ዕድሜ ለሕወሃት!                                    የቢልሃርዚያ በሽታን መከላከልና መቆጣጠር የሚያስችል የሙከራ ፕሮጀክት ይፋ ሆነ! ኢትዮጵያ መጀመሪያዋ አግኝዋ እንዳልሆነች

13 Dec

ከአዘጋጁ፡

 
Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)
 

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 4 ፣ 2010 (ኤፍ ቢ ሲ) በሃገሪቱ ሞቃታማ አካባቢዎች በስፋት የሚታየውን የቢልሃርዚያ በሽታን መከላከል እና መቆጣጠር የሚያስችል የሙከራ ፕሮጀክት ይፋ ሆነ።

ፕሮጀክቱን መተግበር የሚያስችለውን ስምምነት የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ናላ ፋውንዴሽን ከተሰኘ አጋር ድርጅት ጋር ተፈራርሟል።

የሙከራ ፕሮጀክቱ በሽታው በስፋት በሚታይበት ቤንች ማጂ ዞን የሚጀመር ሲሆን፥ ትኩረቱን በትምህርት ቤቶች በማድረግ ከ260 ሺህ በላይ ህጻናትን ተጠቃሚ ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል።

በፕሮጀክቱ በሽታውን መከላከል የሚያስችል የመድሃኒት ድጋፍ እንዲሁም የግልና የአካባቢ ንጸህና አጠባበቅ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች ይሰራሉ ተብሏል።

በቤንች ማጂ ዞን ከሚገኙ ወረዳዎች ሰባቱ ለበሽታው ተጋላጭ ሲሆኑ፥ ከ50 በመቶ በላዩ የዞኑ ህጻናት በበሽታው ተጠቂ መሆናቸው ይነገራል።

ለሶስት ተከታታይ አመታት በሚቆየው ፕሮጀክት በአጠቃላይ 300 ሺህ ዩሮ ጥቅም ላይ የሚውል ይሆናል።

በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ትኩረት የሚሹ የትሮፒካል በሽታዎች ቡድን መሪ አቶ ነብዩ ንጉስ፥ መንግስት በ2015 ለማጥፋት እና ለመከላከል ዘጠኝ በሽታዎችን ለይቶ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

የቢልሃርዚያ በሽታም ከተለዩ በሽታዎች አንዱ መሆኑን ጠቅሰው፥ የሚጀመረው ፕሮጀክት ለተያዘው እቅድ መሳካት አጋዥ ነው ብለዋል።

ከዚህ ባለፈም ሌሎች በሽታዎች ላይ በመስራት እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2030 ሃገሪቱ ልታሳካ ያቀደችውን ዘላቂ የልማት ግብ ለማሳካት የሚደረገው ጥረት አንዱ አካል መሆኑንም አስረድተዋል።
 

Related:

Professor Aklilu Lemma – The Ethiopian Scientist who found the cure for bilharzia
 

%d bloggers like this: