Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)
ይላል የሕወሃት ሊቀ መንበር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል:

ደብረጽዮን ግ/ሚካኤል
የትግራይ ክልል ከስርዓቱ የተለየ ጥቅም እንዳገኘ አስመስሎ ማቅረብም የዘመቻው ዋና አካል መሆኑን አንስተዋል።
ይህ “ህወሓትን ማዳከም ስርዓቱን ለማፍረስ መሰረት ነው” ከሚል ስሌት የመጣ መሆኑን ያነሱት ሊቀመንበሩ፥ ይህም ዘመቻ የትግራይ ህዝብ ላይ ያነጣጠረ መሆኑን ነው ያስታወቁት።
በጠላት ሀይል ተቀነባብሮ እየተነዛ ያለው የሃሰት ሀሳብ ብዙዎችን እያሳሳተ መሆኑ እንዳለ ሆኖ እውነታውን መግለፅ አለመቻል ግን የድርጅታቸው ድክመት ተደርጎ መነሳቱን ገልፀዋል።
በህወሓት እና በትግራይ ህዝብ ስም የሚቆምሩ እና በጥፋታቸው ልክም በህግ ያልተቀጡ ግለሰቦች መኖራቸው የችግሩ ሌላ ምንጭ ነው ሲሉ አንስተዋል።
ሌሎች የኢህአዴግ ድርጅቶች ጣትን ወደሌላ መጠቆመም አንዱ የችግሩ ምንጭ እንደሆነ ይናገራሉ።
እነዚህ ሁሉ ድክመቶች ተደማምረው ውስጣዊ ተገላጭነትን አስፍተዋል ነው የሚሉት።
ለእነዚህ ፖለቲካዊ ችግሮች መፍትሄ ፖለቲካዊ መሆኑን የተናገሩት ዶክተር ደብረፅዮን፥ በትግራይ ህዝብ እና በድርጅቱ ስም የሚነግዱ ግለሰቦችም ለህግ እንዲቀርቡ ያደርጋል ብለዋል።”