የዐቢይ አስተዳደር የታጠቁ ኃይሎች በአገር ውስጥ እንዲንቀሳቀሱ እንደማይፈቅድ በድጋሚ አስታወቀ! ለምንስ ፈቀደ ሲጀመር?

10 Oct

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

ከሰሞኑ የኦነግ አመራር አቶ ዳውድ ኢብሳ ከዋልታ ቴሌቪዥን ጋር በነበራቸው ቆይታ ከመንግስት ጋር ትጥቅ ለመፍታት አልተደራደርንም፤ ትጥቅ የሚፈታም የሚያስፈታም የለም ማለታቸውን ተከትሎ ዛሬ የኢፌዲሪ መ/ኮ/ጉ/ፅ/ቤት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ካሳሁን ጎፌ በጉዳዩ ላይ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

መንግስት የፖለቲካ ምህዳሩን ለማስፋት ባደረገው የሰላም ጥሪ መሰረት በርካታ የፖለቲካ ድርጅቶችና የትጥቅ ትግል ሲያደርጉ የነበሩ ሀይሎች ወደሀገር መግባታቸውን ያስታወሱት አቶ ካሳሁን ኦነግም ወደ ሀገር ሲገባ 1300 ያህል ጦሩን ትጥቅ አስፈትቶ መግባቱንና ጦሩም በአሁኑ ሰዓት በአርዳይታ ማሰልጠኛ ስልጠና እየተከታተለ ነው ብለዋል፡፡
ኦነግ በአስመራ በተደረጉ ሶስት ድርድሮች በሰላማዊ መንገድ ወደ ሀገር ገብቶ ለመፎካከር መስማማቱ የሚታወቅ ነው፤ ለዚህም ወደሀገር ሲገባ ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል ያሉት አቶ ካሳሁን በድርድሩ ወቅት ትጥቅ የመፍታት ጉዳይ ያልተነሳው የመደራደሪያ ጉዳይ ስላልሆነ ነው ብለዋል፡፡

ሰላማዊ ትግል የሚደረገው በሀሳብ እንጅ በአፈሙዝ ስላልሆነ ትጥቅ የመፍታትን ጉዳይ ለድርድር የማናቀርበውና ቀይ መስመር ነው ሲሉ አቶ ካሳሁን በመግለቻቸው ተናግረዋል፡፡

  

ስለሆነም ኦነግ አቋሙን እንደገና በመፈተሽ ትጥቁን እንዲፈታ መንግስት ጥሪውና ያስተላልፋል ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው ካልሆነ ግን የዜጎችን ደህንነት ለማስጠበቅና ህገመንግስታዊ ስርዐቱን ለማስጠበቅ ሲል መንግስት ትጥቅ የማስፈታቱን ስራ ይሰራል ብለዋል፡፡

መንግስት ህግን የማስከበር ስራውን በቆራጥነት ስለሚሰራ መላው ህዝብ የደህንነት ችግር ይገጥመኛል በማለት ስጋት ላይ እንዳይወድቅና እንዳይደናገር አቶ ካሳሁን መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

መስከረም 30/2011 /የኢፌዲሪ መ/ኮ/ጉ/ፅ/ቤት/

 

ተዛማጅ:

ጠ/ሚሩ ተፎካካሪ ፓርቲዎች ትጥቅ መፍታት እንዳለባቸው አስገነዘቡ! የኦሮሞ ነፃነት ግንባሩ (ኦነግ) ዳውድ ኢብሣ ‘ትጥቅ ፈታ መባል ሴንሲቲቭ ጥያቄ’ ነው ይላሉ! ኢትዮጵያ ወዴት እያመራች ነው?

Walta & ESAT Misconstrued Dawud Ibsa for their Objectives – Mereja

ESAT Eletawi Tue 09 Oct 2018

 

Leave comment

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

%d bloggers like this: