ትግራዊው የኢሕአዴግ ጽ/ቤት ኃላፊ ከሥልጣናቸው ተወገዱ! በደብረጽዮን ሥልጣን መያዝ ማግሥት የዐባይ ወልዱን ሰዎች ከሕወሃት በመንጠቆ

9 Dec

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)
by Abbay Media
 
ለረጅም አመታት በአዲስ አበባ ኢሕአዴግ ጽ/ቤት ሃላፊ ሆነው ሲሰሩ የቆዩት የህወሃቱ አቶ ተወልደ ወ/ጻዲቅ ከነበራቸው የጽ/ቤት ሀላፊነት መወገዳቸው ታወቀ።

አቶ ተወልደ ወ/ጻዲቅ የህወሃት ማእከላዊ ኮሚቴ መሆናቸውና የአዲስ አበባ መስተዳድር ምክትል ከንቲባ በመሆን ለረጅም አመታት ሲሰሩ መቆየታቸው ሲታወቅ በአሁኑ ሰአት ከአዲስ አበባ የኢሕአዴግ ጽ/ቤት ሃላፊነታቸው መነሳታቸውን ተከትሎ የም/ከንቲባነታቸውን ስልጣን ይዘው ይቀጥሉ አይቀጥሉ እስካሁን የሚታወቅ ነገር የለም።

ይህ ነው የሚባል የትምህርት ደረጃ እንደሌላቸው የሚታወቁት አቶ ተወልደ ወ/ጻዲቅ ለረጅም አመታት ሁለት ስልጣን ይዘው ቆይተው በአሁኑ ሰአት ከጽ/ቤት ሀላፊነታቸው መነሳታቸው የአቶ አባይ ወልዱ ከህወሃት ሊ/መንበርነታቸው መውረድና በአቶ ደብረጺዮን የመተካቱ የቅርቡ ጊዜ የሕወሃት ሹም ሽር ጋር የተያያዘ ይሁን አይሁን አይታወቅም።

ከሹም ሽሩ በኋላ ከሀላፊነታቸው የተወገዱ የመጀመሪያው የህወሃት ሰው መሆናቸውን ተከትሎ ከፓርቲው የውስጥ ሽኩቻ ጋር የተያያዘ ነው የሚሉ አስተያየቶች እየተሰሙ ነው።
 

%d bloggers like this: