በተለያዩ የኢትዮጵያ ከተሞች ሕዝባዊ እምቢተኝነቱ ዳግም አገረሸ!

23 Dec

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)
By አቢሶሎም ፍሰሃ, AbbayMedia
 
በአብዛኛው የምዕራብ ኦሮሚያ አከባቢዎች እና በአምቦ፣ ጊንጪ፣ ጉደር፣ ግንደበረት፣ በኮቴና ኩታዬ የስራ ማቆም አድማ እየተደረገ መሆኑ ታውቋል።

ከአምቦ እስከ ነቀምት ሙሉ በሙሉ እንቢተኝነቱ ተጀምሮ ሕዝቡ ሱቁንና መንገድ በመዝጋት የሕወሃት አገዛዝ ያብቃ ጥያቄ ማሰማቱ ታውቋል። በሰንዳፋ፣ በኬና ሽኖ በተሰኙ አከባቢዎችም ህዝባዊ ተቃውሞ በመደረግ ላይ መሆኑን የሚወጡ መረጃዎች ያመላክታሉ።

የሕወሃት ስርዓት የሕዝብን ጥያቄዎች ባለመመለስ እና ስልጣኑን በኃይል በወታደራዊ እና በደህንነት ጨፍልቆ ለመግዛት እንደወሰነ ታውቋል። በዜጎች ላይ እየፈፀመ ያለው ኢሰብዓዊ ድርጊት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየባሰበት በመምጣቱ ዜጎችን በመከፋፈል እና በመግደል ጊዜውን ለማራዘም በመወሰን በአባላቱ ላይ እርምጃ ለመውሰድ መወሰኑም ተሰምቷል።

አገር ወደ ጥፋት እያመራች ስለሆነ ከእኛ ጥቅም በላይ አገር ይበልጣል፤ ለግልና ለተወሰነ ቡድን ጥቅም ብለን ያልተፈለገ ውሳኔ መወሰን የለብንም ያሉትን የራሱን ሰዎች ለማጥፋት ወስኖ ተግባራዊ ለማድረግ እየተንቀሳቀሰ መሆኑም ታወቋል።

የሕወሃትን አካሄድ የተመለከቱ ስርዓቱ የማይማርና ለለውጥ አለመዘጋጀቱን በገሀድ እያሳየ ነው፤ የተጀመረውንም የነፃነት ትግል ምላሽ የሚያገኘው ይህ ዘረኛ ስርዓት ሲወገድ በመሆኑ ትግሉን አጠናክሮ መቀጠል ዋናውና ወሳኙ ሥራ ነው። ስለሆነም፣ ሕዝቡ ሕወሃትን ከሕዝብ የመነጠል፣ የማዳከም፣ የሕወሃትን ምርቶች ባለመጠቀም ይህን ዘረኛ ስርዓት የሁላችን ጠላት በመሆኑ ትግሉም የሁላችን ስለሆነ ሕዝባዊ እምቢተኝነቱን ሁላችንም ልንቀላቀለው ይገባል ሲሉ ተደምጠዋል፡፡
 

%d bloggers like this: