ወደ ውጭ የሚላክ ሸቀጣ ሸቀጥ በመጥፋቱ አብዛኛው የኢትዮጵያ አየር መንገድ የጭነት አገልግሎቱ መቋረጡ ታወቀ

8 Mar

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)
 
የካቲት 29 ቀን 2010 ዓ/ም (ኢሳት) በኦሮምያ የሚካሄደውን የስራ ማቆም አድማ ተከትሎ ከክልሉ የሚመጡና ወደ ውጭ አገር በኢክስፖርት ስም የሚላኩ እቃዎች በመቋረጣቸው የኢትዮጵያ አየር መንገድ የካርጎ አገልግሎት በአብዛኛው ስራ ማቋረጡን ምንጮች ገልጸዋል።

አመጹ ከመጀመሩ በፊት ዕረፍት ያልነበረው የአየር መንገዱ የጭነት አገልግሎት፣ በአሁኑ ሰዓት ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ አገልግሎት እየሰጠ ባለመሆኑ በአየር መንገዱ ውስጥ የሚሰሩ ሰራተኞች ይናገራሉ።

በጭነት (ካርጎ) አግልገሎት ላይ የሚሰሩ የአየር መንገዱ ሰራተኞች፣ ብዙዎቹ ዕረፍት እንዲወስዱ መደረጉን ምንጮች ገልጸው፣ የስራ ማቆም አድማው የሚቀጥል ከሆነ በአየር መንገዱ ህልውና ላይ ቀላል የማይባል ተጽኖ ይፈጥራል ብለዋል።

በተከታታይ የተደረጉት የሥራ ማቆም አድማዎች በቡና፣ በጫት፣ በተለያዩ ማዕድናት የንግድ እንቅስቃሴ እንዲሁም በቱሪዝም ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ያሳደሩ ሲሆን፣ በአገሪቱ ያለውን የውጭ ምንዛሬ ዕጥረትም እንዳባባሱት የሚደርሱን መረጃዎች ያሳያሉ።
 

Leave comment

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: