የኢትዮጵያ ሕዝብ አገዛዙ ሳይወርድ ትግሉን አያቆምም ተባለ!

23 Dec

ከአዘጋጁ:

    ሕወሃት የተጋረጠበትን አደጋ ለመቋቋም፡ ማናቸውንም ነገር ከማድረግ አልተቆጠበም። ለምሣሌም ያህል በዚህ ዜና ውስጥ ከተጠቀሱት መካከል፡ የኢትዮጵያ ተቃዋሚዎች ለመከፋፈል፡ ፓርላማው ኦሮሚያ በአዲስ አበባ ላይ ያላትን ጥቅም ለመምከር አጀንዳውን ማንቀሳቀስ ሞክሮ ነበር።

    ለዚህም — ሰማኸኝ ጋሹ አበበ እንዳስቀመጠው — “በመሰሪነቱ ከመለስ ዜናዊ ጋር የሚስተካከለውና ህወሃት ላለፉት 23 አመታት ፓርላማውን በበላይነት እንዲቆጣጠር ያስቻለው አስመላሽ ወ/ስላሴ ዛሬ የአዲስ አበባን ጉዳይ በማምጣት ህዝብን ለመከፋፈል ያቀደው ሴራ ከሽፏል።”

    የሕወሃት ዜና ማሠራጫ ፋናምይህንኑ አስመልክቶ የኦሮሚያ ክልል በአዲስ አበባ ከተማ ላይ ያለውን ሕገ-መንግሥታዊ ልዩ ጥቅም አስመልክቶ በተዘጋጀው ረቂቅ አዋጅ ላይ ሊካሄድ የነበረው የውይይት መድረክ ለሌላ ጊዜ ተላለፈ በማለት ታኅሳስ 22/2017 ዘግቧል።

    በተጨማሪም፡ በኢሣት እንደተዘገበው፣ የፌደራል ጠ/አቃቢ ሕግ አቶ ጌታቸው አምባዬ እና የሕወሃት ጄኔራሎች በሶማሊ ክልል በመሰረቱት የጥቅም ኔትወርክ ምክንያት የሶማሊ ክልል ባለስልጣናት በቅርቡ በፈጸሙት ወንጀል ላይ ምርመራ እንዳይደረግባቸው እየተከላከሉ መሆናቸው ተጠቁሟል።

    TPLF military & civil officials in solidarity with murderer Region 5 Chief Ali Illey (credit: Adjama Dejene)

===============
 

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)
AbbayMedia

ኢትዮጵያ አገዛዙን በመቃወም ጋብ ያለ መስሎ የነበረው ሕዝባዊ ቁጣ አሁንም በተጠናከረ ሁኔታ በተለያዩ ቦታዎች በከፍተኛ የሕዝብ ቁጣ እንደገና መቀስቀሱ አገዛዙን ዳግም ወደማይወጣበት ጭንቀት ውስጥ እንደከተተው ለማወቅ ተችሏል።

በወልቂጤ ዩኒቨርስቲና በአዋሳ ዩኒቨርስቲ በተማሪዎች የተነሳው ይኸው አገዛዙን የሚቃወመው ሰልፍ በከፍተኛ ደረጃ የአካባቢውን ሕዝብ አካቶ እንዳመሸ ታውቋል። ከዚህ ጋር በተያያዘ የስርዓቱን ግድያና አፈና ተቃውመው ከአምቦ እስከ ነቀምት ባሉት ቦታዎች የሥራ ማቆም አድማ መጠራቱን መዘገባችን ይታወቃል።

በአዲስ አበባ የአለው የሕዝብ ስሜት አገዛዙን ጭንቀት ውስጥ ስለአስገባው አዲስ አበቤዎችን በተለያየ የስብሰባ ወጥመድ ለማዘናጋት በማሰብ በድምፅ ማጉያ ጥሪ ያስተላልፍ እንደነበር ሲታወቅ በፓርላማው ውሎም የኦህዴድ አባላት ስብሰባው እንዲቋረጥ ማድረጋቸው ታውቋል።

የአዲስ አበባው ፓርላማ አገዛዙ በአዲስ አበባ ልዩ ጥቅም ጉዳይ ለመወያየት ፍላጎት ቢያሳይም በቅድሚያ ስለተፈናቀሉትና ስለተገደሉት ኦሮሞዎች ተነጋግረን መፍትሄ ማግኘት አለብን፣ ይኽን ትልቅ ጉዳይ ወደ ጎን በመተው ስለአዲስ አበባ ልዩ ጥቅም የምንነጋገርበት ጉዳይ የለም ሲሉ የኦህዴድ ፓርላማ አባላቶች አስታውቀው ስብሰባው እንዲቋረጥ ማድረጋቸውን መዘገባችን ይታወሳል።

ከዚህ ጋር በተያያዘ ዜና፣ የፓርላማ አባሏ ወ/ሮ ነኢማ አሕመድ “ጠቅላይ ሚኒስትሩ ካላነጋገሩን ወደ ሥራ አንገባም ብለናል” ብለው መናገራቸውን በአሜሪካ የአማርኛው ድምጽ ክፍል በሰጡት ቃለ መጠይቅም መግለፃቸው ይታወሳል።

በተለያዩ የአገሪቷ ክፍሎች የሰፈረው የመከላከያ ሰራዊትም ከህዝቡ ተቃውሞ ሲገጥመውና ትብብርም የተነፈገው እንደሆነና ወደ ሱቆች ሄዶ ውሃ እንኳን መግዛት ያልቻለበት ሁኔታ መፈጠሩንም ለማወቅ ተችሏል።

የመከላከያ በክልሎች መስፈርን አስመልክቶ ሕዝቡ ተቃውሞውን በተለያዩ ቦታዎች እያሰማ መሆኑ ሲታወቅ በኦሮምያ አካባቢ መንገዶችን በመዝጋት ተቃውሟቸውን እያሳዩ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል።
 

%d bloggers like this: