የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ከፖለቲካ ወገንተኝነት በፀዳ መልኩ እንደሚንቀሳቀስ አዲሱ ድሬክተር ጄኔራል አደም መሃመድ አስታወቁ!

19 Jun

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

*     መንግሥት በጀመረው የለውጥ ጉዞ ሕገ መንግሥቱንና ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን ከማገልገል አኳያና የተጣለበትን ተልዕኮ ለመወጣት ብቃት ያለው የብሔራዊ  መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ይደረጋል

*     ብሔራዊ  መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ሕዝብን እኩል የሚያገለግል ተቋም ለማድረግ አቅጣጫ ተቀምጦ ወደ ሥራ ተገብቷል

*      ሕውሃት ለአመራሩ ተጠቃሚነትና ፖለቲካው  በኢትዮጵያ  የዘራው  መርዛማ የአንድ ዘር የበላይነት ሊያከትም ነው!

አዲስ አበባ፣ ሰኔ፣ 12፣2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የብሄራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ከፖለቲካ ወገንተኝነት በፀዳ መልኩ እንደሚንቀሳቀስና እንደሚሰራ አዲሱ የአገልገሎቱ ድሬክተር ጄኔራል አደም መሃመድ አስታወቁ።

በዛሬው ዕለት ድሬክተር ጄኔራሉን ጨምሮ አዲሱ የአገልግሎቱ አመራር ከተቋሙ ሠራተኞችና ባለሙያዎች ጋር ትውውቅ አድርገዋል።

ድሬክተር ጄኔራል አደም መሃመድ (ፋና ፎቶ)

በዚህ ወቅትም ውይይት የተካሄደ ሲሆን፥ ድሬክተር ጄኔራል አደም መሃመድ  ሕገ መንግሥታዊ ስርአቱን ከአደጋ ለመጠበቅ በሚደረገዉ ጥረት ተቋሙ ተልዕኮዉን ሲፈጽም ከፖለቲካዊ ወገንተኝነት በፀዳ መልኩ ሊሆን ይገባዋል ብለዋል።

ተቋሙ የግዳጁን አፈጻጸም ዉጤታማነት ከፍ ለማድረግ መንግሥት በሰጠዉ አቅጣጫ መሰረት በተቋሙ ውስጥ የሪፎርም ሥራ እንደሚሰራ አመልክተዋል።

ድሬክተር ጄነራሉ ለሕዝብ የሚተጋ፣ የሚሠራ እንዲሁም የሃገርና ሕዝብ ጥቅም የሚያስከብርና የሚያስቀጥል ተቋም ይደረጋል ብለዋል።

መንግሥት በጀመረው የለውጥ ጉዞ ሕገ መንግሥቱንና ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን ከማገልገል አኳያና የተጣለበትን ተልዕኮ ለመወጣት ብቃት ያለው ተቋም እንደሚደረግ ገልፀዋል።

ከዚህ ባለፈ ማንኛውንም ሕዝብ እኩል የሚያገለግል ተቋም ለማድረግ አቅጣጫ ተቀምጦ ወደ ሥራ እንደተገባ ታውቋል።

%d bloggers like this: