የቬሮኒካ መላኩ ሶሻል ሚዲያ አካውንት ምን ሆነ? ተዘጋ? ለምን? ሕወሃት ሰበረው?

9 Dec

ከአዘጋጁ፡

  በሕወሃት ስሞታ/ ሰባሪነት — ከሁለት አንዱ — የቨሮኒካ የሶሻል ሚዲያ አካውንቷ ተዘግቷል የሚል ጭምምታ ይሰማል። ፌስ ቡኳን ሞክሬያለሁ። መጀመሪያ This account is not available! የሚል መልዕክት አይቻለሁ።

  ከዚያ ወድያ ግን ታህሳስ 7/2017 የጻፈችውን — ከዚህ በታች የሠፈረውን አግኝቻለሁ። ስለዚህ ባለፉት ሁለት ቀናት የተከሰተ ሁኔታ ሊሆን ይችላል።

  የሶሻል ሚዲያ ማኅበረሰብ ግን ይህንኑ አካውንቷ ተዘግቷል የሚለውን በቁጭት በማገላበጥ ላይ ነው!

  ለየት የሚለው፣ ሰማኽኝ ጋሹ አበበ “ቬሮኒካ መላኩ የህወሃትን የሳይበር ሜካናይዝድ ብርጌድ ከጥቅም ውጭ ስላደረገችባቸው አካውንቷን አዘግተውታል። ይህ ግን ጊዜያዊ ድል ነው። እንደገና ስትመለስ ከምትወረውረው ሚሳይል ለማምለጥ የት ትደበቁ ይሆን። እናንተን አያርገኝ።” በማለት ያሠፈረው ነው

 

መጣጥፎች የሌሉበት የቬሮኒካ መላኩ ፈስቡክ


Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)
Veronica Melaku, Dec 7, 2017
 
“የደባርቅ ከነማ የእግር ኳስ ቡድን መቀሌ ሄዶ እንድጫዋት ተወሰኖበታል ” የሚል ዜና ዛሬ ተመልክቻለሁ። ይሄ በምንም ተአምር ተቀባይነት የሌለው ውሳኔ ነው። መቀሌ ላይ ለአማራ የተጠመደ አደገኛ ወጥመድ ይሸተኛል።

ለማንኛውም ዛሬ ለእናንተ የሚጠቅም ነገር ከ 500 አመታት በፊት ከጣሊያን ፍሎረንስ ከተማ የፈለቀው እውቁ የፖለቲካ ፈላስፋ የነበረው ኒኮሎ ማኪያቬሌ “The prince ” በሚለው መፅሃፉ ላይ ለወዳጁ ለታላቁ የፍሎረንስ ልኡል ሎሬንዞ ያካፈለውን ምክር ልልቀቅባችሁ።

በነገራችን ላይ እውቁን ሳይንቲስት ማኪያቬሌን ሰይጣን ለበስ አድርገው ለአለም ያሰራጩት እንግሊዞች ናቸው እንጅ ምርጥ የሆነ ሪያሊስት የሆነ ስትራቴጂስት ነበር። ከሩዝቬልት እስከ ኦባማ ፣ ከማርጋሬት ታቸር እስከ አንጌላ መርክል ያሉ መሪዎች ሲያደንቁት ስትራቴጅውንም ሲጠቀሙበት ነበር። አሁንም እየተጠቀሙበት ነው።

ለማንኛውም ማኪያቬሌ እንደዚህ ይላችኋል
“The lion cannot protect himself from traps, and the fox cannot defend himself from wolves. One must be a fox to recognize traps and a lion to frighten off wolves.”

ቀበሮ ብልህ ነው። ቀበሮ ወጥመድ አጥምዶ ማንም ይዞት አያውቅም። ቀበሮ የተጠመደለትን ወጥመድ ቀድሞ ተረድቶ ራሱን ከጠላቶቹ ይጠብቃል። ለቀበሮ ብልህነቱ ጠንካራ ጎኑ ሲሆን ከተኩላ ራሱን ለመጠበቅ የሚበቃ አቅመቢስነቱ ደግሞ ደካማ ጎኑ ነው።

አንበሳ ጠንካራ ነው ።ጀግና ነው ። አስፈሪ ነው ። ሊያጠቃው የመጣውን ጠላት ደቁሶ ድምጥማጡን ያጠፈዋል። የአንበሳ ጠንካራ ጎኑ አስፈሪነቱ ሲሆን ደካማ ጎኑ ደሞ የተጠመደለት ወጥመድ ዘሎ መግባቱ ነው።

ማኪያቬሊ ለፍሎረንሱ ልኡል ሎሬንዞ ያለው ” አንድ ሰው ራሱን ከጠላቶቹ ለመጠበቅ እንደ ቀበሮ ብልህ እንደ አንበሳ አስፈሪ መሆን አለበት ” ብሎታል።

አማራ እንደ አንበሳ አስፈሪ መሆኑ የታወቀ ነው ነገር ግን ደግ በመሆኑና ሰውን ስለሚያምን ዘሎ ወጥመድ ውስጥ ይገባል። ይሄ ማለት የቀበሮ ብልህነት ያስፈልገናል ማለት ነው።

የአማራው ደባርቅ ከነማ መቀሌ ሄዶ በጠላቶቹ የሞቀ አቀባበል ቢደረግለትም ወይም የአካል ጉዳት ቢደርስበትም በሁለቱም ሲናሪዮ ወጥመድ ውስጥ ለማስገባት የተጠመደ አደገኛ Trap ነው።

የሞቀ አቀባበል ቢደረግለት እነሱን እንደ እንግዳ ተቀባይ አማራን ደሞ በተቃራኒው ዲሞናይዝ በማድረግ ወልድያ ከነማን በእግርኳስ ፌደሬሽን ለማስቀጣት እንደ ግብአት ለመጠቀም የፕሮፓጋንዳ ተጠቃሚ ይሆናሉ። በሌላ በኩል በደባርቆች ላይ የአካል ጉዳት ቢደርስም የባሰ ወጥመድ ውስጥ መግባት ነው።

በዚህም መሰረት ደባርቅ ከነማ ይሄን ጨዋታ ቦይኮት ለማድረግ ለሰከንድ እንኳን ማሰብ አያስፈልገውም። ከፈለገ ኳሱ ድብን ብሎ ይቅር። ባለፈው ባህርዳር ከነማ መቀሌ ሄዶ የመልሱን ጨዋታ በ ህርዳር መደረግ ሲገባው አዲስ አበባ ያስደረጉት ትግሬዎቹ ቦይኮት እንደሚያደርጉ ቁርጡን ስለተናገሩ ነው። አሁን ደግሜ ደጋግሜ የማሰምርበት ጉዳይ የተጠመደ ወጥመድ ውስጥ ራሳችሁን ከመወርወር ትቆጠቡ ዘንድ ነው።
 

ተዛማጅ፡

  ባለፈው ሳምንት ወልዲያ ተቀስቅሶ በነበረው ተቃውሞ ምክንያት ሱቆቻቸውን የዘጉ ነጋዴዎች አልከፈቱም፣ የህወሓት አባላትም ለአስቸኳይ ስብሰባ ተጠርተዋል

  Champing at the cyberbit: TPLF has been targeting Ethiopian dissidents at home & abroad with new commercial spyware thru 2017 — without much success given the persistent demands to get rid of it!

 

%d bloggers like this: