ስኳር ኮርፖሬሽን ከውጪ የገዛውን 3, 777 ኩንታል ስኳር ሲቀብር ከረመ፤ በቀብሩ ላይ ያልተገኘው ፌደራል ኦዲተር ገለጻና ምክንያቱን እንደማይቀበል አስታወቀ!

13 Dec

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)
 
(ኢሳት ዜና ታህሳስ 4 ቀን 2010 ዓም) ከውጭ አገር የተገዛውን ሁለት መርከብ ስኳር ተበላሽቶ እንዲቀበር ማድረጉን ስኳር ኮርፖሬሽን ቢያስታውቅም ኦዲተር መስሪያ ቤት ግን ምክንያቱን እንደማይቀበለው አስታወቀ።

በመበላሸቱ በመተሃራ እንዲቀበር አድርጌዋለሁ ቢልም የፌደራል ኦዲተር ግን ተቀብርዋል ስለተባለው ስኳር ምንም ዓይነት ሕጋዊ መረጃ አለማግኘቱን አስታወቀ። የስኳር ኮርፖሬሽኑ ስኳሩ መበላሸቱንና ለምግብነት እንደማይውል ውጪ አገር ድረስ ልኮ ማስመርመሩንና ስኳሩ በሚቀበርበት ወቅት በስፍራው የነበሩ የዓይን እማኞች እንዳሉ ገልጿል።

በሁለት መርከቦች ተጭኖ ወደ አገር ቤት የገባው ተበላሽቷል የተባለው ስኳር መጠን እጅግ ብዙ መሆኑን ኦዲተር መስሪያ ቤቱ አስታውቆ ምንም ዓይነት ሕጋዊ ካሳ ሳይጠየቅ ካለምንም ማስረጃ ተቀብርዋል ተብሎ በባለስልጣኖች የቀረበው ምክንያት ተቀባይነት ስለሌለው እርምጃ ሊወሰድበት ይገባዋል ማለቱን ሸገር ኤፍኤም ዘግቧል።

በመላው ኢትዮጵያ የስኳር እጥረት ባለበት ባሁኑ ወቅት በውጭ ምንዛሬ ተገዝቶ ወደ አገር ቤት ከገባ በኋላ ተበላሽቶ ተቀብርዋል ለተባለው ስኳርና ከ77 ቢሊዮን በላይ ወጥቶባቸው በጅምር ለቀሩ የስኳር ፕሮጀክቶች እስካሁን በሕግ የተጠየቀ አካል የለም።
 

%d bloggers like this: