Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)
አዲስ አበባ፣ ኅዳር 20 ፣ 2010 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ ከቅድመ መደበኛ ጀምሮ እስከ መሰናዶ ባሉ የትምህርት ተቋማት ላይ በተደረገ ምዘና 74.9% ከተቀመጠላቸው ደረጃና መስፈርት በታች መሆናቸው ተረጋገጠ።
የአጠቃላይ ትምህርት ጥራትና አግባብነት ሬጉላቶሪ ኤጀንሲ በምዘና ውጤቱ ላይ ከመምህራን እና ከትምህርት ተቋማት አመራሮች ጋር እየተወያየ ሲሆን፥ በ2009 ዓ.ም ያካሄደውን የቁጥጥርና ክትትል ስራ ግኝትም ይፋ አድርጓል።
በመዲናዋም ከቅድመ መደበኛ እስከ መሰናዶ በሚገኙ 1,612 የትምህርት ተቋማት ላይ ከመምህራን አቅም ጀምሮ በመማሪያ ቁሳቁስና በሌሎችም ዘርፎች ምዘና ተደርጓል።
በዚህም 25 ነጥብ 1 የትምህርት ተቋማት በሚፈለገው ደረጃ ላይ ሲገኙ፥ ቀሪዎቹ 74.9% ከደረጃ በታች መሆናቸው ተረጋግጧል ነው የተባለው።
ይህም በሃገሪቱ የመማር ማስተማር ሂደቱን ውጤታማ ለማድረግ እየተተገበረ ያለው የትምህርት ጥራት ደረጃ በሚፈለገው መጠን ውጤታማ አለመሆኑን አመላካች ነው ተብሏል።
በሃገሪቱ ከ1ኛ እስከ 4ኛ የትምህርት ጥራት ደረጃ ተለይቶ የመማር ማስተማር ሂደቱን የተሻለ ለማድረግ እየተሰራበት ይገኛል።
እንደ ሃገርም ሁሉም የትምህርት ተቋማት 3ኛ ደረጃ ላይ እንዲገኙ ቢፈለግም የተገኘው ውጤት ግን ከዚህ ተቃራኒ መሆኑን በውይይቱ ወቅት ተገልጿል።
የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ወይዘሪት ብሩክነሽ አራጋው እንዳሉት፥ በዝቅተኛ ደረጃ ላይ የሚገኙ የትምህርት ተቋማትን አቅም ለማሳደግ ድጋፍ እየተደረገላቸው ነው።
ከዚህ ባለፈ ግን ድጋፍ ተደርጎላቸው መሻሻል ባልቻሉ ተቋማት ላይ ከማስጠንቀቂያ ጀምሮ ፍቃድ እከመንጠቅና ትምህርት ቤቱን እስመዝጋት የደረሰ እርምጃ እየተወሰደባቸው መሆኑንም ተናግረዋል።
መሰል ውይይቶች የተቋማቱን አቅም ለማሳደግ ይረዳሉም ነው ያሉት ዋና ዳይሬክተሯ።
ተዛማጅ፡
-
ምርጫ 2007ን ለመዝረፍ በሕወሃት/ኢሕአዴግ በከፍተኛ የትምህርት ተቋሞች የተደረጉ ወንጀለኛ ዝግጅቶች – በፓርቲው ውስጣዊ መረጃ ላይ የተመሠረተ ትንታኔ
Ethiopia’s higher-education boom built on shoddy foundations: Regime’s politics are obstacle
Education under persistent attack in Ethiopia
The widespread inequality in the education sector in Ethiopia & its implication to the nation’s future
Excellent UNESCO report identifies heart of Ethiopia’s education problems
2014 performance ranking of Ethiopia’s 31 universities: An old nation as beginner & in doubt
ደንቆሮ የምትፅፈው ኢትዮጵያ ጮንቆሃል መሰለኝ
Sent from my Samsung Galaxy smartphone.
LikeLike
እንደለመዳችሁት እናንተ ባለጌዎች፣ ነፍሰ ገዳይ ደናቁርት! ሃገራችንን ለዚህ ሁሉ ችግር የዳረጋችሁ! ሕዝብ ይፍረድ እስቲ አሁን ካጻጻፍህ እንኳ አንተና ሕወሃት ወራዳነታችሁን መሸፈን ያልቻልክ!
LikeLike