ጩሉሌው ሕወሃት የአማራና ኦሮሞ መሪዎችን እጅ ጠምዝዞ አስተላለፍኩ የሚላቸው የኢሕአዴግ ስብሰባ ውሣኔ ሃሣቦች ‘ባዶነት’ ስለመጭው ጊዜ አሳሳቢነት መስካሪና ከተጠናከረ የሕዝብ ትግል ውጭ አማራጭ አለመኖሩን ጠቋሚ ናቸው!

30 Dec

በከፍያለው ገብረመድኅን The Ethiopia Observatory (TEO)
 

የሕወሃት ማዘናጊያ ሥራዎች ከሚጠበቀው በታች ተራነታቸውን በዚህ መግለጫ አሳይተዋል። በአስቸኳይ ጊዜ አዋጆችና በአፈና ጭምር ተሞክረው አፈናው ባልተሳካበት ሁኔታ፡ አሁን ባልታወቀ ምክንያት ሕወሃት በሥልጣኑ መቀጠል መሻቱንና እንደሚችልም የሚጠቁም መግለጫና የተለመዱትን የአፈና ሥራዎቹን እንደሚቀጥል በገሃድ ይናገራል።

የኢትዮጵያን የፖለቲካ ሂደት ለሚከታተሉ ዜጎች ግን፡ መግለጫው ድንብርብሩ የወጣ አስተዳደር — ከመሃላቸው አንዳቸውም ከአንዳቸው በማይሻሉበት ሁኔታ — ግራ እንደተጋባ መንጋ መምሰላቸውን ያሳያል።

ዲሞክራሲን በስምና ሕጋዊ መሰተዳደር በተግባር ባልታየባት ሃገር፡ የፊውዳል ርዝራዦችና ያላለሙትን መሸምጠጥ የለመዱ ወንበዴዎች ከዚህ የተሻለ ሊያደርጉ ስለማችይሉ በየአንቀጹ አንስተው የደረደሯቸው የተለመዱ አባባሎችም፡ በጥጋበኞች ሲጠረዝ ለኖረ ሕዝብ፡ “ድርጅታችን የሁሉም ሕዝቦች እኩልነት በተከበረባት አገራችን አንድ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ማኅበረሰብ የመገንባትን መርህ ተክትሎ ሲንቀሳቀስ ቆይቷል፡” ሲባል፣ በተጎዳውና በተገፋው ሕዝብ ውስጥ ለሚፈጠረው መከፋትና ቅሬታ ሕወሃት ደንታ እንደሌለው ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ አሳይቷል።

በኛ ግምት፡ በታሪክ እንደታየው ሁሉ፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ — በሕወሃት የተመረዙ አባባሎች ሳይደናገር — ከእንግዲሀ የወደፊት ዕድሉን እንደገና ነጻ መሆኑን በትግሎ ማረጋገጥ እንደሚኖርበት የሚያሳይ ሁኔታ ነው የተፈጠረው።
 
በትዕዝብት ዐይን ሥር ያረፉ ሕወሃት የመረጣቸው መንገዶችና የገለጸባቸው አባባሎች

እስቲ እያንዳንዱ ዜጋ ታዲይ የኔ ሁኔታ፣ ወይንም የጎረቤቴ፣ የትምህርት ቤት ጓደኛየ ለምን እንዲሆነ ብሎ ብቻ ይጠይቅ!

“ድርጅታችን የሁሉም ሕዝቦች እኩልነት በተከበረባት አገራችን አንድ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ማህበረሰብ የመገንባትን መርህ ተክትሎ ሲንቀሳቀስ ቆይቷል፡፡”
 
“ሕገ መንግስታዊ ዴሞክራሲያችን የግልና የቡድን መብቶችን በማስከበር የሰላምና የእድገት መሰረት እንደሆነ በእነዚሁ አመታት ተረጋግጧል፡፡”
 
“አዲሲቱ ኢትዮጵያ ከየትኛውም ህብረብሄራዊ አገር የምትለየው በዝሃነትን በማወቅና በማክበር ነው፡፡ ለ25 አመታት የተገነባው ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት የቋንቋ፣ የባህል፣ የታሪክ እኩልነትን አረጋግጦአል፡፡ የአገራችን ብሄር ብሄረሰቦች ራሳቸውን በራሳቸው ካልሆነ በቀር በሌላ የማይተዳደሩበት ሁኔታ ፈጥሯል፡፡”
 
“የኢሕአዴግ ስራአስፈፃሚኮሚቴ ከሁለት ሳምንት በላይ ጊዜ ያካሄደው ግምገማ በዚህ የህዝባችን ልባዊ ፍላጎትና ቅን አገራዊ አስተሳሰብ ላይ የተመሰረተና ለዚሁም መላው ድርጅታዊ አቅሙን ተገዥ ለማድረግ በሚያስችል ቁርጠኝነት የተካሄደ ነው፡፡ በመሆኑም ስብሰባው በትናንተናው እለት በመላው የአገራችን ሕዝቦች ከባድ ተጋድሎ የተመዘገቡ ስኬቶችን ለመጠበቅና ለማስፋት እንዲሁም ከምንም ነገር በላይ በአመራር ድክመት የተፈጠሩትን አደጋዎችና ስጋቶች ለመቅረፍ በሚያስችል ስምምነትና መግባባት ተጠናቋል፡፡”
 
  “ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴው በዚህ ስብሰባ ቀደም ሲል የተጀመረው የመታደስ ሂደትና የደረሰበትን ደረጃ እንዲሁም በአገራችን የሚታዩ የቆዩና ወቅታዊ ችግሮችን ከነዝርዘር መገለጫቸው በመለየት በመንስኤና መፍትሄዎቻቸው ላይ መክሮ የሃሳብ አንድነትና መተማመን ፈጥሯል፡፡ ችግሮቹን በመቅረፍ በእስካሁን ትግላችን የተመዘገቡ መልካም ውጤቶችን አስጠብቆ ለማስቀጠል የሚያስችል ቁርጠኝነትና ጠንካራ መግባባትን አረጋግጦ ወጥቷል፡፡”

 
  “ድርጅታችን የሁሉም ህዝቦች እኩልነት በተከበረባት አገራችን አንድ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ማህበረሰብ የመገንባትን መርህ ተክትሎ ሲንቀሳቀስ ቆይቷል፡፡ በተጨባጭም አገራችንን ከመበታተንቋፍ አውጥቶ አዲስ አይነት ዴሞክራሲያዊ አንድነትና የእኩልነት ትስስር በመገንባት ረጅም ርቀት ተጉዟል፡፡”
 
“በልማትና በሃገራዊ አንድነት ዙሪያ መትጋት ሲኖርባቸው ሕዝብን ከህዝብ ጋር በሚያራርቅ አፍራሽ ተግባር ውስጥ የተሰማሩ የግልና የመንግሥት የሚዲያ ተቋማት አካሄዳቸውን የሚያስተካክሉበት ሁኔታ ለመፍጠር እንደሚንቀሳቀስ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴው የወሰነ ሲሆን በተለይም በክልልም ሆነ በፌዴራል ደረጃ ከፖለቲካዊ፣ ከሕጋዊ አሠራርና ከሕገመንግሥታዊ ሥርዓት በራቀ መልኩ የሁከትና የግርግር መልእክት በህዝብ ሚዲያ የሚሰበክበትን እድል ለመዝጋት የሚያስችሉ የተቀናጁ እርምጃዎችን እንደሚወስድ በዚህ አጋጣሚ ይገልፃል፡፡”
 
በዜጎች ላይ አላግባብ እሥርና ግርፋት ሠቆቃ የሚፈጽም የወንበዴዎች አስተዳደር፡ በሚያስገርም ድፍረት እንዲህ ይላል፦
 
“ህገ መንግስታዊ ዴሞክራሲያዊ ስርዓታችን ያስከበራቸውን ሰብአዊና ዴሞከራሲያዊ መብቶች የመጣስ አዝማሚያዎችና ተግባራት በጥብቅ እንዲመከቱ ወስኗል፡፡ በዚህ ረገድ የህዝብን ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች በአስተማማኝ ደረጃ ለማስከበር ከፍተኛ ፋይዳ ያላቸው ተጨማሪ ርምጃዎች እንዲወሰዱም አቅጣጫ አስቀምጧል፡፡”

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ የሚያሠኙ የሕወሃት ቅጥፈቶች!

በመሆኑም፣ መግለጫው ከተጫነው አሰስ ገሠሥ ሁሉ፣ ለእኔ ሕወሃት ትንሽ ወደ እውነቱ አቅጣጫ ለማየት ሞክሯል የሚያሰኘኝ፣ የሚቀጥለው ዐረፍተ ነገር ብቻ ነው.-

“በአጭሩ በህብረተሰባችን ዘንድ ህገመንግሥታዊ ሥርዓቱን፣ ልማታዊ አስተሳሰብና፣ በብዝሃነት ላይ የተመሠረተ ኢትዮጵያዊ አንድነት በማጠናከር ረገድ የተሰራው ስራ መሆን የሚችለውን ያህል ውጤት ሳያመጣ እንደቀረ ሥራ አስፈፃሚው ባደረገው ግምገማ ማረጋገጥ ችሏል፡፡ በዚህ የተነሳ ብሄረሰባዊና አገራዊ ማንነትን አስተሳስሮ በመገንባት በኩል የታየውን ጉድለት በአፋጣኝና በአስተማማኝ መንገድ መፍታት እንደሚኖርብን ታምኖበታል፡፡”

ከዚህ ቀጥሎ በመግለጫቸው እንድተነገረው የመደለያ — ለችግሮቹ መፍትሄ የለሽ ስብሰባ ማካሄዳቸውን የሚመሠክሩትን — ቅጥፈቶቻቸውን እያንዳድንዱ ዜጋ የራሱን ፍርድ እያንዳድንዱ ዜጋ የራሱን ፍርድ እንዲሰጥ እንደሚከተለው ነቅሰን እናቀርባቸዋለን፦

    * “ድርጅታችን ኢህአዴግ አገራችንን በለውጥ ጎዳና መምራት ከጀመረበት ከ1983 ዓ.ምጀምሮ በሁሉም የህይወት መስኮች መሰረታዊና ተስፋ ሰጭ ለውጥ ሲመዘገብ የቆየ ቢሆንም፣ ከቅርብ አመታት ወዲህ ደግሞ ለውጡን በተጀመረው ስፋትና ግለት ለማስቀጠል የሚደረገውን ጥረት የሚፈታተኑ ችግሮች እየታዩ መምጣታቸውን ይገነዘባል፡፡”

    * “አገራችን በአንድ በኩል በተከተልነው መሰረታዊና ትክክለኛ አቅጣጫ በተገኙ መልካም ውጤቶች እጅግ የሚያስጎመዥ ሁኔታ ላይ ትገኛለች፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ በፈፀምናቸው ስህተቶችና ከእድገታችን ጋር ተያይዘው በተከሰቱ አዳዲስ ለውጦችና ፍላጎቶች ምክንያት ለጊዜውም ቢሆን በአሳሳቢ ወቅታዊ ችግሮች ተወጥራ የቆየችበት ሁኔታ መፈጠሩን የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው በትኩረት ገምግሟል፡፡”

    * “ለሁሉም የአገራችን ህዝቦች ግልፅ እንደሚሆነው ለበርካታ ዘመናት በማሽቆልቆል ሂደት ውስጥ ለማለፍ የተገደደችው አገራችን ለ25 አመታት ቀና ብላ ስትጓዝ ቆይታለች፡፡ ይህምበሁሉም አገር ወዳድ ዜጎች የሚታመንበትና አለምም የመሰከረለት ነው፡፡ የኢኮኖሚ ውድቀትና ማሽቆለቆል ተገትቶ ለሩብ ምእተ አመት የዘለቀው አገራዊ እድገት ኢትዮጵያችን በትንሳኤ ጎዳና መገኘቷን አብስሯል፡፡ ህገመንግስታዊ ዴሞክራሲያችን የግልና የቡድን መብቶችን በማስከበር የሰላምና የእድገት መሰረት እንደሆነ በእነዚሁ አመታት ተረጋግጧል፡፡”

    * “ብዝሃነት የኢትዮጵያችን መሰረትና መገለጫ እንደሆነ በመቀበል ይህንንኑ በአግባቡ ለማስተዳዳር ያደረግነው ጥረት አገራችን ዜጎች ለረጅም አመታት በፍቅርና መከባበር የሚኖሩባት የሰላም አገር እንደሆነች አስመስክሯል፡፡”

    * “የሚያስጎመዥ እውነታ ከቅርብ አመታት ወዲህ በመታየት ላይ ባሉ ጊዜያዊ ችግሮች የተነሳ ለአደጋ እየተጋለጠና ለሁሉም ማህበረሰቦቻችን የስጋት ምንጭ መሆን በጀመረ አዲስ ክስተት መልክ የሚገለፅበት አዝማሚያ ሰፋ ብሎ ታይቷል፡፡ ከዚህ የተነሳም መላ የአገራችን ህዝቦች ኢትዮጵያችንን ከገጠሟት ጊዜያዊ ችግሮች በማውጣት በትግላችን የተመዘገቡ ስኬኮችን ለመጠበቅና ለማስፋት፤ ድክመቶችንና አደጋዎችን ደግሞ በቁርጠኝነት ለማስተካከል የሚሹበት ሁኔታ ተፈጥሯል፡፡”

    * “በፊዴራላዊ አስተዳደራዊ ስርአታትን በእኩልነትና በመተሳሰብ የሚሳተፉበትን ሁኔታም አመቻችቷል፡፡ በዚህ የተነሳ ስርዓቱ ለበላይነትና የበታችነት የማይመች ሆኖ ተዋቅሯል፡፡ በተግባርም እኩልነት እንጂ የባላይነትም ሆነ የበታችነት የማይፈጠርበት ስርዓት ተገንብቷል፡፡”

    * “ይህንን መሰረታዊ መርሆ የሚነካ ማንኛውም ዝንባሌ የበላይነትን በዘላቂነት ሊፈጥር የማይችልና ከመኖቆር ውጭ ሌላ ውጤት የማያስገኝ እንደሚሆንም ይታመናል፡፡ ከዚህ በመነሳት ለሩብ ምእተ አመት በእኩልነትና በሰላም የዘለቀው ስርዓታችን የዚህ ውጤት እንደሆነ ስራ አስፈፃሚያችን በድጋሚ አረጋግጧል፡፡ በመሆኑም በማንኛውም ሽፋን ይህንን የእኩልነት ስርዓት ለማዳከም የሚደረግ ሙከራ ተቀባይነት እንደሌለውና ሊመከት እንደሚገባው ወስኗል፡፡”

    * “ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ በአንድ ወይም በሌላ ብሔር ህዝብና ድርጅት ስም እየማሉና እየተገዘቱ ጥገኛ ፍላጎታቸውን ለማርካት የሚንቀሳቀሱ ወገኖችን እንቅስቀሴ ማክሰም እንደሚገባ ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡ ሁሉም ብሔራዊ ድርጅቶች በሚያስተዳድሩት ክልል ውስጥ ያሉ ጥገኞችን ያለልዩነትና ማመንታት መታገል እንዳለባቸው ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡

  ሥራ አስፈፃሚው በድርጅታችን የዴሞክራሲ መጥበብ እዛው በዛው የውሳኔዎችን በታማንኝነትና በቁርጠኝነት የመፈፀም ዲሲፒሊንን እያላላ እንደመጣ አረጋግጦአል፡፡ በዚህ የተነሳ በድርጅትና በመንግስት ቋሚ መመሪያዎች በመገዛት መፈፀም የነበረባቸው ተግባራትና መሰጠት የነበረባቸው የእለት ተለት ውሳኔዎች እየቀሩ በብዙ የመንግስት መ/ቤቶች ህዝብ የሚጠብቃቸው አገልግሎቶች የማይሟሉበት ሁኔታ ተፈጥሯል፡፡”

    * “በአጠቃላይ በድርጅታችን በተለይም ደግሞ በሥራ አስፈፃሚው ውስጥ የታየው የውስጠ ድርጅት ዴሞክራሲ ችግር አደጋው በድርጅቱ ውስጥ ብቻ ታጥሮ የቀረ አልነበረም፡፡ የህዝብ መብትን በማክበርና ተገቢውን ህጋዊ አገልግሎት የመስጠት ግዴታን ባለመወጣት ጭምር የሚገለፅ ነበር፡፡ ከዚያም አልፎ ዴሞክራሲያችንን ማስፋትና ማጠናከር ሲገባ በተለያዩ መንገዶች የማጥበብ አዝማሚያም ተስተውሏል፡፡”

    * “ከበየቦታው እየተነሱ ያሉ ግጭቶች ከሰው ሞትና ከንብረት ውድመት በዘለለ የሃገራዊ ሕልውናችን ለአደጋና ሕዝባችንን ለጥፋት ቋፍ ያደረሱበት ሁኔታ ከመኖሩ በላይ ለውጭ ጥቃት ተጋላጭነታችንን የመጨመር ውጤት አስከትለዋል፡፡”

    * “ይህም በአጭር ቃል የመበልፀግ ተስፋና የሐገራዊ ሰላም መናጋት የተፋጠጡበት ሁኔታ ላይ እንደድንገኝ አድርጎናል፡፡ ከዚህ በመነሳት ስራአስፈፃሚ ኮሚቴያችን ህገመንግስታዊ ዴሞክራሲያችንን በታማኝነት ተግባራዊ ማድረግ ብቻ ሳይሆን መድረኩ የሚጠይቀውን ሁኔታ መነሻ በማድረግም ማስፋትና የግጭት መንስኤዎችን መቅረፍና የአገራችንን ሰላም ወደተለመደው አስተማማኝ ሁኔታ በአጭር ጊዜ መመለስ እንደሚገባ ወስኗል፡፡”

    * “በአገራችን የሚገነባው ህገመንግስትታዊ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት በፍላትና ጥቅሞች ብዝሃነት ላይ የተመሰረት ነው፡፡ ከዚህ በመነሳት የመድብለ ፓርቲ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ በድርጅታችንና በመንግስት መሪነት ለ25 አመታት የቀጠለ ቢሆንም ከቅርብ አመታት ወዲህ የአስተሳሰብ ብዝሃነት በአግባቡ እንዲገለፅ የሚያደርግ ተጨባጭ ሁኔታ እየተዳከመ መጥቷል፡፡”

    * “ይህንን ችግር በጊዜና በአግባቡ ተገንዝቦ ማስተካከል የሚገባው ድርጅታችን ተገቢውን ህጋዊ እርምጃ በመውሰድ ረገድ ያሳየው ዳተኝነት የመድብለ ፓርቱ ስርግቱን ችግር እንዲገጥመዉ አድርጓል፡፡ የዴሞክራሲ ምህዳሩን የማስፋት ጉዳይ ምንም እንኳ በአዋጅና በድርጅታችን በጎ ፈቃድ ላይ ብቻ የሚመሰረት ባይሆንም በዚህ ረገድ ልንወስደው ይገባን[ል፡፡”

  ለዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ሁነኛ ድርሻ ካላቸው ተቋማት መካከል የሃገራችን ሚዲያና ፕሬስ በሚገባው ደረጃ ነፃነታቸው ተጠብቆ የህዝብ ዓይንና ጆሮ ሆነው ያገለግሉ ዘንድ የተደረገው እንቅስቃሴ የሚፈለገውን ውጤት እንዳላመጣ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴው በግምገማው ተመልክቷል፡፡ በዚህ ረገድ የታየው ዘገምተኛ ዕድገት እንደተጠበቀ ሆኖ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በክልልም ይሁን በፌዴራል ያሉ የህዝብ የሚዲያ አውታሮች ሕግና ሥርዓትን ጠብቀው የማይሠሩበት ሁኔታ እያመዘነ የህዝቡን ሰላምና አብሮ የመኖር ገንቢ ባህል የሚሸረሽሩ ሰበካዎች የሚሰጥባቸው፣ ብሎም ህዝብን ከህዝብ ጋር የሚያጋጩ አጥፊ ቅስቀሳዎች የሚካሄድባቸው እየሆኑ ለመምጣታቸው የኢህአዴግ ሥራ አስፈፃሚም ሆነ የሚመራው መንግሥት ድክመት አስተዋፅኦ እንዳደረገ ይቀበላል፡፡”

    * “አመራሩ ዴሞክራሲያዊ ህብረተሰብ በመገንባትና በህገመንግስታዊ ስርዓታችን ዙሪያ ብሔራዊ መግባባት መፍጠር እየተገባው የህዝብ የተደራጀ ሲቪል እንቅስቃሴ እንዳልተጠናከረ አረጋግጧል፡፡ በአገራችን ህገመንግስታዊ ዴሞክራሲ ዋስትና የሚኖረው ከአዋጅ አልፎ ህዝብ በተደራጀና ንቁ አኳኋን ሲሳተፍና ሲጠቀምበት ቢሆንም በዚህ ረገድ የተደረገው እንቅስቃሴ የሲቪል ማህበረሰቡን ተሳትፎ መሆን በሚገባው ደረጀ ከፍ ለማድረግ ያስቻለ እንዳልሆነ ተመልክቷል፡፡ በዚህ መሰረት በአገራችን የሚገነባው ዴሞከራሲያዊ ስርአት የሚታይበትን የሲቪል ማህበረብ ተሳትፎና ሁለገብ እንቅስቃሴ ገደብ ከጣሉበት ችግሮች በማላቀቅ ማጠናከር እንደሚባ ታምኖበታል፡፡አመራሩ የዴሞክራቲክ ተቋማት ግንባታና የህዝብ የተደራጀ ተሳትፎ የሞት የሽረት ጉዳይ እንደሆነ ተገንዘቦ ባለመንቀሳቀሱ የተፈጠረውን መሰረታዊ ጉድለት ለመፍታት ልዩ ትኩረት መስጠት እንደሚገባም መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡”

    * “የህዝቡን ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማስፋት፣ የህግ የበላይነትን ለማደረጋገጥ፣ የግልፅነትና የተጠያቂነት አሰራርን ለማንገስና ውጤታማና ቀልጣፋ አስተዳዳር ለመገንባት የተደረጉ ጠረቶች ያስገኙትንን መልካም ፍሬ መጠበቅና ማስፋት አዳጋች ሆኖ ቆይቷል፡፡ በየደረጃው የመኑ የመንግስት አስፈፃሚ አካላት በቅን ልቦናና መንግስታዊ መመሪያዎችን በተከተለ አኳኋን ህዝቡን የሚያገለግሉና ተሳትፎና ተጠከሚነቱን የሚያረጋግጡበት እድል ቀንሷል፡፡ በዚህ የተነሳ ከፍተኛ የህዝብ ምሬት ተፈጥሯል፡፡ ስራ አስፈፃሚው ይህ ችግር ከምንም ነገር በላይ በከፍተኛው አመራር ደረጃ በሚታይ ጉድለት ምክንያት የተፈጠረና የተባበሰ እንደሆነ አረጋግጧል፡፡”

    * “የህግ የበላይነት የማስፈን ድክመት በመታየቱ በሙስናም ሆነ በሌሎች ጥፋቶች ውስጥ የተዘፈቁ ግለሰቦችን በወቅቱና ህጋዊና አስተማሪ በሆነ መንገድ መጠየቅ ሳየቻል ቆየቷል፡፡ ዜገች በህገመንግስቱ ዋስትና ያገኙ መብቶቻቸው የሚጥሱ ሰዎችን በህግ ተጠያቂ ማድረግ መሆን በሚገባው ደረጃ ሳይፈፀም ቆይቷል፡፡ በተጨማሪም መንግስት የህዝብና የአገር ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ በነደፋቸው ፕሮጄክቶት ዙሪያ የሚታዩ የአፈፅፀምና የስነምግባር ችግሮችን አስተማማኝና ውጤታማ በሆነ መንገድ የማረምና የማስተካከል ጉድለት ታይቷል፡፡”

    * “አገራችንን በሁሉም መስክ ተወዳዳሪ ሊያደርጉ የህዝባችንን ተጠቃሚነት ሊያሰፉ የሚችሉ ፕሮጄክቶች፣ የጊዜ የዋጋ ንረትና የሃብት ብክነት የሚታይባቸው ሆነዋል፡፡ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው እነዚህ የመልካም አስተዳዳር ችግሮች ህዝብና አገርን ያልተገባ ዋጋ የሚያስከፍሉ እንደሆኑ በመገንዘብ በአፋጣኝ እንደስተካከሉ ማድረግ እንደሚገባ አምኖበታል፡፡ በዚህ ረገድ ይህንን የመልካም አስተዳደር ችግር በተግባር ማቃለል ሲገባ ባጉል ተስፋና በባዶ ቃልኪዳን የመሸንገል ህዝበኛ አዝማሚያዎች በጥብቅ መመከት እንዳለባቸው ወስኗል፡፡”

    * “በፊዴራላዊ አስተዳደራዊ ስርአታችን በእኩልነትና በመተሳሰብ የሚሳተፉበትን ሁኔታም አመቻችቷል፡፡ በዚህ የተነሳ ስርዓቱ ለበላይነትና የበታችነት የማይመች ሆኖ ተዋቅሯል፡፡ በተግባርም እኩልነት እንጂ የባላይነትም ሆነ የበታችነት የማይፈጠርበት ስርዓት ተገንብቷል፡፡ ይህንን መሰረታዊ መርሆ የሚነካ ማንኛውም ዝንባሌ የበላይነትን በዘላቂነት ሊፈጥር የማይችልና ከመኖቆር ውጭ ሌላ ውጤት የማያስገኝ እንደሚሆንም ይታመናል፡፡”

  ከዚህ በመነሳት ለሩብ ምእተ አመት በእኩልነትና በሰላም የዘለቀው ስርዓታችን የዚህ ውጤት እንደሆነ ስራ አስፈፃሚያችን በድጋሚ አረጋግጧል፡፡ በመሆኑም በማንኛውም ሽፋን ይህንን የእኩልነት ስርዓት ለማዳከም የሚደረግ ሙከራ ተቀባይነት እንደሌለውና ሊመከት እንደሚገባው ወስኗል፡፡በአንድ ወይም በሌላ ብሔር ህዝብና ድርጅት ስም እየማሉና እየተገዘቱ ጥገኛ ፍላጎታቸውን ለማርካት የሚንቀሳቀሱ ወገኖችን እንቅስቀሴ ማክሰም እንደሚገባ ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡ ሁሉም ብሔራዊ ድርጅቶች በሚያስተዳድሩት ክልል ውስጥ ያሉ ጥገኞችን ያለልዩነትና ማመንታት መታገል እንዳለባቸው ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡”

    * “ሥራ አስፈፃሚው በድርጅታችን የዴሞክራሲ መጥበብ እዛው በዛው የውሳኔዎችን በታማንኝነትና በቁርጠኝነት የመፈፀም ዲሲፒሊንን እያላላ እንደመጣ አረጋግጦአል፡፡ በዚህ የተነሳ በድርጅትና በመንግስት ቋሚ መመሪያዎች በመገዛት መፈፀም የነበረባቸው ተግባራትና መሰጠት የነበረባቸው የእለት ተለት ውሳኔዎች እየቀሩ በብዙ የመንግስት መ/ቤቶች ህዝብ የሚጠብቃቸው አገልግሎቶች የማይሟሉበት ሁኔታ ተፈጥሯል፡፡

    * “የዴሞክራሲ መጥበብ እዛው በዛው የውሳኔዎችን በታማንኝነትና በቁርጠኝነት የመፈፀም ዲሲፒሊንን እያላላ እንደመጣ አረጋግጦአል፡፡ በዚህ የተነሳ በድርጅትና በመንግስት ቋሚ መመሪያዎች በመገዛት መፈፀም የነበረባቸው ተግባራትና መሰጠት የነበረባቸው የእለት ተለት ውሳኔዎች እየቀሩ በብዙ የመንግስት መ/ቤቶች ህዝብ የሚጠብቃቸው አገልግሎቶች የማይሟሉበት ሁኔታ ተፈጥሯል፡፡”

    * “በአጠቃላይ በድርጅታችን በተለይም ደግሞ በሥራ አስፈፃሚው ውስጥ የታየው የውስጠ ድርጅት ዴሞክራሲ ችግር አደጋው በድርጅቱ ውስጥ ብቻ ታጥሮ የቀረ አልነበረም፡፡ የህዝብ መብትን በማክበርና ተገቢውን ህጋዊ አገልግሎት የመስጠት ግዴታን ባለመወጣት ጭምር የሚገለፅ ነበር፡፡ ከዚያም አልፎ ዴሞክራሲያችንን ማስፋትና ማጠናከር ሲገባ በተለያዩ መንገዶች የማጥበብ አዝማሚያም ተስተውሏል፡፡ ህገ መንግስታዊ ስርአታችን ልዩ ልዩ ጥቅሞችና ፍላጎቶች እንዲሁም በእነዚህ ላይ የተመሰረቱ ልዩነቶች በዴሞክራሲያዊ፣ ህጋዊና ሰላማዊ መንገድ እንዲስተናገዱ በቂና አስተማማኝ እድል ከፍቶ እያለ አመራራችን ዴሞክራሲውን የማስፋት ግዴታውን ባለመወጣቱ ችግሮችና ልዩነቶች በግጭት መንገድ የሚፈቱበት ሁነታ እንዲፈጠር አስተዋፅኦ አድርጓል፡፡ ይህም ለሰላማችን መታወክ የበኩሉን አስተዋፅኦ አድርጓል፡፡”

  መንገድ መዝጋት የተቃውሞ መግለጫ ምልክት ሆኖ ሳለ፣ አሁን ሕወሃት የወሰነው፡ ምንም ዐይነት ተቃውሞ አይኖርም፤ ባሰኘኝ ጊዜ ገብቼ አሥራለሁ፤ ገርፋለሁ፤ እገድላለሁ ይላል።

  “የሕዝባችንን ሰላማዊ ኑሮ የሚያውኩ ማንኛውም እንቅስቃሴዎች ከሕዝብ ጋር በመሆን በቁጥጥር ስር ለማዋል መንግሥት ሙሉ ሃላፊነት ወስዶ እንዲያስፈፅም ተወስኗል፡፡ የሕግ የበላይነትን የማረጋገጥ ጉዳይ ላፍታም ቢሆን ጥያቄ ውስጥ ሊገባ እንደማይገባውና በዚህ ረገድ የሚታዩ የህግ ጥሰቶችን በመቆጣጠር ህግና ሰላምን በአስተማማኝ ደረጃ ማስፈን እንዳለበት ተወስኗል፡፡”

================

    * ሀ. “በየአካባቢው በሕገወጥ መንገድ የሚደረጉ መንገድ የመዝጋት፣ የዜጎችን በነፃ የመንቀሳቀስ መብት የማወክ እንዲሁም የሕዝቡን የእለትተለት እንቅስቃሴ የሚያስተጓጉሉ የቡድንም የተናጠልም እንቅስቃሴዎች እንዲቆሙ ይደረጋል፡፡

    * ለ. “በወሰንም ሆነ በሌሎች ምክንያቶች የሚያጋጥመውን ሞትና መፈናቀል ሙሉ በሙሉ ለማስቆም ወስኗል፡፡ በቅርቡ በኦሮሚያና በሶማሌ ክልል መካከል ባሉአዋሳኝ አካባቢዎች ባጋጠሙ ግጭቶች ሳቢያ የተፈጠረው የዜጎች ሞትና እንግልት እንዲሁም የመቶ ሺዎች መፈናቀል በአስቸኳይ ተገቶ ተፈናቃዮች መደበኛ ህይወታቸውን በተረጋጋ መንገድ የሚመሩበት ሁኔታ ባስቸኳይ ለማመቻቸት ወስኗል፡፡ በተጨማሪም በእነዚህ አካባቢዎች ለግጭት መንስኤ የሆኑ የሕገ ወጥ ንግድ እንቅስቃሴዎች እንዲቆሙ፤ አርሶ አደሮችና አርብቶ አደሮች የኢኮኖሚ እንቅስቃሴያቸው ለአደጋ እንዳይጋለጥ አስፈላጊው ጥበቃና ድጋፍ እንዲደረግ ወስኗል፡፡ በዚህ አጋጣሚ የአገራችን የመከላከያ ሰራዊትና የፀጥታ አካላት በአስቸጋሪ ሁኔታ ሰላማችንን ለማስከበር ለከፈሉት መስዋእትነት የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ያለውን አክብሮት ይገልፃል፡፡”

    * ሐ. “ከውስጠ ድርጅት ዴሞክራሲ አኳያ አሁን የተጀመረውን ግምገማ መሠረት በማድረግና የትራንስፎርሜሽን አጀንዳችንን በውጤት ለማስፈፀም እያንዳንዱ ብሔራዊ ድርጅት በከፍተኛ አመራር ደረጃ የሚታይበትን ድክመት በጥልቀት ገምግሞ በግልጽነትና በተጠያቂነት ላይ የተመሰረተ የማስተካከያና የእርምት ርምጃ እንዲወስድ ወስኗል፡፡”

 

%d bloggers like this: