር?

  በእኛ እምነት ኢትዮጵያ የጎደላትን አይቶ ያንን ለሟሟላት የሚደረግ የፖለቲካ፡ መዋቅራዊና የግለሰቦች/የድርጅት ለውጥ ተግባራዊ ማድረግ ማለት ነው! ይህም ከሕወሃቶች ደባና ተንኮል የጸዳ፡ በሕዝብ ውክልና የሚከናውንና በሕዝብ ውክልና የሚጸድቅ መሆን ይኖርበታል!

  “ጥልቅ ተሃድሶ” ተብሎ በኢትዮጵያውያን ላይ በቅርቡ ኢትዮጵያውያንን ሕወሃት የተሳደበበት የተለመደውን የማጭበርበር እንቅስቃሴ — በሩቁም አይጨምርም!

  አንድ አመራር በሕዝቡ ዘንድ ተዓማኒነት ካጣ በኋላ፥ ሃገሪቱ በዚያው አመራር ሥር ሆና፥ ማለትም ነባሩ አመራር ከነግሳንግሱ እንዳለ ሥልጣን ላይ ሆኖ — ምንም ዐይነት ችግር ውስጥ ብትገባ — የፈለገውን ዐይነት ተሃድሶ ቢለፈፍ በሕዝብ ዘንድ ተቀባይነት አይኖረውም! ያለው አመራር ቢቀበልም ባይቀበልም፡ ሕውሃት ለኢትዮጵያ ሕዝብ ከእንግዲህ ፍሬ ከርስኪ የሆነ የማፍያዎች ክምችት በመሆኑ፡ የብዙ ንጹሃን ኢትዮጵያውያንን ደም በግፍ ያፈሰሰና በወራዳ የሃገር ሃብት ዘረፋ የተግማማ ድርጅት በመሆኑ፡ በኢትዮጵያውያን ፊት ምንጊዜም ተቀባይነት የለውም፤ አይኖረውምም!

  ስለሆነም፣ እንደተለመደው አሁን የኢትዮጵያን ሕዝብ ለማማለል፥ ‘የውጪ ጉዳይና የደኅንነት ፖሊሲ’ ለውጥ ተብሎ የተጀመረው ተፍ ተፍም፡ ከላይ ከተጠቀስው የማይለይ፡ ሌላው የሕወሃት ጠናጋራ ተንታኞች ያቀረቡት ሃሣብ ዓላማ የግንባሩን የሥልጣን ዕድሜ ለማራዘም የሚደረግ በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ ሕወሃት የሚፈጽመው ሸፍጦች አካል ነው!

  ማንም ይሁን ማንም፣ ከእንግዲህ የኢትዮጵያ ሕዝብ ልቡን የሚከፍተው — ከሕወሃት እንደ ድርጅት ውጭ — ለኢትዮጵያውያን ከእንግዲህ ብዙ ከገበርን ፡ ሃገራችንም የወደፊት እርምጃው መልካም አጋጣሚ በነበረት ወቅት ከባከነ በኋላ፡ ከእንግዲህ በአዲስ መልክ ልትመለከታችው የሚገቡ ጉዳዮች — ደግመዋለሁ፣ ሕወሃትና የታወቁት ነፍሰ ገዳዮቹ እንደ ግለሰብና ድርጅት ከተወገዱ በኋላ — ለሚከተሉት አንኳር ጉዳዮች የተለየ ትኩረት በመስጠት ኢትዮጵያ የወደፊት ዕድሏን እንደገና ልትመሠርትና ልትጠቀምበት ይገባታል፦

   (ሀ) በታጠቀው ኃይል፥ በፈና በያዘው የሕዝብ መገናኛና የሕዝብን ገንዘብ ለስግብግብ ተላላኪዎች በገዥነት በመበተን ሳይሆን፡ በሰብዓዊ መብቶች መከበር ዙርያ እምነቱ የተፈተነ ግለሰቦች ስብስብና ድርጅት፣

   (ለ) በሕግ የበላይነት የሚገዛ የገለሰቦችና የድርጅቶች ስብስብ

   (ሐ) በሕግ ላይ የተመሠረተ መዋቅራዊ አመራርና ሥራ አፈጻጸም የበላይነት የሚያምን የግለሰቦች ስብስብ ወይንም ድርጅት የአመራር አስኳል እንዲሆኑላት መሰባሰብ ያስፈልጋል!

  ከዚህ ውጭ፡ በተጥናገረ ዐይኖቻቸው ብቻ ሣይሆን፡ በተጠናገረ አዕምሯቸው፡ ዛሬም የኢትዮጵያ የሥልጣን ኮርቻ ላይ ለመቀጠልም ሆነ እንደ አዲስ ለመቆናጠጥ የሚሹትን ሌላ ለምድ የለበሱትን የሕወሃት መልዕክተኞች ሥልጣን አካባቢ እንዳይደርሱ፣ እንደውም የኢትዮጵያ ሕዝብ እነዚህን ወንበዴዎች ለፍርድ የሚያቀርብበት በጎን ማዘጋጀት ይኖርበታል!

=====================
 

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)
by Wazema Radio,
 
ኢትዮጵያ ሁለት አስርተ አመታት ለሚጠጋ ጊዜ ስትመራበት የነበረውን የውጪ ጉዳይና ደህንነት ፖሊሲ ለመቀየር እየተዘጋጀች መሆኑን የዋዜማ ምንጮች ገልፀዋል።

የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ፖሊሲውን ለመከለስ የሚረዱ ሀሳቦችን በማሰባሰብ ላይ ያተኮረ ስራ ሲሰራ የቆየ ሲሆን፣ ረቂቅ ፖሊሲው በቅርቡ ቀርቦ ውይይት ይደረግበታል ተብሎ ይጠበቃል።

ፖሊሲው በተለይ በአፍሪቃ ቀንድ አካባቢ የተከሰቱ ለውጦችን ታሳቢ አድርጎ እየተዘጋጀ መሆኑን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ያስረዳሉ።

ከአስራ ስባት አመታት በፊት የተዘጋጀውና በቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር እንደተፃፈ በሚነገርለት የውጪ ጉዳይ ፖሊሲ የሀገሪቱ ዋነኛ የህልውና አደጋ ድህነት መሆኑን በማተት ድህነት ከተቀረፈ ሀገሪቱ ከዉጪ ሀይሎች የሚገጥማትን ፈተና በድል አድራጊነት መወጣት እንደምትችል ያትታል።

ፖሊሲው ከኤርትራ ወረራ ማግስት የተፃፈ ቢሆንም ብዙዎቹን ክፍለ አህጉራዊ ችግሮችን “በልማታዊ መነፅር” የሚመለከትና የሀገሪቱን የአደጋ ተጋላጭነት አቃሎ የሚመለከት በመሆኑ ሲተች ቆይቷል።

ሀገሪቱ ወደብ አልባ በመሆኗ የገጠማትን ቀላል የማይባል ፈተና በእጅጉ የሚያቃልለው ይህ ፖሊሲ በራሱ በገዥው ፓርቲ አንዳንድ አባላት ሳይቀር ትችት ይቀርብበት ነበር።

ከፖሊሲው መውጣት በኋላ ሀገሪቱ ከፖሊሲው ትርክት በተፃራሪ ወደ ሶማሊያ ጦሯን አዝምታለች።

በአሁኑ ወቅትም ቢያንስ አስራ ሁለት የታጠቁ ሀይሎች በስልጣን ላይ ያለውን መንግስት ለመጣል በጎረቤት ሀገራት ተጠልለው ይገኛሉ።

ምስራቅ አፍሪቃ በርካታ የአረብ ሀገራትንና የሀያሉን ሀገራት የጦር ሰፈር ማስተናገድ መጀመሩ፣ የደቡብ ሱዳን ነፃ ሀገር መሆንና ሌሎች አለማቀፍ ሁኔታዎችም ባለፉት አመታት የተከሰቱ ለውጦች ናቸው።

አዲሱ ፖሊሲ የአየር ንብረት ለውጥን ጨምሮ የተለያዩ ለውጦችን ታሳቢ አድርጎ እንደሚዘጋጅ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
 

%d bloggers like this: