የኢትዮጵያ ዕዳ መሸከም ጫናና ወለድ የመክፈል አቅም አስጊ ደረጃ ላይ ደርሷል!

15 May

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

ከኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ ማበር 

ከሳህራ በታች ያሉ የአፍሪካ ሃገራት የዕዳ ጫናቸው እያደረ ወደ ሰማይ መጥቶል ምክንያቱም ከፍተኛ ብድርና ያጋጠማቸውን ኪሳራና እጥረት ለመሸፈን ሲሉ በእዳ ይዘፈቃሉ ምንም እንኮን አጠቃላይ የኢኮኖሚ እድገት እያደረጉም ቢሆን ይላል ዓለም ዓቀፍ የገንዘብ ድርጅት ባወጣው ሪፖርት፡፡ የአፍሪካ አገራት ከዓለም ዓቀፍ የብድር ገበያ ብድር ማለብ ቀጥለዋል እንዲሁም የውጭ ምንዛሪ ብድር ሪከርድ ሰብረዋል ባልተረጋጋው የኢንቨስተሮች ፍላጎት ለቀጣይ ምርት ሂደት፡፡  የዓለም ዓቀፍ የገንዘብ ድርጅት የአፍሪካ ዴሬክተር አበበ ዓዕምሮ ስላሴ ለሮይተር እንደገለጡት ድርጅቱን ያሳሰበውና የእዳው ጫና የእድገቱ ጭማሪ ከአማካዮ በላይ መሆኑ ነበር፡፡ ድርጅቱ የአህጉሪቱ የኢኮኖሚ እድገት 3.4 ከመቶ በ2018እኤአ ሲገመት በ2017እኤአ ከነበረው 2.8 በመቶ ዓለም ኣቀፍ እድገት የምርት ዋጋ መጨመር እንደሚኖር ገልፀዋል፡፡ ምንም እንኮን ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ሃገራቶች   40 በመቶ አካባቢ የዕዳ ጫና በከፍተኛ አደጋና ስጋት ውስጥ ይገኛሉ፣ እዳቸውን ለመክፈልም ከፍተኛ ዋጋ ይከፍላሉ፡፡IMF warns of rising African debt despite faster economic growth (REUTERS- Kwasi Kpodo, May 8,2018)

“Sub-Saharan Afrian nations are at growing risk of debt distress because of heavy borrowing and gaping deficits, despite an overall uptick in economic growth, the International Monetary Fund.

African government issued a record $7.5 billion in sovereign bonds last year, 10 times more than in 2016. And they have issued or plan to issue over $11 billion in additional debt in the first half of 2018 alone, the report said. Foreign currency debt increased by 40 percent from 2010-13 to 2017 and now accounts for about 60 percent of the region’s total public debt on average, IMF data showed. Average interest payments, meanwhile, increased from 4 percent of expenditures in 2013 to 12 percent in 2017. Six countries- Chad, Eritrea, Mozambique, Congo Republic, South Sudan and Zimbabwe- were judged to be in debt distress at the end of last year. And the IMF’s rating for Zambia and Ethiopia were changed from moderate to “high risk of debt distress.”   ”

አይኤምኤፍ፣የኢትዮጵያየዕዳመሸከምጫናናወለድየመክፈልአቅምአስጊደረጃላይደርሶልአለ!!!

‹‹የኢትዮጵያ የዕዳ መጠን እየጨመረ ነው›› ግንቦት 2 ቀን 2010ዓ/ም (ቢቢሲ አማርኛ ዜና ሜይ 10 ቀን 2018ዕኤአ)

አለም አቀፍ የገንዘብ ተቆም አይ ኤም ኤፍ ባወጣው የአፍሪካ ሃገራት  ምጣኔ ሀብታዊ ዘገባ፤ የኢትጵያ የእዳ ጫና መጠን ከአጠቃላይ የሃገር ውስጥ ምርት 56.2 በመቶ ድርሻ እንደሚይዝ ገለፀ፡፡  ባሳለፍንው አመት የ10.9 በመቶ እድገት ያስመዘገበችው ሃገር ይህን ያክል ዕዳ መሸከሞ አስጊ የሚባል ደረጃ ላይ እንደሆነች ያሳያል ብሎል መግለጫው፡፡ ከሳህራ በታች የሚገኙ የአፍሪካ ሃገራት በፍጥነት በማደግ ላይ የሚገኘውን ምጣኔ ሃብታቸውን ለማሥቀጠል ሲሉ ከፍተኛ የሆነ ዕዳ ውስጥ እየገቡ እንደሆነ በየዓመቱ የሚወጣው ዘገባ ያትታል፡፡ 40 በመቶ የሚሆኑት ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው የአፍሪካ ሃገራት ከፍተኛ የሚባል የዕዳ መጠን አስመዝግበዋል፤ ወይም ወደዚያ እየተጠጉ ነው የሚለው ዘገባው እነዚህ ሃገራት በቅርብ ጊዜ ውስጥ የማይወጡት ችግር ይገጥማቸዋል ሲል ይተነብያል፡፡ ኢትዮጵያ እና ዛምቢያ ከአጠቃላይ ሃገራዊ ምርታቸው ጋር ያተመጣጠነ ዕዳ እያስመዘገቡ መሆኑን የዓለም አቀፍ ተቆም ጥናት ያሳያል፡፡ በ2016 የኢትዮጵያ ዕዳ መጠን ከሃገራዊ አጠቃላይ ምርቶ 55 በመቶ የነበረ ሲሆን በ2017 ደግሞ ቀላል የማይባል ለውጥ በማሳየት ወደ 56 በመቶ አድጎል፡፡ ኢትዮጵያን ጨምሮ አብዛኛዎቹ የአፍሪካ ሃገራት አሁንም የመሠረተ ልማት ሥራዎቻቸውን ለማስቀጠልና ማህበራዊ ዋስትናን ለማረጋገጥ ወደ ብድር መግባታቸው አይቀርም የሚለው ዘገባው ቀጣይነት ያለው እድገት ማስመዝገብ ካለባቸው ግን የብድር መጠናቸውን መቀነስ ግድ ይላል፡፡ በሌላ በኩል ኢትዮጵያ ውስጥ ለመሠራታዊ ፍጆታ የሚውሉ እቃዎች ዋጋ ከቀን ወደ ቀን እያሻቀበ መጥቶል፡፡ በ2016እኤአ የሃገሪቱ አጠቃላይ የመሠረታዊ ፍጆታ ዋጋ በ6.7 በመቶ ብቻ ያደገ ሲሆን በ2017እኤአ ግን ከእጥፍ በላይ በመጨመር 13.6 በመቶ እድገት አሳይቶል፡፡››  የአፍሪካ አገራት በእዳ ጫና የተነሳ ለወሰዱት ብድር ወለድ መክፈል እማይችሉነት ደረጃ ደርሰዋል፡፡

Africa’s Public Debt seen Exceeding 50% of GDP in 2017, IMF says (Bloomberg- David Malingha, 0ct 30,2017)

“The median level of government debt in Sub-Saharan Africa will probably rise to more than 50 percent of gross domestic product this year, increasing strain on the financial sector and limiting much-needed stimulation for growth, the International Monetary Fund said. … Dollar- denominated bond issuance from the region’s markets was about $4.6 billion in the first half of this year compared with $750 million for the whole of 2016, the IMF’s African Departmnet Director Abebe Selassie said by phon before the release of the report. “High levels of public debt can be quite harmful,” he said. “ The debt-servicing cost can be a major source of drain of resources that could otherwise be used.” ዓለም ዓቀፍ የገንዘብ ድርጅት፣ የአፍሪካ ሃገራት የእዳ ጫና ባለፍት 18 ዓመታት ውስጥ ያልታየ ሲሆን ፣ ለወሰዱት ብድር ወለድ ለመክፈል እንዲረዳቸው ከፍተኛ ታክስ መሰብስብ ይኖርባቸዋል፡፡ በተለይ ከሳህራ በታች ያሉ ሃገራት በአዲስ የዕዳ ጫና ዳፍንት ተመተዋል በዚህም ምክንያት 40 በመቶ የሚሆኑት ሃገራት በዕዳ ጫና ስቃይ ውስጥ ይዋኛሉ፣ በአምስት ኣመት ውስጥ እዳቸው በእጥፍ ጨምሮል፡፡ ስምንት የአፍሪካ አገራቶች  ለወሰዱት ብድር ወለድ ለመክፈል ባለመቻላቸው  ከዓለም ዓቀፍ የመበደር መብታቸውን አጥተዋል፡፡  ኣለም አቀፋዊ የእዳ ስረዛ ዘመቻ ሃብታም ሃገራት ለደሃ ሃገራት የሚያደርጉበት ዘመን አብቅቶል ምክንያቱም ደሃ ሃገራት የተበደሩት ከንግዱ ህብረተስብ ቱጃር ባለፀጎች በመሆኑ ምህረት የለሽ ነው፡፡

‘’ IMF officials at the spring meetings in Washington have urged African countries to increase the efficiency of public expenditure, hand over public investment to the private sector, and fully implemenet fiscal consolidation plans, including seeking new revenues from consumer taxes.’’(FINANCIAL TIMES)

የኢትዬጵያየውጪብድርክምችት፣ ከብሄራዊ አማካይ ጠቅላላ አመታዊ ምርት ድርሻ በ2011 እኤአ 19.9 በመቶ የነበረ ሲሆን በ2014 እኤአ 27 በመቶ ነበር፡፡ የመንግሥታዊ ልማት ዘርፎች ብድር  ከብሄራዊ አማካይ ጠቅላላ አመታዊ ምርት ድርሻ በ2011እኤአ 20.9 በመቶ የነበረ ሲሆን በ2014 እኤአ 42.0 በመቶ ሆኖል፡፡ በ2016/17 እኤአ የህወሓት መንግስትና ብሄራዊ ባንክ ባለሞሎች የሃገሪቱን ልትወጣ በማትችለው የውጪ ብድር ክምችት ከተው ኢኮኖሚውን አዘቅት እንደሚከቱት አጥኝዎች ተንብየዋል፡፡ ለዚህም ግልፅ ማሽረጃ የ2009 ዓ/ም ዓመት እቅድና አፈጻጸም፣ በተለይ የውጪ ንግድ ገቢ ማሽቆልቆል፣ የውጪ ብድር መክፈል አቅም መሽመመድና የውጪ ምንዛሪ እጥረት በቀጣይነት ተከስቶል፡፡ በ2008ዓ/ም የውጭ ዕዳ ክፍያ 1 ቢሊዩን ዶላር ለመክፈል ተገዶል፡፡ የወለድ ክፍያው በዓመት ከ350 ሚሊዩን ዶላር ከፍ ብሎል፡፡ በ2009ዓ/ም የውጭ ዕዳና የወለድ ክፍያ 1.5 ቢሊዩን ዶላር ለመክፈል ተገዶል፡፡ የኢትዬጵያ የውጭ ብድር 40 እስከ 50 ቢሊዩን ዩኤስ ዶለር ሲገመት ይህውም ከአመታዊ አጠቃላይ የአገር ውስጥ ምርት($69) ቢሊዬን ዩኤስ ዶለር (GDP) 58% እጅ ይይዛል፡፡

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ›› ይነሳ!!! የህግ ልዕልና በኢትዮጵያ ይስፈን!!!

የፖለቲካ እስረኞች ይፈቱ!!!

ምንጭ: Ethiopianexplorer.

 

%d bloggers like this: