ሰበር ዜና: በአቃቤ ሕግ ጉዳያቸው ተይዞ በእስር የሚገኙ የተለያዩ ፖለቲከኞች እንዲለቀቁ ተወስኗል- ጠ/ሚ ኃይለማርያም

3 Jan

Credit: Fana

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)
 
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 25፣ 2010 (ኤፍ ቢ ሲ) የአራቱ የኢህአዴግ ብሔራዊ ድርጅቶች ሊቀመንበሮች በወቅታዊ ሀገራዊና ክልላዊ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመንግስት የመገናኛ ብዙሃን መግለጫ በመስጠት ላይ ይገኛሉ።

በመግለጫው ላይ ከተነሱት፦

ጠቅላይ ሚኒስተር ኃይለማርያም ደሳለኝ: በአቃቢ ሕግ ጉዳያቸው ተይዞ በእስር የሚገኙ የተለያዩ ፖለቲከኞች የተሻለ ሃገራዊ መግባባት ለመፍጠርና የዲሞክራሲ ምህዳሩን ለማስፋት በማሰብ ክሳቸው ተቋርጦ እንዲለቀቁ ተወስነኗል::”

“በደርግ ዘመን በምርመራ ስም ልዩ የጭካኔ ተግባር ሲፈጸምበት የነበረውና በተለምዶ ማዕከላዊ በመባል የሚታወቀው የምርመራ ማእከል እንዲዘጋ ተደርጎ ሙዝየም እንዲሆን ተወስኗል።

በምትኩ አለም አቀፍ ስታንዳርዱን የጠበቀ ዘመናዊ የምርመራ ማእከል በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አዋጅ ተቀቋቁሞ እንደዲሰራ ይደረጋል።”

“በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተቋቋመ ዓለም አቀፍ ደረጃን የጠበቀና የሰብአዊ መብት አያያዝ መስፈርቶችን ያሟላ የምርመራ ተቋም ተመስርቷል”
 

%d bloggers like this: