የሕውሃቱ ጌታቸው አሰፋ ድኅንነት መ/ቤት በሰኔ 16ቱ ፍንዳታ ያለው ሚና ላይ ፖሊስ ተጨባጭ መረጃ ማግኘቱን ለፍርድ ቤት አስታወቀ! በተጠረጠሩት ጥላሁን ጌታቸውና ብርሃኑ ጃፋር ላይ የጠየቀውን ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ፈቀደ

27 Aug

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 21፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በሰኔ 16 የጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የድጋፍ ሰልፍ ላይ ራሱ ቦምቡን በማፈንዳት አደጋውን በራሱ ላይ አድርሶ ለሁለት ሰዎች ህይወት መጥፋትና 164 ሰዎች ላይ  የአካል ጉዳት በማድረስ በምርመራ ላይ የሚገኘው ተጠርጣሪ  ጥላሁን ጌታቸውና  በዛሬው  ዕለት  ፖሊስ ቦምቡን የሚያፈንዱ  አካላትን በመመልመል፣ በማደራጀት፣ በማስተባበርና በራሱ መኪና በመጫን  ተጠርጣሪዎችን ቦምቡ የፈነዳበት ቦታ ድረስ አድርሷል የተባለው ተጠርጣሪ  ብርሃኑ ጃፋር  ፖሊስ ወንጀሉን  መፈጸማቸውን የሚያመላከቱ መረጃዎች እንዳለው ለፍርድ ቤት ገለጸ።

በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ተረኛ 1ኛ የወንጀል ችሎት የመርማሪ ፖሊስን የምርመራ ውጤት እና የተጠርጣሪዎችን  የተጨማሪ ጊዜና የመቃወሚያ  አስተያየት አዳምጧል።

የፌደራል ፖሊስ መርማሪም በዛሬው የጊዜ ቀጠሮ ተጠርጣሪዎቹ ከሌሎች ግብረ አበሮቻቸው ጋር በመሆን  የራሳቸውን ርእዮተ ዓለም በማራመድ  በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይና በሌሎች ከፍተኛ ባለስልጣናት ላይ ጥቃቱን ለመሰንዘር በማቀድ  ሰላማዊ ሰልፉን ለማደናቀፍ የተንቀሳቀሱ መሆናቸውን ጠቁሟል።

በዚህም 1ኛ ተጠርጣሪ አቶ ጥላሁን ጌታቸው በበኩሉ በየጊዜው ተጨማሪ  ቀጠሮ ሊጠየቅብኝ አይገባም ዋስትና ይፈቀድልኝ ሲል ፍርድ ቤቱን የጠየቀ ሲሆን፥  2ኛው ተጠርጣሪ አቶ ብርሃኑ ጃፋርም በጠበቃው አማካኝነት ከዚህ በፊት ቦምቡን በማቀበል ምርምራ ሲከናወንበት የነበረ ሲሆን፥  ዛሬ ደግሞ ተጠርጣሪዎቹን  አደራጅቷል፣ መልምሏል፣ እንዲሁም አስተባብሮ በራሱ መኪና ተጠርጣሪዎቹን  ከእነቦምቡ ከቤታቸው አንስቶ  ቦምቡ የፈነዳበት ቦታ ድረስ ሸኝቷል መባሉ አዲስ ጉዳይ ነው ብሏል።

በየጊዜው ለተመሳሳይ ጥያቄ  ተጨማሪ ጊዜ መጠየቁም  አግባብ አይደለም  ዋስትና ሊፈቀድለት ይገባል ሲሉ  የመርማሪ ፖሊስን የተቃወሙ ሲሆን፥ ራሱ ብርሃኑ ጃፋርም  ምስክር ካልሆንክ ተብየ ነው  ተጨማሪ አዲስ ክስ የሚመጣበኝ ስለዚህ ይህ ጉዳይ ሊታይልኝ ይገባል  ሲል ለፍርድ ቤቱ ጥያቄ ማቅረቡ ተገልጿል።

መርማሪ ፖሊስ በበኩሉ ተጠርጣሪዎቹ በዋስ ቢወጡ አደጋ ሊፈጥሩና  በዚህ ወንጀል ከከፍተኛ እስከ መካከለኛ  አመራሮች እጃቸው ያለበት ወንጀል በመሆኑ  የዋስ መብት ሊፈቀድ አይገባም ሲል የዋስትና ጥያቄውን  ተቃውሟል።

የሁለቱን ተጠርጣሪዎች የተመለከተው ፍርድ ቤትም በሌሎች ሀገራትም እንደዚህ አይነት ታላላቅ ውንጀሎች ሲፈጸሙ ሀገራቱ ረጅም ጊዜ ውስደው  የቴክኒክ ምርመራ የሚያደረጉ መሆኑን በማንሳት ከዚህ አንፃር ለመርማሪ ፖሊስ  ለምርመራ የተሰጠው ጊዜ አጭርና ጥያቄው አሳማኝ በመሆኑ፣ የወንጀል ድርጊቱ  ከባድና ውስብስብ  መሆኑ  ከዚህ በፊት በጠቅላይ አቃቤ ህግ ተጨማሪ  ማስረጃ ይሟላ ተብሎ  መዝገቡን የመለሰው  ተገቢነት ያለው በመሆኑ ፖሊስ የጠየቀው የ14 ቀን ተጨማሪ ጊዜ ፈቅጃለሁ ብሏል።

መርመሪ ፖሊስም ምርመራውን በትጋት እንዲሰራ ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ  ሰጥቷል።

በዚህም ፍርድ ቤቱ ለጳጉሜ 5 ቀን 2010 ሶስት ስዓት ተኩል  ተለዋጭ ቀጠሮ ስጥቷል።

%d bloggers like this: