የቦሌ ክ/ከተማ የሰዓሊተ ምሕረት ምዕመናን በአጋዚ ድብደባና መሣሪያ ጋጋታ ሳይደናገጡ የሕወሃት አማሳኞችን ሲታገሉ ዋሉ! ምዕመናም በሕወሃት ዘራፊዎች ላይ በግልፅ ተነስተው ዋሉ!

5 Jan

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)
 

ሐራ ተዋህዶ እንደዘገበው:-

    * በተባረረው አስተዳዳሪ፣ የፓትርያርኩ እና የሥራ አስኪያጁ በልዩነት መጠባበቅ ኹኔታውን እያከፋው ነው፤

    * ምእመናኑን፣ “ዱርዬዎች” የሚሉት ፓትርያርኩ፣የተባረረው አስተዳዳሪ እንዲመለስ ማዘዛቸው ተጠቁሟል፤

    * ሥራ አስኪያጁ፣ የክፍለ ከተማውን የፖሊስ ኃይል ድጋፍ በደብዳቤ እንዲጠይቅ በማዘዝ ምእመኑን በቆመጥ አስደበደቡ፤

    * በጽናት የተቋቋመው ምእመኑ፣ በጸሎተ ምሕላ እና በዝማሬ ጥበቃውን አጠናክሮ ውሏል፤የተባረረውን አስተዳዳሪ መመለሱ ይቅርና፣“ዛሬ ጠዋት [ጥር 4/2018] በካቴድራሉ ውስጥና አካባቢ ታይቷል፤”መባሉ፤የምእመኑን ቁጣ አብሶታል፤ንቃቱንና ተቃውሞውን አጠናክሮታል፤
   

  Credit: Hara Zetewahido


    * በጠዋቱ የምእመናኑ የጥበቃ መርሐ ግብር ቅይይር አጋጣሚ፣ ወደ ካቴድራሉ ከገባው የክፍለ ከተማው ፖሊስ ጋራ፣ደወል ቤቱን ቀድሞ ለመቆጣጠርና በነቂስ የወጣው ምእመን እንዳይገባ ለመግታት፣ፍጥጫና ትንቅንቅ ነበር፤ተኩስም ተሰምቷል፤

    * ምእመኑ፥“ቤተ ክርስቲያናችን እናታችን ናት፤ ከእርሷ የሚበልጥብን የለም፤” ብሎ በአቋሙ በመጽናት ካቴድራሉን በመቆጣጠሩና በማስከበሩ ቀጥሏል፤

=====================
 

    * የክፍለ ከተማውን ፖሊስ ለማገዝ የተጠራ አድማ በታኝ ፖሊስ፣ እስከ ጊዜ ቅዳሴ በካቴድራሉ ዙሪያ ከበባ ቆይቷል፤

    * ካህናቱ እና የሀ/ስብከቱ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት፣ከምእመናኑ አልተለዩም፤ ጸሎቱ እና ቅዳሴውም አልታጎለም፤

    * የምእመናኑ ተወካዮች፣ “ከሀገረ ስብከቱ ጋራ አነጋግሩን፤ መፍትሔ አሰጡን፤” ሲሉ የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደርን ጠየቁ፤

    * ጥያቄውን መነሻ በማድረግ፣ የሀ/ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ፣ ምእመኑን ወርዶ በማወያየት ችግሩን እንዲፈታ የፍትሕ እና ጸጥታ ቢሮ አሳሰበ፤

    * ሥራ አስኪያጁ፣ “በቂ የፖሊስ ኃይል ካልተመደበልኝ እኔስ ምን ዋስትና አለኝ፤” ብሎ ቢያንገራግርም፣የሀ/ስብከቱን ልኡካን ይዞ ምእመናኑን ለማነጋገር ተስማማ፤

    * ነገ ጧት፥የክፍለ ከተማው ሥራ አስፈጻሚ፣ የሀገረ ስብከቱን ልኡካንና ምእመናኑን በካቴድራሉ ያወያያል፤

    * ምእመናኑ፣ ከነገው የቋሚ ሲኖዶስ ሳምንታዊ ስብሰባም ትኩረትና ማጽናኛ እንጠብቃለን፤ ቢሉም ፓትርያርኩ “ተዉኝ፤ጣልቃ አትግቡብኝ፤ሥራ አስኪያጁ በሚያቀርብልኝ ሪፖርት ውሳኔ እሰጣለሁ፤”ብለዋል ላነጋገሯቸው ብፁዓን አባቶች፡፡

ምድራዊውና የዘራፊዎች ሸሪፍ የሆነው የኢትዮጵያ ሕዝብ የሕወሃት ካድሬ መሆኑን አልታወቀብኝም ብሎ ከሆነ እጅግ ተሳስቷል — እርሱም እንደ ቀዳሚ ሽፍታው ጳውሎስ ቅንዝረኛው ጽዋውን እስኪለጋ!
 

ተዛማጅ፡

  ካድሬው ፓትርያርክ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያለን አካል አክራሪና አሸባሪ ካሉ በውግዘት እንደሚለዩ ቅዱስ ሲኖዶሱ በጥብቅ አስጠነቀቃቸው! የዕለቱ የምልአተ ጉባኤው ውሎ በድንገት ተቋረጠ

  ካድሬው ፓትርያርክ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያለን አካል አክራሪና አሸባሪ ካሉ በውግዘት እንደሚለዩ ቅዱስ ሲኖዶሱ በጥብቅ አስጠነቀቃቸው!
  Ethiopian Orthodox Church clergy in Gojjam and Gondar call for rejection of & dissociation from existing Tigrean Church leadership

  በትግሬነት የተመረጡት ‘የኢትዮጵያ’ ኦርቶዶክስ ፓትርያርክ በሁለት አፍ የቀላመዱበት ዛሬ ሕወሃትን አርበድባጁን የሕዝብ ትግልና የሳቸውን ቅሌት ነገ ታሪክና ትውልድ ምን ያህል ያፍሩባቸው ይሆን?

  በዘራቸው የተመረጡት ካድሬው ፓትሪያርክ ለኢትዮጵያውያን መጨፍጨፍ ግድ ሳይኖራቸው፡ ሕወሃት እንዳይገለበጥ ውግዘትን መሣሪያ አድርገው ቀረቡ

  የኦርቶዶክስ ገቢ በቢሊዮን ቢቆጠርም የምዕመናኑ ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ መቀነሱን ካድሬው ፓትሪያርክ በተሰበረ ልብ ለሕዝብ ይፋ አደረጉ

  አፍንጫን ሲመቱት ዐይን ያለቅሳል ዐይነት ሆኖባቸው ፓትሪያርኩ የቅዱስ ሲኖዶሱን ውሳኔ አገዱ

 

%d bloggers like this: