የኦሕዴድ የፈረጠመ ክንድ ሕወሃትን በየፈርጁ መጎሸም!

10 Dec


 
Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)
 
Abebe Tolla Feyisa
 
ሃጫሉ ሁንዴሳ ትላንት የኦህዴድ ባለስልጣኖች በተገኙበት በሚገርም ልበሙሉነት ግፍ እና ጭቆናን የሚያወግዝ ከዛም አልፎ ታጋዮችን የሚያበረታታ ዜማ በሚሊኒየም አዳራሽ አቅርቧል።

ከጥቂት ቀናት በፊት ሃጫሉ በራሱ አዲሳባ ላይ ሊያዘጋጅ የነበረው የሙዚቃ ኮንሰርት ልክ እንደ ቴዲ አፍሮ በመንግስት ተሰርዞበት ነበር። ዛሬ ግን የኦህዴድ ባለስልጣናት ፊት ጮክ ብሎ አዜመ። (ይሄ ምን ያመለክታል ያልከኝ እንደሆነ… ትላንት በሌሎች የመንግስት ባለስልጣናት እንዳይዘፍን የተከለከለውን ከያኒ ዛሬ እነ ለማ መገርሳ ፊት በነፃነት መዝፈኑ ኦህዴድ ቀድሞ ከሚታማበት “የህውሃት ታዛዥነት” በሙሉ ወይም በከፊል አፈንግጦ መውጣቱን ነው።)

ኦህዴድ ሆይ ያዝልቅልህ እያልኩኝ… ስለ ኦህዴድ እና አቶ ለማ መገርሳ አብዮት ያቆርኩት አለኝ ሰሞኑን አንቆረቁረው እና እንነቋቆርበታለን…

እስከዛ ጀግናው በኦሮምኛ የሸለለውን ከተረጎሙት መካከል ለኔ የተስማማችኝን… እነሆ…. (ማን እንደሆነ የተረጎማት እንጃ…

“ሸልል ሸልል ይሉኛል ምኑን ልሸልል እኔ
ቂልንጦ አይደለም ወይ…
ቃሊቲ አይደለም ወይ….
ከርቸሌ አይደለም ወይ…
ሸልሎ የማይጠግበዉ የሚገኝ ወገኔ፡፡

የፈረሶቻችንን ዝና፣
የጀግኖቻችንን ዝና
አድዋ መቀሌ ይንገረና!
አብሮ መኖር ይሻል ብለን…
መከባበር ይሻል ብለን…
እስከዛሬ ታግሰናል…
ከእንግዲህ ግን ይበቃናል”

ሃጫሉ ሁንዴሳ
 

%d bloggers like this: