ለ17-ዓመት ‘የትግራይ ነጻነት’ ጦርነት ሕወሃት የኢትዮጵያን ሕዝብ ካሣ አስከፍላለሁ ይላል! ሌላው ጦር ግንባር!

19 Jan

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)
 
አዲሱ የሕወሃት ተሿሚ ገታቸው ረዳ የተባለው የስብሃት ነጋ ‘የፖለቲካ ክርስትና ልጅ’ ሰሞኑን ከሕወሃትዎች ሰባተኛው ዙር ጸረ-ኢትይዮጵያ የመቀሌ ዱለታቸው ብቅ ብሎ፡ ከላይ የተጠቀሰውን ሃሣብ መፈንጠቁ፣ ሕዝቡ ብዙ ትኩረት ባይሠጠውም ከሰሞኑ የሕዝቡ ግርምቶች አንዱ ነበር።

ወንበዴውና ዘወትር ሃሣቡ ከፍተኛ የዝቅተኝነት ስሜት ከሚንጸባረቅበት ከወንበዴው ሕወሃት ነውና ማንም አላሳሳበም ወይንም ማስደንገጡ አልተሰማም!

የሕወሃትን ቃል አቀባይ ጠቅሶ፣ ኢሣት ሰሞኑን እንደዘገበው ከሆነ፣ ጌታቸው ረዳ — ከዚህ ቀደም በዚሁ መሰል ሥራ ብቁ ባለመሆኑና መባረሩ ሲታወስ፣ አሁን ደግሞ ለኢትዮጵያውያን በል ተብሎ የተላከው ጉዳይ የሚከተለው ነው፦

“የትግራይ ሕዝብ ከማንም በላይ ውድ ዋጋ የከፈለ በመሆኑ መካስ አለበት”፣ የሚለው የወንበዴዎቹ ማደነጋገሪያ ነው!

የሚገርመው፣የኢትዮጵያ የገንዘብ ሚኒስትር አብርሃም ተከሰተ እዚያው አዲሱ ተሿሚና ዶላች አባል ስለሆነ፡ እርሱም በቀን ብዙ ሺህ ብር በውሎ አበል ከሚከፈላቸው ስብሰባ ሲወጣ፣ ገንዘብ ሚኒስቴር ይህን በተግባር እንዴት እንደሚተረጉመው ይነግረናል ብለን ተስፋ እናድርግ። ለጊዜው ግን የእኔን አማራጭ አተረጓጎሞች ልወርውር፦

      * ምናልባትም እስከዛሬ የጦርነት ካሣ ተብሎ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ሕወሃት ከኢትዮጵያ ሕዝብ የወሰደውንና የነጠቀውን ለትግራይ ሕዝብ ሳይሆን፡ የኤፈርት ሂሣብ ውስጥ ከቶት ይሆናል። የሕወሃቶች አኗኗር ወደ አንደኛው ዓለም ደረጃ ስለተመነጠውቀ፡ ይህ ከድህነት ወደ ከፍተኛው የኑሮ ደረጃ መመንጠቅ — ኤኮኖሚስቶች እንደሚሉት — ሃብትና ፍላጎቶች እኩል ስለማያድጉ ለዚፍ ሠፊ ጥማታቸው (appetite) ማርኪያ በጣም ብዙ ገንዘብ ስላስፈለጋቸው አንድ ገንዘብ የሚያሰባስቡበት መንገድ ሊሆን ይችላል፤

      * ሕወሃት በግልባጭ መናገርንም እንደ ፖለቲካ መሣሪያው ስለሚጠቀምበት — አንዳንዴ በኢትዮጵያ አንደነት መፍረስ ዜጎችን እንደሚያስፈራራ ሁሉ — ምናልባትም ሕዝባዊ ተቃውሞውን አዳክሜዋለሁ የሚል መልዕክት በማስተላለፍ — ሕዝቡ ላይ ሥነ ልቦናዊ ጦርነት ማወጁም ሊሆን ይችላል፤

      * የይሉኝታ እንጥፍጣፊዋ ሳትቀር በቅሌት ከተተካበት አካባቢ ይህ መምጣቱ — ኢትዮጵያውያንን እምብዛም አያስገርምም — ምናልባትም ሕወሃትን ለራሱ እንጂ!

ሕወሃቶች ኢትዮጵያን እንደጠላት ሃገር ስለሚመለከቱና ማስገበርን የአሸናፊነታቸውና የበላይነታችው ምልክት አድርገው በፊውዳላዊው ዐይኖቻቸው ስለሚያዩ፣ በቀድሞ መንግሥታት የተተከሉ መሠረተ ልማቶች ሳይቀሩ ከገቡባት ቀን (ከዛሬ 27 ዓመት ጀምሮ) እየነቀሉ ወደ ትግራይ መውስድ የተለመደ ብልግናቸው ነበር።

በአንድ ምሣሌ ይህንን ለመግለጽ፣ ሌሎቹን ሁሉ እንርሳና፣ ከአንድ ዓመት ተኩል በፊት — መንግሥት ነን እያሉም — ከሰሜን ሸዋ የኢትዮጵያ አንዲት ትንሽ ከተማ ውስጥ የሕወሃት ወንበዴዎች የመብራት ኃይል ሠራተኞች ነን በማለት፡ የመብራት ጀኔረተር ነቅለው በጭነት መኪና በጨለማ ወደ ትግራይ ሊወስዱ ሲሉ፡ በጨለማ የተዋጠው የከተማዋ ሕዝብ ተጯጩኾና ተጠራርቶ እንዳስቆማቸው ይታወሳል።

ከጋምቤላ የውሃ ፐምፖች አልቀሯቸውም! በየክፍለ ሃገሩ ከቢሮዎች ውስጥ የጽሕፈት መሣሪያዎች እንኳ አልተረፏቸውም! ይህንን ተራ ዘረፋ ከሚያበራቱት አንዱ ደብረጽዮን ገብረሚካኤል የፓርቲው ኃላፊ ሆኖ ኅዳር ውስጥ መሰየሙ ይታወሳል።

በዚህም በግል አመራሮቹ ራሳቸውን፣ በድምር ደግሞ የትግራይን ሕዝብ ለመያዝ እንዲያስችላቸው፡ ትግራይ ውስጥ በዛ ያሉ የልማት ሥራዎች ተሠርተዋል፤ ወይንም ለፕሮፓጋንዳ የሚበጁ ቁጥሮችን ሕወሃት በትኗል። ለምሣሌ በጤና ባለሙያዎች ዕርዳታ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚወልዱት እናቶች ቁጥር 16 ከመቶ ደርሶ፣ በዓለም ላይ ሃገራችንም በዚህ የሃገሮች ዕድገት ማነጻጸሪያ 117ኛ መሆኗን መረጃ ከተ.መ.ድ. ተቀብለን ዘግበን ነበር

የሕወሃት ምላሽ ለዚህ፣ በ25 ዓመታት ሊያደርጉ ያልቻሉትን ከሁለት ሣምንት በኋላ በፋና ገጽ ላይ ኢትዮጵያ ውስጥ በሆስፒታል ወይንም ጤና ጣቢያ የሚወልዱት እናቶች ቁጥር 60 ከመቶ መሆኑ ከታች እንደሚታየው ለዓለም ተነገረ! በእነዚህ ሰዎች አሠራር አፍሬያለሁ!

ሕወሃት በ2013፡ ከትግራይ ውጭ በጤና ባለሙያዎች አዋላጅነት የሚወልዱት እናቶች ብዛት አሥር ከመቶ ዙርያ ሆኖ፣ የትግራይ ግን 54 ከመቶ ደርሶ ስለነበር፣ ያንን ለማምታት የተደረገ ደባ ነበር። የሚያሳዝነው፣ በቢል ጌትስና ባለቤቱ ስም ዕርዳታ የሚሠጠው ጌትስ ፋውንዴሽን የሐውሃትን ቁጥር በማስተጋባት ሃገራችን ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰብን ነው። ምናልባትም 98 ከመቶ ኢትዮጵያውያን እያለ በፋውንዴሽኑ የሚቀጥራቸው ትግሬዎች ስለሆኑ እንደሆን አላውቅም!

እነርሱም ቢሆኑ ለድርጅቱ በወሸት ላይ የተመሠረተ ዴታ ይሠጡት ይሆናል። እንደዜጎች ግን ሃገራችን ምንም ደሃ ብትሆን ድህነታችንን ፊት ለፊት ተጋፍጠን መፍትሄ መሻት አዋጭ ነው ብለን እናምናለን! የሃሰቱ የቁጥር ክምር ኢትዮጵያን የትም አያደርሳትም — የሃሰት ቁጥሮች የፖሊሲ መፍትሄዎችን ከማራቅ ውጭ!

አሁንም ይኽው ተግባራቸው አልቆመም — የተተከለው ተነቅሎ ቢያልቅም! በወረቀት ላይ ያሉትን መንግሥታዊ ስምምነቶችም አልማሯቸውም። ከውጭ የሚገኘውን ዕርዳታና ብድር በዘዴ ወደ ትግራይ በየጊዜው እያዞሩ ናቸው።

አንድ የሚያስገርም ምሣሌ ልጥቀስ።

ከ2015-2020 በሚቆየው የብድር ስምምነት መሠረት፣ የአፍሪካ ልማት ባንክ ለኢትዮጵያ አራት ከተሞች (አዳማ፣ አድዋ፣ ብቸናና ጎንደር) የውሃ ሥራዎች ለመሥራት የመጀመሪያውን ክፍል $102.42 ሚሊዮን እንደሚፈጅ ታውቆ፣ ይህ ሥራ በብድር ገንዘቡ ለአራቱ ከተሞች እንደሚከናወን ፕሮጂከቱ ቢያመለክትም፣ እስካሁን ባለው ሂደት፣ ዋነኛዋ ውሃ ተጠቃሚው አድዋ የሚገኘው የሕወሃቱ አልሜዳ ሆኖአል። ፕሮጀችቱና የገንዘብ ፈሰሱ እስከ 2020 የሚቀጥል ቢሆንም፡ የውጭ ዕርዳታው ተጠቃሚው ሕወሃት፤ ዕዳ ክፋዮቹ ግን የኢትዮጵያ ግብር ከፋዮች ሆነዋል።

አበዳሪው የአፍሪካ ልማት ባንክም ይህንን ስምምነትና የፕሮጀክቱና ዓላማ ሲያብራራ እንዲህ ይላል

“Increased availability of water in the towns is also expected to trigger expansion of existing investments and arrival of new ones. As in the case of Almeda textile factory in Adwa – a major beneficiary of the program, which employs a large proportion of women, it is expected that employment opportunities for women will increase.”

ሕወሃቶች አዲስ አበባን ከመያዛቸው በፊት ትግራይ ውስጥ ከነበሩ የመንግሥት ባንኮች ጭምር ያለውን ገንዘብ እየዘረፉ እንደመጡ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ያስታውሳል። በጠመንጃ ሃገሪቱን ከያዙም በኋላ፣ ራሳቸውን በእያንዳንዱ የመንግሥት መ/ቤቶች በኃላፊነት በመሰየም፣ ከባንኮች በብድር ስም ገንዘብ እየወሰዱ፣ ትግራይ ውስጥ የመንግሥት ሣይሆኑ በግል ወንበዲዎች ባለሃብቶች የሆኑባቸው ድርጅቶች ማቋቋሚያ የተደረገው ከኢትዮጵያ ባንኮችና ከመንግሥት ካዝና መሆኑን ሠነዶች በወቅቱ አሳይተዋል።

በኢትዮጵያ መ/ቤቶች የት ነው ትግራዊዎች አመራር ላይ የሌሉት — በእነርሱ የሥውር አሠራር ጭምር ከላይ ባይሆኑ ኩችናም ሆነው ለግል ጥቅም ‘አመራር እየሰጡ’— የተማሩትም ቢሆኑ እንኳ — ብሔራዊነትንና አመራር መማራቸውንና አመራር ችሎታን የግል ስግብግበነት አሳጥቷቸዋል!

በዚህም ለጋራ ጥቅም እያንዳንዱን ኢትዮጵያዊ የማስተባብር ሥራ ከመሥራት ይልቅ፣ ራሳቸውን ብቻ ለመጥቀም ሃገሪቷን ሲዘርፉ፡ በትግራይ ነጻነት ስም ድልድዮቻችንንና መሠረተ ልማቶቻችንን ሲያፈርሱ ኖሩ።

አሁን ካሣ ክፈሉ ይሉናል!

እነዚህ ወንበዲዎች እኮ ራሳቸው ተጠያቂ መሆን የሚገባቸው ናቸው። የሃገሪቱን ጦር ኃይል በትነው፡ የወንበዴው ሽፍቶች የሃገሪቱ ጦር ኃይል ሆኑ። ኢትዮያዊነት የማይቀበሉት ጉዳይ በመሆኑ፡ የጦሩን አመራር በሙሉ ትግራዊ አድርገው፣ ጦር አዛዦቹ በሃገር ምዘበራ ላይ ተሰማሩ!

በፋሽስታዊ አስተሳሰባቸው መንስዔነት የተበተነው የኢትዮጵያ ሠራዊት ከደሞዙ ተቆራጭ የነበረውን የጡረታ ገንዘብ እንኳ እንዳይከፈለው ተወስኖበት ተበተነ። በአንጻሩ — ቀደም ሲል እንዳልኩት ሁሉንም ነገር ቅሌት ባላበሱበት ሁኔታ — እያንዳንዱ የሕወሃት ሽፍታ ጡረታው የሚታሰበው — 17 ዓመት በበረሃ ከነበረበት ጊዜ አንስቶ ነው! ይሁን እንኳ ቢባል፣ ዛሬ የመንግሥት ሬኮርዶች በመበተን በሚታወቀው ሕወሃት መዝገብ ነው የሚከፈላቸው ወይንስ 17 ለሁሉም ሃይማኖት ነው — ጥቅማ ጥቅሞች ላይ ሲመጣ የእነርሱ አሠራር ባህሪ ነውና!

የውጭ ሰላም ማስከበርም (international and regional peacekeeping)፡ የትግሬዎች መጠቃቀሚያ ሆኖአል። ሶማልያ ላይ ግን ለሽብር ኃይሎች መሣሪያ እንደሚሸጡ (ሜቴክ ከጋፋት በአንቶኖቭ አውሮፕላን ለሶማሌ ጦር በሚል ሽፋን) እያከፋፈለ መሆኑን የተባበሩት መንግሥታት መረጃ ሰብሳቢዎች ቢይዙም፣ እስከዛሬ የጸጥታው ምክር ቤት እርምጃ መውሰድ እንዳይችል ተደርጓል!

ከኢትዮጵያ ተልኮ አልሸባቦች የሚጠቀሙበት መሣሪያ ሶማሊያ ገበያ ውስጥ ለገዥ በሚሸጥበት ጊዜ የተ.መ.ድ. መርማሪዎች ያነሷቸው ፎትግራፎች:

ETHIOPIAN-MADE RIFLE (CREDIT UNITED NATIONS S/2014/726)


ETHIOPIA-MADE RIFLES FOUND AL-SHABABAAB HNADS (S/2014/726)

በሕወሃት ለመርህና ለሕግ ተገዥ አለመሆን ምክንያት፡ የሕወሃትን ጦር ከሶማሊያ መውጣት አበክሬ እደግፋለሁ፤ በተለያዩ ጽህፎቼም ዘርዝሬያለሁ። በቅርቡም በዚያው ዙርያ የወጣው ጽሁፌ ይህንኑ አሥምሮበታል፦
Ethiopia on the brink. Everyone has failed Somalia— its politicos, Horn nations, AU, UN, the West bear huge responsibilities, TPLF most of all! PART I (1)

በብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ አማካይነት ወደ ሶማልያ በአንቶኖቭ ከሚላኩት መሣሪያዎች የሚገኝ ገቢ ሕወሃት ወታደራዊ ባለሥልጥኖች ኪስ ነው የሚግባው። ወደ መካከለኛው ምሥራቅ በቀጥታና በሰዎች አማካይነት እንደሚያስተላልፉ የሚያነሱ አሉ።

ሕወሃት ከሶማልያ ካልወጣ፣ ሶማልያ ሰላም አትሆንም! ሶማልያ ሰላም ካልሆነች ደግሞ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ለፈላጭ ቆራጮች ፍላጎት ማርኪያ መሆኑ ይቀጥላል፤ የሃገሪቱም ዕድገት የታቀበ ይሆናል።

ሶማልያ ውስጥ የሕወሃት ዓላማ የሶማልያን መንግሥት ማዳከም ነው። የአሜሪካንን ድጋፍ ለሕወሃት ለማስቀጠል፣ ሕወሃት ሽብርተኞች ተብለው የተፈርጁትን እነአልሸባብና ሌሎቹን አክራሪዎች እስክ ድረስ ይዋጋል። አልሸባብ ከተማ ውስጥ እንዳይገባ ሕወሃት በመከላከል ቢረዳም፡ ግቡ ግን ሶማልያ በአሸናፊነት እንዳትወጣ አይደለም። ይህም አልሸባብ እንዳይሞት ረድቶታል። በሕወሃት አስተሳሰብ የተጠናከረች ሶማልያ በኦጋዴን በኩል አታስቀምጠኝም፣ ከሌሎችም ተቃዋሚ ኃይሎች ጋር ታብርብኛለች የሚል ሥጋት አለው።

በሌላ በኩል ደግሞ ሕወሃት የአካባቢውን ሰላም ማናገቱንና ድህነቱ እንዲቀጥል ያደርገዋል — ሶማልያም ውስጥ መገንጠልን እያበረታታ ነው። ለምሳሌ ሶማሌላንድ ከውጭ መንግሥታት ጋር እንደ መንግሥት ግንኙነትና ውክልና ያላት ከኢትዮጵያና ከጅቡቲ ጋር ነው። ሶማሌላንድም የሕወሃት የቅርብ አጋር በመሆኗ፡ በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳዮች በመግባት፣ ማለትም ኦሮሞችን በመያዝ፣ በማሠርና ማንገላታት ትታወቃለች። በቅርቡም በኦሮሚያና ሶማሌ ክልሎች መካከል ግጭት ሲካሄድ በክልሏ የተጠለሉት ላይ ጥቃት ፈጽማ ማስወጣቷ ይታወሳል።

አንዳንድ የሃገሪቷ ጋዜጦች እንደጻፉት፡ ሕወሃት ያለውን በመያዝ የግብጽ ድጋፍ አላቸው የሚል አስተያየቶችን ሠንዝረዋል። ይህም ከላይ ከተነሳው ሃሣብ ጋር የተያያዘና የሶማልያ ጠላት ወዳጄ ነው የሚል ይመስላል!

አሳሳቢው የኢትዮጵያ የፖለቲካ ሁኔታ ቀጣይነት

አስፈሪው ነገር፣ በሃገራችን ውስጥ አሁን ያለው አስከፊ የፖለቲካ ሁኔታ፡ በአስከፊነቱ ይቀጥላል። አንደኛ የሕወሃት አስከፊ ፖሊሲዎች መገለጫ በድርጅቱ አመራር ሆነው የተመረጡት ግለሰቦች ናችው። ደብረጽዮን የሚታወቀው በነፍሰ ገዳይነቱና ዘራፊነቱ ነው። ይህ በተራ ሽፍትነት ዘመኑ ጭምር የታወቀበት ባህሪው ነው። በቅርቡ የተጋለጠው የዝሙት ባህሪው የግል ችግሩ ቢሆንም — የሃገሪቱን የውጭ ምንዛሬ ለእርሱ ዝሙት ቱሪዝሙ ማባከኑ ኃላፊነት የጎደለው ሊጠየቅበት የሚገባ ባህሪ ነው!

የሃገሪቱ የፖለቲካ ችግሮች ይባባሳሉ ከምልበት ምክንያትም አንዱ የሕወሃት አመራሮች ብልግናና ደካማነት ነው። የሃገሪቱ የገንዘብ ሚኒስትር እዚያ ውስጥ ነው። እርሱም በጉበኝነትና የዘር ጉዳይ ላይ የታወቀ አክራሪ የአርከበ ዕቁባይ ቀኝ እጅ ነው። የኢሣቱ ኤርምያስ ለገሠ ባካፈለን መረጃ መሠረት፣ ግለሰቡ የአዲስ አበባን መሬት ካቀረማመቱት የሕወሃት ግለሰቦች ቀደምት ተጠቃሽ ነው!

የነጌታቸው ረዳም ጸረ-ኢትዮጵያዊነት ከነጌታቸው አሰፋና ሞንጆሪኖ የማያንስ፡ ከቀሪዎቹ ጋርም በዘረኝነቱ ተመሳሳይ በመሆኑ ነው!

ሁለተኛው የሃገሪቱ ሁኔታ የሚያሳስብበት ምክንያት፡ መሪዎች ነን የሚሉት የሕወሃት ሰዎች በግለስብ ደረጃም ሆነ በድርጅት ጤነኛ ባለመሆናቸው ነው።

በሕዝባዊ ተቃውሞው መጠናከር ምክንያት ሕወሃት ምንም ዐይነት ተለማማጭነት ቢያሳያም — ሳይኮሎጂስቶች እንደሚሉት ጤነኛ ያልሆነ የጸጸትና ተለማማጭነቱ (UNHEALTHY REGRET & GUILT) ፖለቲካዊ ቢሆንም — የፖለቲካ ጤንነቱ የተቃወሰ መሆኑን ስለሚያመለክት ነው።

ሥልጣን ክፉኛ ስለጣማቸው፡ በሁሉም መንገድ ሃገሪቱን ለማንበርከክ በመዘጋጀታቸው ነው እንደሚታየው የተሳከሩት!

በዚህ ሁሉንም ኢትዮጵያዊ ጎድተውናል። አማራው፣ ኦሮሞው፥ ደቡባዊው ወዘተ…ከሁሉ በላይ የተጎዳው ግን የትግራይና ቀሪው የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው። የትግራይ ሕዝብ በበቂ ምክንያት በሕወሃት ላይ እየባሰ የመጣው ገፊት ቀማሽ ሆኖአል። ሁሉም የትግራይ ሕዝብ ይህ ይገባዋል ማለት ባይቻልም፣ ኢትዮጵያውያን በስማቸው በሚነግደው ድርጅት ሲገደሉና ሲጠቁ “እስየ!” ያሉት ከጥቂቶች በላይ ናቸው። ይህ ትግራዊያንን የኢትዮጵያዊያን ጥላቻ ማረፊያ በመሆን ትግሬዎች ተጎድተዋል።

ኢትዮጵያውያንም ወገኖቼ በሚሏቸው ትግሬዎች በመወጋታቸው ኃዘናቸው ጥልቅ ነው! በደርግ ጊዜ የኢርትራና የትግራይ ሰዎች ታርጌት በነበሩበት ሰዓት — በዘራቸው በኩል በመጣው ጥቃት ከእነርሱ ጋር እንደነበረና ቤቱና ልቡን ከፍቶላቸው ነበር! ዛሬ እነርሱ ግን ከሰውነት ይልቅ፣ ከወንድማማችና እህትነት ይልቅ ዘራቸውንና ጥቅማቸውን መርጠው ለወግናቸው ጀርባቸውን ሠጥተዋል!

ከዚህ በታች የሠፈረው ጽሁፍ ይህንኑ አፍቅሮተ ሕወሃት ያሠከራቸውን ትግሬዎች ስሜት የሚያሳይ ነው!
================
 

“Tigray Must Be Paid War Reparations”

Postby Tigray People Fight » 09 Dec 2017, 18:36

Throughout Ethiopia history the Tigray paid enormous sacarifice with thier life and resources to defend ungrateful Ethiopians from various foreign Invaders.The Tigray People paid thier unreplaceable life to Liberate the entier Ethiopia during the bitter 17 years war with thier precious Life,blood,Sweat,Tears,scream and much needed meager resources.Thus The Entier Tigray People must paid huge sum amount of money to compensate them for thier losses of materials and human life despite human life can not be replaced since it is priceless.The monetary compensation for Time at people will help them in small scales day to day life.Also Tigray People and Tigray state should be the biggest recpients Of federal budget to restore Tigray People life that was immesurably impacted during the numerous wars the Tigray people fought against powerful heavily armed combatants.Nothing is Free in this World.Anyone against this proposition is evil anti Tigray and they must be arrested and punished.All the federal government,and Ethiopia government Tigray People must be the majority since it is the Tigray People who sacarifieced To Liberate all Ethiopia while GALLA and Amhara were breeding ugly [deleted] children to call themselves today “majority” to be in power and get largest federal budget which is a shame.It should be who paid the ultimate sacarifice to free all Ethiopians should get the benefits of thier hard sacarifice and hard won victories which is the mighty Tigray People.

Tigray Will Develop on The Grave yard of our Enemies!!!!
 

በኢንተርኔት ከታህሳስ ጀምሮ እየዞረ ያለ የትግራዊነት መለክያ የሆነ የስሜት መግለጫ ነው። አንድም ኢትዮጵያዊ የሆነ ትግራዊ ወጥቶ ይህ ጽሁፍ እኔን አይወክለኝም ያለ የለም!

እንደታሪክ ሂደት ሁሉ፣ የተለወጠ ቀን መጥቶ እንዳያስተዛዝበን የሚያሠጋ ደረጃ ላይ ነን!
 

%d bloggers like this: