ነፃ ያልወጣው ነጻ አውጭ ጄኔራል ጥቅማችን ተቋረጠ በማለት ወያኔ ኢትዮጵያንና በመካሄድ ላይ ያለውን ለውጥ በኃይል ለማዳፈን መዘጋጀቱን ገለጸ! ወይ ወያኔዎች በሕዝብ መተፋታችውን አለመገንዘብ!

4 Jul

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

 

“…ያለው ሁኔታ ከ[ዐ]ብይ ጋር የተገናኘ እንደሆነ ሳይሆን እናይ በመሰረቱ ማየት ያለብን እንደጠላት ሃይል አድርገን ነው። እንደጠላት ሃይል አድርገን ካልወሰድነው እንዴት አምርረን እንደምንወጋውም ግልፅ ሊሆንልን አይችልም። ስለዝህ ሄዶ ሄዶ ከኢህአዴግ ውስጥ ተነስቶ እየበሰበሰ ራሱን እየበላ የኢህአዴግም ፕሮግራም ጭምር እየበላ በልቶ በልቶ ከጨረሰ ብሁዋላ በመጨረሻ በስልጣን ላይ የወጣው ሃይል ከኢህአዴግ ፕሮግራም ጋር የሚገናኝ ትንሽ የኢህአዴግ ሽታ እንኩዋን የለውም። ለእኔ ይህ የጠላት ሃይል ነው። እንደጠላት ሃይል እንውሰደው። አሁን የኢህአዴግ ሽታ የለውም ማለት ይህ ሃይል ህዝባዊ ሽታ ያለው አይደለም ማለት ነው። ከህዝባዊነት የወጣ ስላልሆነ ሄዶ ሄዶም የጊዜ ጉዳይ ካልሆነ ለፌደራላዊ ስርአታችን ሊያጠፋ የሚችል አካሄድ እየሄደ ያለበት ሁኔታ ነው ያለው።”

 

የወያኔው ብልጣ ብልጥ ልብ ሲያደርቅ!

“…ሁላችንም እንደምናውቀው [ሥ]ልጣን ከ[ሕ]ዝብ ነው። ስልጣን ከህዝብ የምርጫ ድምፅ ነው የሚገኘው። ያን የህዝብ ድምፅ መሰረት አድርጎ ደግሞ የሚ[ሠ]ራ ሥርአት ይኖራል። ባጭሩ አሁን ያለው ግን የግለሰው ፍፁም የ[ሥ]ልጣን ገዥነትና አንበርካኪነት ነው ያለው። የመንግስታችንን ስርአት ትርጉም ወደሌለው ደረጃ አውርዶታል። ኢሥአዴግ አሁን ጠፍቷል። ትርጉም ወደሌለው ደረጃ አው የወረደው። ግንባሩም፣ ምክር ቤቱም ፓርላማዉም ትርጉም ወደሌለው ደረጃ ወርዷል። ፌደረሽን ምክር ቤቱን ጨምሮ ሁሉም ነገር ምልክት ወደሆነበት ደረጃ ወርዷል። ስለዚህ አሁን ሄዶ ሄዶ የንጉ[ሠ] ነገ[ሥ]ት አገዛዝ ተመስርቷል ማለት ነው። በቃልም እየሰማን ነው። ንጉሠ ነገሥት የሚል።”

One Response to “ነፃ ያልወጣው ነጻ አውጭ ጄኔራል ጥቅማችን ተቋረጠ በማለት ወያኔ ኢትዮጵያንና በመካሄድ ላይ ያለውን ለውጥ በኃይል ለማዳፈን መዘጋጀቱን ገለጸ! ወይ ወያኔዎች በሕዝብ መተፋታችውን አለመገንዘብ!”

 1. አለም July 9, 2018 at 16:23 #

  ውድ አቶ ከፍያለው፥
  ጥያቄ አለኝ።
  ጠ/ሚ አብይ በኢትዮጵያና በኤርትራ መሃል ያለውን ጠብ ወደ ሰላም አሸጋገሩ እየተባልን ነው። ሰላም መኖሩን የማይፈልግ ያለ ቢኖር ህወሓት ብቻ ይመስለኛል። ኢሳይያስ የምናውቀው ኢሳይያስ እንጂ አዲስ ግለሰብ አይደለም። እንኳን ለኢትዮጵያ ለራሱም ህዝብ አልበጀም። ከህወሓት/መለስ ጋር ሆነው አሰብን የተዋዋሉ፣ ደም ያፋሰሱ ናቸው። ኤርትራውያን ባገራችን ቡና ላኪ እስኪሆኑ ድረስ፣ በጠራራ ፀሐይ ዘረፋና ግድያ ሲያካሂዱ፤ ሥራ ቅድሚያ ሢሰጣቸው፣ አንድ ቢሊዮን ዶላር መለስ ቼክ ሲጽፍላቸው፣ ወዘተ። ሰማንያ ሺ ሰው ደም የፈሰሰው ለምን ነበር? ለመሆኑ ይኸ ሁሉ ግርግር ለኢትዮጵያ ምን ጥቅም ያስገኛል? ማንነው ለኢትዮጵያ ጥቅም የቆመ? እነ ዶ/ር ብርሃኑ ሥልጣን ያግኙ እንጂ ስለ ኢትዮጵያ ጥቅም ደንታ የላቸውም። ባለፈው ቢቢሲ ሃርድቶክ ላይ የግንቦት 7 አቋም የኤርትራን መብት ማስከበር እንደ ሆነ ነኣምን ገልጾ ነበር። ሌንጮ ለታ ላፋሰሰው ደም ወደ ሄግ ሄዶ ለፍርድ መቅረብ ሲገባው አገር ቤት ገባ አሉን። ማንነው የኢትዮጵያን መብት የሚያስከብረው? ጠ/ሚ አብይ “ተፎካካሪ” እንጂ “ተቃዋሚ” አንበል ብለዋል። ለዶ/ር መረራ አዲስ ሹመት ሰጥተዋል። ለዶ/ር ብርሃኑም ይቀጥሉ ይሆናል። እንደ 1983ቱ ለንደን ኰንፈረንስ ዛሬም የአገራችን ዕጣ በአሜሪካኖች፣ በኢሳይያስና በዶ/ር በረከት እጅ ወድቋል። ኢትዮጵያውያን የህወሓትን መርዝ ውጠው ገና አማራ፣ ኦሮሞ እያሉ ነው። በጎሳ ተደራጅተው አናሳ ሆነዋል፤ ለአገር የሚበቁ አንድ የሉባቸውም።

  ለምን ወቅታዊ ትንታኔ የሚሰጡ ጠፉ? አብይ ኤርትራ ድረስ ተጠርቶ እንደሄደ ያህል ተጉዞ ውል መፈራረሙ አሳፋሪ ነው። በኢትዮጵያና በኤርትራ መሓል ድንበር የለም ማለት ውሎ አድሮ ችግር አለው። የወቅቱን ችግር ለመፍታት ሌላ ቆይቶ የሚከሰት ችግር መፍጠር ነው። ችግሩን የሚቀሰቅሱት ደግሞ ኤርትራውያን ይሆናሉ። አሁን እየተካሄደ ያለው የሰላም ግርግር ጥቅሙ ከኢትዮጵያ ይልቅ ለኤርትራ ነው። ኤርትራውያን ሲያያዝላቸው መልሰው የሚናከሱ ናቸው። መረሳት የሌለበት፣ ኢትዮጵያና ኤርትራ ሁለት አገር እንጂ አንድ አይደሉም። አንድም አይሆንኑም። በተባበሩት መንግሥታት ዘንድ እንደ አገር ተመዝግበው ወንበር ይዘዋል። ዶ/ር በረከት ኤርትራ የኢትዮጵያ ቅኝ ግዛት ነች ብሎ ሲያታልል ከርሞ፥ አሁን ተመልሶ ከፌዴሬሽን፣ ከኮንፌዴሬሽን እንቁልልጭ እያለ ነው። ስለ ኤርትራ እንጂ ስለ ኢትዮጵያ ቅንጣት ገዶት አያውቅም። በሰላም አሳብበው ኤርትራውያን አገራችን እንዳይዘርፉ ምን ማገጃ ተደርጓል? በዩጋንዳ፣ በኮንጎ፣ በደቡብ ሱዳን የሚያካሄዱትን ማየት በቂ ማስጠንቀቂያ ይሁነን። በኦሮምያና በአማራ፣ በቤንሻንጉልና በጋምቤላ ያሉ ዜጐች ክትትል ማድረግ ይጠበቅባቸዋል። ኢትዮጵያ ለኢትዮጵያውያን፤ ኤርትራ ለኤርትራውያን!!

  Like

Comments are closed.

%d bloggers like this: