የለማ መገርሣ አስተሳሰብ በማንኪያ!     የሕወሃት ወንበዴዎች ግን አፍራሽነታቸውን ያቆማሉ ብሎ ማመን እጅግ ያስቸግራል!

24 Feb

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)


 

ፋና እንደዘገበው

“በፌደራል ደረጃ የአመራር ዕድልን የሚያገኝ ሰው ሁሉንም የሃገሪቱ ብሄር ብሄረሰቦች በአንድ ዐይን የሚያይ ይሆናልም ብለዋል።

የሕዝብ ክብር የሚመጣው እኩልነትንና ፍትሃዊ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ ሲቻል መሆኑን አቶ ለማ ተናግረዋል።

የሕዝቡ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ጥያቄ ሊመለስ ይግባዋል ያሉት አቶ ለማ፥ የኦሕዴድ ሥራ አስፈፃሚም ይህንን በጥልቀት በማየት የክልሉ አመራርና ማዕከላዊ ኮሚቴው በመግባባትና በመተማመን እዚህ ውሳኔ ላይ ደርሷል ነው ያሉት።

የኦሮሞ ሕዝብም ሆነ የኦሕዴድ ጥያቄ በክልል ሳይወሰን በሀገሪቱ አመራር ቦታ ላይ ተሳትፎ እንዲኖረው ከሕዝቡ ጋር ሰፊ ትግል ሲደረግ መቆየቱን አስታውቀዋል።

ከዚህም መነሻነት በፌደራል መንግስት ውስጥ የአመራር ድርሻ ሊኖረን ይገባል ስንል የክልላችንን ጉዳይ በመርሳት ሳይሆን፥ በታሪክ ውስጥ የተገኘውን ዕድል የሰፊውን ሕዝብ ክብር በጠበቀ ሁኔታ እንዴት መሥራት ይኖርበታል የሚለውንም በጥልቀት ማዕከላዊ ኮሚቴው መገምገሙን ነው የገለፁት።

ይህ የተገኘው ዕድል የሚሰጠውን ኃላፊነት የሁሉንም ሕዝብ ተጠቃሚነት ባረጋጠ መልኩ ለመወጣት አርቆ ማሰብም ያስፈልጋል ነው ያሉት።”

ፋና ከቃለ መጠይቃቸው ያልጠቀሰው:

“ኦሕዴድ ጠቅላይ ሚኒስትር የሚሆነው ሰርቆ ኦሮሞን ሃብታም ለማድርግ አይደለም። ለፍትህ፣ ለእውነት ሁሉንም ሕዝብ እኩል አገልግሎ ሕዝባችንን እንዲያስከብር ነው። የሚሄደውም ሰው በዚህ ደረጃ መሆን አለበት። ሕዝባችንን ወክሎ ሃገራችንን ለማገልገል ዕድል የሚያገኝ ሰው በዚያ ደረጃ የሚሰራ መሆን አለበት።

እኔን በተመለከተ በኦሮሚያ ደረጃ የጀመርኳቸው ነገሮች አሉ። የተሻለ ወንበር ስለተገኘ ብቻ የጀመርኩትን ከግብ ሳላደርስ እሚሄድ ከሆነ ጥሩ አይደለም። ሕዝቤ በጀመርኩት ነገር ተደስቶ ለማንም ያልሰጠውን ፍቅር ሰጥቶኛል። ስለዚህ ይህንን በሃሳብ ደረጃ አይቶ ፍቅር የሰጠኝን ሕዝብ ወደ ተግባር ቀይሬ መካስ እፈልጋለሁ።”

/OBN video
 

%d bloggers like this: