የሜቴክ የቀድሞ ዋና ዳይሬክተር ሜጄር ጀነራል ክንፈ ዳኘው ሲፈረጥጡ መተማ ተይዘው በቁጥጥር ሥር ዋሉ

13 Nov

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

አዲስ አበባ፣ ህዳር 4፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) የቀድሞ ዋና ዳይሬክተር ሜጄር ጀነራል ክንፈ ዳኘው በቁጥጥር ስር ዋሉ።

የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንዳረጋገጠው ተጠርጣሪው በሁመራ በኩል ከሀገር ለመውጣት ሲሞክሩ ነው በቁጥጥር ስር የዋሉት።

ግለሰቡ በአሁኑ ወቅት ወደ አዲስ አበባ እየመጡ መሆኑም ተገልጿል።

በሙስና ወንጀል የተጠረጠሩ ሌሎች የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ሰራተኞች በቁጥጥር ስር ውለው ትናንት ፍርድ ቤት መቅረባቸው ይታወቃል።

በእነዚህ ተጠርጣሪዎች ላይም ፍርድ ቤቱ የ14 ቀን የጊዜ ቀጠሮ መስጠቱም የሚታወቅ ነው።


 

 


ተዛማጅ

ፍርድ ቤቱ በሙስና ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር በዋሉ የሜቴክ ሰራተኞች ላይ ፖሊስ የጠየቀውን የ14 ቀን ጊዜ ፈቀደ

ፍርድ ቤቱ በሰብዓዊ መብት ጥሰት በተጠረጠሩ ግለሰቦች ላይ 14 ቀን የምርመራ ጊዜ  ፈቀደ 

በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው እስካሁን በቁጥጥር ስር የዋሉ ግለሰቦች ዝርዝር ይፋ ሆነ

ሜቴክ ያለ ህጋዊ የጨረታ ሂደት የ37 ቢሊየን ብር የውጭ ሃገር ግዢ ፈጽሟል  

ጠቅላይ አቃቢ ህግ በሰብዓዊ መብጥ ጥሰት ዙሪያ የሰጡት መግለጫን በተመለከተ የቀረበ

ጠቅላይ አቃቢ ህግ በሀገር ሃብት ላይ ስለተፈጸመው ምዝበራ የሰጠው መግለጫ

 

 

%d bloggers like this: