በኢ/ር #ስመኘው ግድያ #የሜቴከና_ህወሓት እጅ አለበት ይባላል!

26 Jul

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

በሥዩም ስዩም ተሾመ

ሰኞ ዕለት ጠ/ሚ አብይ አህመድ “የህዳሴ ግድብ አሁን ባለው አካሄድ የዛሬ አስር አመት አይጠናቀቅም” ማለቱ ይታወሳል፡፡ ትላንትና ደግሞ የመብራት ሃይል ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር #አዜብ_አስናቀ ከመከላከያ ኢንጂነሪግ እና የህወሓቶች ዘረፋ ጋር በተያያዘ ከሃላፊነት ሊነሱ እንደሆነ ዋዜማ ራዲዮ ዘግቧል፡፡ በዚህ መሠረት የዶ/ር አመራር የግንባታ ሂደቱን ለማፋጠን የማስተካከያ እርምጃ በመውሰድ ላይ እንደሆነ መገመት ይቻላል፡፡ ለዚህ ደግሞ የግንባታ ሂደቱ እንዳይፋጠን ዋና ማነቆ የሆኑትን የመከላከያና ህወሓት ባለስልጣናት ከቦታው ጠራርጎ ማስወገድ ያስፈልጋል፡፡ ከዚህ አንፃር ኢንጂነር ስመኘው ብዙ ሚስጥር ያወጣል፡፡ ስለዚህ ኢንጂነሩ ይህን ከማድረጉ በፊት የመከላከያና ህወሓት ገድለውታል ወይም አስገድለውታል፡፡ ከዚህ በፊት ወዳጄ William በህዳሴው ግድብ ዙሪያ ጥልቅ ትንታኔ የያዘ ፅሁፍ አውጥቶ ነበር፡፡ በዚህ ፅሁፍ ለግድቡ ግንባታ መጏተት ዋናው ምክንያት በዶ/ር #ደብረፂዮን ገ/ሚካኤል የሚመራው ቦርድ እና #የሜቴክ ጄኔራሎች መሆናቸው በግልፅ ጠቅሶ ነበር፡፡ ይህን ባደረገ ጥቂት ቀናት ውስጥ ወደ ሀገሩ እንግሊዝ ተጏዘ፡፡ ከዚያ ወደ ኢትዮጵያ ሊመለስ ሲል ቪዛ ተከለከለ፡፡ ይህ ጋዜጠኛ ከሞት የተረፈው እንግሊዛዊ በመሆኑና ቢሞት ከሀገሪቱ የውጪ ደህንነት መስሪያ ቤት (MI6) ምላሹ የከፋ ስለሚሆን ብቻ ነው፡፡ ጋዜጠኛው እውነታውን በመዘገቡ ምክንያት ይህን ካደረጉ ሙሉ መረጃውን በተግባር የሚያውቀው ኢንጂነር ስመኘውን ደግሞ ከመግደል ውጪ አማራጭ የላቸውም፡፡ ይህን ያደረጉት ደግሞ ለህዳሴው ግድብ ግንባታ የተመደበውን ገንዘብ ሲዘርፉ የኖሩት የመከላከያና ህወሓት ባለስልጣናት ናቸው፡፡ ከዚህ በፊት ኢንጂነሩ ለደህንነቱ በመስጋት ወደ ውጪ ሀገር ለመሸሽ ሞክሮ የነበረ መሆኑ፣ እንዲሁም አንዳንድ የህወሓት አፈ-ቀላጤዎች ደግሞ ቀድመው ሙሾ ሲያወርዱ የነበረ መሆኑ ጠቋሚ ነው፡፡

/ምንጭ  Hashim Ethio Ethio

በዚህ ፌስቡክ ላይ ይህ ጥቆማ መጻፍ አጋጣሚ አስገርሞኛል፡፡ ረቡዕ ማምሻውን የዋዜማን ዜና ካነበብኩ በኋላ፣ እኔም በትዊተር ሚከተለውን በትኜ ነበር። ማን ኢንጂነሩን እንደገደላቸው ይጠቁማል ለማለት ሳይሆን፡ ምርመራው ሠፋ እንዲል ይረዳል።

እኔ ካለፈው በማስታወስ የጻፍኩት ስለኢንጅነር ስመኝው ሳይሆን፡ ይህ ፌስቡክ እንዳነሳው የሜቴክ ወንጀልኛነት በኢትዮጵያ ውስጥ በተለይም ጄኔራል ክንፈ ዳኘው ቀደም ሲል የፈጸሙት ውንብድና ላይ ያተኮረ ነበር እንደሚከተለው፡-

እስከ መቼ ይሆን፣ ወሮበሎቹና ዘራፊዎች ጥቅማችን ተጓደለ ብለው ጥቃታቸውን እንዲያስፋፉ የሚፈቀድላቸው?

ምኅረትና ይቅርታ ጥሩ ነገር ናቸው። ነገር ግን ከወር በፊት እንዳልኩት፣ ኅብረተሰብ ትጥቁን ፍቶ፡ እጁን ወደ ሰማይ አንስቶ፡ ደም የጠማቸው፡ ዘረፋ ቆመብን ብለው ሕዝባችንን ለአደጋ እያጋለጡ ዛሬ በኢንጂነር ሰመኝ ግድያ እንደተደረገው፣ ሃገራችንን ወደ እርስ በእርስ ግጭት ለሚገፉ — ጥፋትና ቅጣት ተፋተዋል ብለው በሚያምኑ የታወቁ ከርሳቸው አምላኩ ሰላምችንን ለማጣትና የለውጥ አቅጣጫችንን ለመሳት አይደለም!

ይታሰብበት!

 

%d bloggers like this: