የሕወሃት ማፍያዎች የመጨረሻ ጉዞ:        የደኅንነቱ መሥሪያ ቤት ከመከላከያ ጋር በተያያዘው የሥልጣን ትግል ፌደራል ፖሊስ በተጠንቀቅ እንዲቆም ትዕዛዝ ደረሰው!

10 Dec

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)
by Adjama Dejene
 

በጌታቸው አሰፋ የሚመራው የደኅንነቱ ዋና መሥሪያ ቤት ባስተላለፈው መመሪያ መሠረት የፌደራል ፖሊስ ከደህንነቱ የሚወርድለትን ማንኛውም ትዕዛዝ ለመፈጸም የሚያስችለውን የተጠንቀቅ ትዕዛዝ እንደወረደለት ከፌደራል ፖሊስ የተገኘ መረጃ ያመለክታል።

በደኅንነቱና በመከላከያ ባለው ቅራኔ ምክንያት የደኅንነቱ ዋና መሥሪያ ቤት በጄነራል ሳሞራ ትእዛዝ፤ መከላከያው እርምጃ ሊወስድ ይችላል የሚል የሥጋት ትንተና አቅርቧል።

ከመከላከያ የሚመጣን ማንኛውም አደጋ ለመከላከል በሚል አቶ ጌታቸው አሰፋ በመከላከያ ውስጥ ለእርሱ የሚታዘዙ የጦር አዛዦችን የመመልመል እንቅስቃሴ እያደረገ ይገኛል።

በተጨማሪ አቶ ጌታቸው አሰፋ ፌደራል ፖሊስን ከጎኑ በማሰለፍ በማንኛውም ወቅት እርምጃ ለመውሰድ የሚያስችለውን ሁኔታ እንዳዘጋጀ ታውቋል።

በፌደራል ፖሊስ የወንጀል መከላከል ዘርፍ ም/ል ዋና ዳይሬክተር የሆነው ም/ል ኮሚሽነር ግርማይ ከበደ (ማንጁስ) የአቶ ጌታቸውን ትእዛዝ ተቀብሎ ለማስፈጸም እንዲረዳው በሚል የፌደራል ፖሊስ ወታደሮች ከሱ ዕውቅና ውጪ ምንም አይነት እንቅስቃሴ እንዳያደርጉ መመሪያ አስተላልፏል።

ፌደራል ፖሊስ የደኅንነቱ ዋና መሥሪያ ቤት ተዋጊ ክፍል እንደሆነ በፌደራል ፖሊስ ውስጥ ያሉ ወኪሎቻችን ይጠቁማሉ።

አቶ ጌታቸው አሰፋ የፌደራል ፖሊስና የክልል የጸጥታ አካላትን በመጠቀም ከመከላከያ የሚመጣበትን ተጽኖ ለመቋቋም እየሞከረ ይገኛል። ለዚህም እንዲረዳ በሚል የክልል የጸጥታ አካላትን ቀጥታ ለደኅንነቱ መሥሪያ ቤት ተጠሪ የሚሆኑበትን አሠራር እንዲዘረጉ እየተደረገ ነው።

ጌታቸው አሰፋና ጀነራል ሳሞራ የኑስ ረጅም ጊዜ የቆየ ቅራኔ እንዳላቸው ይታወቃል።
 

%d bloggers like this: