100 ሺ ብር መደለያ የቀረበላቸው ፖሊሶች ሕገ ወጦችን በቁጥጥር ሥር አዋሉ

4 Sep

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

ከጥቁር ገበያ ጋር በተያያዘ የታሸጉ ሱቆችን በመክፈት የውጪ አገር ገንዘቦችን ለማውጣት በማሰብ 100 ሺ ብር ለፖሊሶች መደለያ ያቀረቡት ግለሰብና ተባባሪዎቻቸው በቁጥጥር ስር ዋሉ፡፡

በከተማዋ የውጪ አገር ገንዘቦች በህገ ወጥ መንገድ ከሚመነዘርባቸው አካባቢዎች አንዱ በሆነው ጋንዲ ሆስፒታል አካባቢ ከሚገኙት የንግድ ሱቆች መካከል ጥቂቶቹ ከዚሁ ተግባር ጋር በተያያዘ ሰሞኑን እንዲታሸጉ ተደርገዋል፡፡ ሱቆቹ ከመታሸጋቸውም ሌላ በፖሊስ ኃይል ሲጠበቁና ቁጥጥር ሲደረግባቸው ቆይቷል፡፡

ባለፈው ረቡዕ አመሻሽ ላይ ከታሸጉት የንግድ ሱቆች መካከል የአንደኛው ሱቅ ባለቤቶች ሥፍራውን ከሚቆጣጠሩት የፖሊስ አባላት መካከል ለሁለቱ “100 ሺ ብር ጉቦ እንስጣችሁና ሱቁን ከፍተን በውስጡ የሚገኘውን ገንዘብ እናውጣ” የሚል ጥያቄ ያቀርቡላቸዋል፡፡

የፖሊስ አባላቱም በሃሳቡ የተስማሙ በመምሰል የሱቁን ባለቤትና ተባባሪዎቻቸውን በቁጥጥር ሥር ያዋሉ ሲሆን፤ ሱቁ ተከፍቶ ፍተሻ ሲደረግም ከ300 ሺ ብር በላይና በ10 ሺዎች የሚቆጠር የውጪ አገራት ገንዘብ ተይዟል፡፡

ፖሊስ በአሁኑ ወቅት በጉዳዩ ላይ ምርመራ እያደረገ እንደሚገኝ ታውቋል፡፡

/Addis Admas

 

Leave comment

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

%d bloggers like this: