የአዲስ አበባ ከተማ መሬት ልማትና አስተዳደር ከማዘጋጃ ቤት እንዲወጣ ተወሰነ! ተጠያቂነትና አቤቱታ ሰሚ ዕጦትን ከጉበኛና ዘራፊው ዘመነ ሕወሃት ለማባባስ? አልያ?

24 Oct

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ ከማዘጋጃ ቤት ቅጥር ግቢ እንዲወጣ ተወሰነ፡፡

የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ ለዓመታት ከነበረበት ማዘጋጃ ቤት እንዲወጣ የተወሰነው፣ በማዕከል ደረጃ የሚገኙ ሁሉም የመሬት ተቋማት በአንድ ላይ ሆነው አገልግሎት መስጠት አለባቸው ተብሎ ነው፡፡

በዚህ መሠረት የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮና በሥሩ የሚገኙ ስድስት ተቋማት፣ እንዲሁም የከተማውን ማስተር ፕላን የመቆጣጠር ሥልጣን የተሰጠው የፕላን ኮሚሽንና የግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣን ካሉበት ተነስተው ቦሌ ክፍለ ከተማ የቀድሞ 24 ቀበሌ አካባቢ በሚገኝ የግለሰብ ሕንፃ ውስጥ ይገባሉ ተብሏል፡፡

የከተማ አስተዳደሩ ውሳኔ ግን በመሬት ሥሪት ባለሙያዎች ላይ አግራሞት ፈጥሯል፡፡ ሪፖርተር ያነጋገራቸው የመሬት ሥሪት ባለሙያዎች እንደሚሉት፣ ከአስተዳደሩ ዋነኛ ሥራዎች መካከል መሬትና መሬት ነክ ሥራዎች ግንባር ቀደሞች ናቸው፡፡ ይህንን ግዙፍ ተቋም ከማዘጋጃ ቤት ማስወጣት አግባብ እንዳልሆነ፣ ምክንያቱም ቅሬታ ያለው አካል ለከንቲባው አቤቱታ ማቅረብ የሚችለው እዚያው ሆኖ አገልግሎት መስጠት ሲችል ነው በማለት ያስረዳሉ፡፡

ያም ሆኖ ግን በዚህ ሳምንት የመሬት ተቋማቱ ከማዘጋጃ ቤት፣ እንዲሁም ከያሉበት ሌሎች ሕንፃዎች ወጥተው ወደ አዲሱ ቦታቸው ያቀናሉ ተብሏል፡፡


“Even though Addis Ababa had master plans proposed by internationally well-known urban planners, most of the plans failed to direct the development of the city in accordance with the intended goals. In some cases, the planning practices have become part of the prevailing urban problems, such as uncontrolled urban sprawl, high cost of infrastructure development, poor land use management, and deteriorating quality of life.”

— Yirgalem Mahtemie: Carrying the Burden of Long-term Ineffective Urban Planning’ An Overview of Addis Ababa’s Successive Master Plans and their Implications on the Growth of the City (2007)


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሽመልስ እሸቱ (ኢንጂነር) ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ የመሬት ተቋማት ተበታትነው ከሚሰጡት አገልግሎት ይልቅ በአንድ ቦታ ሆነው የሚሰጡት አገልግሎት የተሻለ መሆኑ ታምኖበታል፡፡ በዚህ መሠረት ሁሉም የመሬት ተቋማት አንድ ላይ ሆነው አገልግሎት መስጠት የሚጀምሩበት አሠራር እየተመቻቸ ነው ሲሉ ኃላፊው ገልጸዋል፡፡የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ከአፄ ኃይለ ሥላሴ ዘመነ መንግሥት ጀምሮ መቀመጫውን አራዳ በሚገኘው ማዘጋጃ ቤት አድርጎ አገልግሎት ሲሰጥ ቆይቷል፡፡

ከዚያ ጊዜ ጀምሮ አገልግሎት የተሰጠባቸው ከሦስት መቶ ሺሕ በላይ ፋይሎች በማዘጋጃ ቤት በሚገኘው ማኅደር ክፍል ይገኛሉ፡፡ ቢሮው ወደ ሌላ ቦታ ሲንቀሳቀስ እነዚህን ነባር ፋይሎች አብሮ ባያንቀሳቅስም፣ ሌሎች በእንቅስቃሴ ላይ የሚገኙ ፋይሎችን ግን ይዞ ይጓዛል፡፡

በተለይ በቀድሞ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባዎች አቶ ኩማ ደመቅሳና አቶ ድሪባ ኩማ ጊዜ፣ የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ ቀድሞ ከነበረበት ቢሮ ወደ እሳትና ድንገተኛ አደጋ አገልግሎት የሚገኝበት ሕንፃ ተዛውሮ ነበር፡፡ ከዚያ በኋላም ማዘጋጃ ቤት በሚገኘው ባህል አዳራሽ በመለያያ ግድግዳ የተከፋፈለ ቢሮ ውስጥ እንዲገባ ተደርጎም ነበር፡፡

ነገር ግን ቦታዎቹ ለሥራ ብቻ ሳይሆን ለአገልግሎትና ለፋይል አያያዝ የተመቹ ስላልሆነ፣ ቢሮው በድጋሚ ወደነበረበት ተመልሷል፡፡ አሁን ግን ለመጀመርያ ጊዜ ከማዘጋጃ ቤትና ከከንቲባው በብዙ ኪሎ ሜትሮች ርቆ እንዲከትም ተወስኗል፡

 

ሪፖርተር: የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ ከማዘጋጃ ቤት እንዲወጣ ተወሰነ

 

 

%d bloggers like this: